Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

7 ኢትዮጵያውያን በደብሊን አውሮፕላን ማረፊያ ጥገኝነት ጠየቁ

$
0
0

airplane

ህጋዊ መታወቂያ ወይም የጉዞ ሰነድ አልያዙም ተብሏል
– የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአ/አ ስንነሳ ህጋዊ ሰነድ ነበራቸው ብሏል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየርላንድ ርዕሰ መዲና ደብሊን በኩል ወደ አሜሪካ ሎሳንጀለስ የጀመረውን አዲስ በረራ ለማስመረቅ ባለፈው ቅዳሜ ከአዲስ አበባ በመነሳት ባደረገው ጉዞ፣ ተሳታፊ የነበሩ 7 ኢትዮጵያውያን መንገደኞች፣ አውሮፕላኑ ደብሊን አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ሲያርፍ ወደ ኢሚግሬሽን ክፍሉ አምርተው ጥገኝነት መጠየቃቸውን አይሪሽ ኢንዲፔንደንት ትናንት ዘገበ፡፡ሁለት ህጻናትን ጨምሮ ጥገኝነት የጠየቁት 7 መንገደኞች በአየር ማረፊያ ጣቢያው ሲደርሱ ምንም አይነት መታወቂያ ወይም የጉዞ ሰነዶችን አልያዙም ነበር ያለው ዘገባው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቃል አቀባይ ግን፣ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች በሙሉ ከአዲስ አበባ ሲነሱ ህጋዊ ሰነዶችን ይዘው ነበር፣ ስለ ጥገኝነት ጠያቂዎቹ የግል ጉዳይ ግን አስተያየት መስጠት አንፈልግም ብለዋል፡፡
አየር መንገዱ ላለፉት ከ40 በላይ አመታት ወደ አውሮፓ አገራት በረራ ሲያደርግ መቆየቱን ያስታወሱት ቃል አቀባይዋ፣ የምናጓጉዘው የተሟላ ህጋዊ የጉዞ ሰነድና ተገቢ ቪዛ ያላቸውን መንገደኞች ብቻ ነው ሲሉ መናገራቸውንም ዘገባው ገልጧል፡፡አንድ የአገሪቱ የህግ ክፍል ቃል አቀባይም የተለያዩ አገራት መንገደኞች በደብሊን አየር ማረፊያ ጣቢያ ሲደርሱ ጥገኝነት መጠየቃቸው የተለመደ የዘወትር ክስተት ነው፣ ባለፈው አመት ብቻ 221 መንገደኞች ለትራንዚት አርፈው ጥገኝነት ጠይቀዋል ብለዋል፡፡

The post 7 ኢትዮጵያውያን በደብሊን አውሮፕላን ማረፊያ ጥገኝነት ጠየቁ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles