ጁሙዓ በአንዋር መስጂድ እና በክልል ማእከላዊ መስጂዶች ተሰባስበን በመስገድ ለወኪሎቻችን አጋርነታችንን እንግለጽ!
የአንድ ብር ሰደቃ መርሃ ግብር ይኖረናል!
እስካሁን ለወኪሎቻችን ያለንን አጋርነት በተለያዩ መንገዶች ስንገልጽ ቆይተናል፡፡ የረመዳን ጁሙዓዎች ደግሞ አጋርነታችንን ለመግለጽ ከምንጠቀማቸው አመቺ ገጠመኞች ይመደባሉ፡፡ በእስካሁኑ የትግል ቆይታችን አንድነታችንን አጠንክረን ችግሮቻችንን በጋራ እንደተጋፈጥን ሁሉ አሁንም በዚሁ አንድነታችን እንደምንቀጥል ማረጋገጥ አስፈላጊ ተግባር ነው፡፡ይህን በተግባር ላይ ለማዋል የፊታችን ጁሙዓ በአዲስ አበባ አንዋር መስጂድ እና በክልል ደግሞ በማእከላዊ በሆኑ መስጂዶች ላይ ተሰባስበን የመስገድ እና በቀኑም ለችግረኞች በነፍስ ወከፍ የአንድ ብር ሰደቃ የመስጠት መርሃ ግብር ይኖረናል፡፡ በመሆኑም መርሃ ግብሩን ላልሰሙት ሁሉ በማሰማት ሁላችንም እንረባረብ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን!
የጁሙዓ ቀጠሯችን በአንዋር እና በክልል ማእከላዊ መስጂዶች ነው! ኑ…. ለወኪሎቻችን አጋርነታችንን እንግለጽ!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!
The post ነገ አርብ በአንዋር መስጊድ እና በተመረጡ ከተሞች የመሰባሰብና የሰደቃ ፕሮግራም እንደሚኖር ድምፃችን ይሰማ አስታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.