Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የሸሪዓ ፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንት ጣር በማእከላዊ (1)

$
0
0

የመፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የነበሩትና የቀድሞ የፌዴራል ሸሪዓ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ሸህ መከተ ሙሄ አሰቃቂውን የማእከላዊ ወህኒ ቤት ቆይታቸውን ወደ ኋላ እያጠነጠኑ ይተርኩታል… 

ferdየእኔ ተራ ደርሶ ስለነበር በኪሴ የነበረውን 500 ብር እና ቀበቶ፣ በብሔራዊ ፖስታ ቤት ሪኮማንዴ ያስገባሁበትን ደረሰኝ፣ ሰዓቴንና መታወቂያ ካርድ ተረከቡኝ። እጅግ የደቀቀ ፍተሻ ተደረገልኝ። ይህን እንደጨረስኩ ወደ ጨለማ ቤት ቁጥር 10 አስገቡኝ። የበሩን መዝጊያ ብረት በቁልፍ ከፍቶ ሲበረግደው ጩኸቱ እጅግ ያስደነግጣል። ‹‹ግባ!›› ብሎ ወደውስጥ ገፈተረኝ። ቤቱ ጨለማ ስለሆነ ከውጭ የሚገባ ሰው ምንም ማየት አይችልም። ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ከቤቱ በረንዳ ላይ የመንገድ መብራት ስለነበር በእሱ ውራውርት የተወሰነ ነገር ለማየት እድል አገኘሁ። በበሩ ጩኸት ከእንቅልፍ ባነው ከተጋደሙበት የተወሰኑት ቀና ቀና አሉ። ሸህ ሱልጣን ከእኔ ቀድመው በዚሁ ክፍል ገብተው ስለነበር ተነስተው አቅፈው ‹‹አሰላሙ አለይኩም በሰላም መጣህ! አይዞህ! ለማንኛውም ሲነጋ እናወራለን። እዚህ ተኛ›› ብለው ወደቦታቸው መለስ አሉ። እኔ አገር አማን ብዬ ለመተኛት ጃኬቴን ሳወጣ ያዩኝ የነበሩት በግንቦት 7 ተጠርጠረው የታሰሩት መምሬ ደሳለኝ እንበአል በረጋ አነጋገራቸው ‹‹ወንድሜ አሁን መልሰው ስለሚጠሩህ ልብስህን አታውልቅ፤ አንተ ይህን ቤት የምታውቅ አይመስለኝም፤ ለማንኛውም እንዳትደናገጥ ጋደም በል›› አሉኝ። ይህንን ንግግር በጥርጣሬ ነበር የተቀበልኩት። ‹‹ኧረ ጉድ! መንግሥት እዚህም ሰላይ አስቀምጦ ቢሆን?›› የሚል ጥያቄ በአእምሮዬ ውስጥ ተመላለሰ።*የሸሪዓ ፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንት ጣር በማእከላዊ የመፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የነበሩትና የቀድሞ የፌዴራል ሸሪዓ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ሸህ መከተ ሙሄ አሰቃቂውን የማእከላዊ ወህኒ ቤት ቆይታቸውን ወደ ኋላ እያጠነጠኑ ይተርኩታል… የእኔ ተራ ደርሶ ስለነበር በኪሴ የነበረውን 500 ብር እና ቀበቶ፣ በብሔራዊ ፖስታ ቤት ሪኮማንዴ ያስገባሁበትን ደረሰኝ፣ ሰዓቴንና መታወቂያ ካርድ ተረከቡኝ። እጅግ የደቀቀ ፍተሻ ተደረገልኝ። ይህን እንደጨረስኩ ወደ ጨለማ ቤት ቁጥር 10 አስገቡኝ። የበሩን መዝጊያ ብረት በቁልፍ ከፍቶ ሲበረግደው ጩኸቱ እጅግ ያስደነግጣል። ‹‹ግባ!›› ብሎ ወደውስጥ ገፈተረኝ። ቤቱ ጨለማ ስለሆነ ከውጭ የሚገባ ሰው ምንም ማየት አይችልም። ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ከቤቱ በረንዳ ላይ የመንገድ መብራት ስለነበር በእሱ ውራውርት የተወሰነ ነገር ለማየት እድል አገኘሁ። በበሩ ጩኸት ከእንቅልፍ ባነው ከተጋደሙበት የተወሰኑት ቀና ቀና አሉ። ሸህ ሱልጣን ከእኔ ቀድመው በዚሁ ክፍል ገብተው ስለነበር ተነስተው አቅፈው ‹‹አሰላሙ አለይኩም በሰላም መጣህ! አይዞህ! ለማንኛውም ሲነጋ እናወራለን። እዚህ ተኛ›› ብለው ወደቦታቸው መለስ አሉ።

እኔ አገር አማን ብዬ ለመተኛት ጃኬቴን ሳወጣ ያዩኝ የነበሩት በግንቦት 7 ተጠርጠረው የታሰሩት መምሬ ደሳለኝ እንበአል በረጋ አነጋገራቸው ‹‹ወንድሜ አሁን መልሰው ስለሚጠሩህ ልብስህን አታውልቅ፤ አንተ ይህን ቤት የምታውቅ አይመስለኝም፤ ለማንኛውም እንዳትደናገጥ ጋደም በል›› አሉኝ። ይህንን ንግግር በጥርጣሬ ነበር የተቀበልኩት። ‹‹ኧረ ጉድ! መንግሥት እዚህም ሰላይ አስቀምጦ ቢሆን?›› የሚል ጥያቄ በአእምሮዬ ውስጥ ተመላለሰ።

እንደተባለውም የፖሊስ ጫማ ኮቴ ወደ ክፍሌ አቅጣጫ ተሰማ፤ በግምት ከ10 ደቂቃ በኋላ ነበር። የብረት መሸንጎሪያውን እንደጉድ አስጩኾ ‹‹መከተ ሙሔ ውጣ!›› አለ። ነገሩ እውነት ነው እያልኩ ፈጠን ብዬ ወጣሁ። ከዚያ 32 ቁጥር የምርመራ ክፍል ቢሮ አስገባኝና መርማሪ ሲሳይ የተባለው ፖሊስ በህይወቴና በንብረቴ ዙሪያ ጥያቄዎችን ጠየቀኝ። ከዚያም ለሌሎች መርማሪዎች አስተላለፈኝ። እነ አቡበከር የት እንዳሉና የስልክ ቁጥራቸውን ጠየቀኝ። እንደማላውቅ ሳስረዳው አንደኛው በቦክስ ለመማታት ቃጣው። ‹‹አቁመው!›› አለ። የእኔ ዋና መርማሪ ሆኖ የተመደበው አንዳርጋቸው በተረጋጋ መልክ ምርመራውን ለማስኬድ ፈልጎ እኛን ለመወንጀል ወዳሰቡበት ድርሰታቸው ገባ። ‹‹በህቡእ መቼ ተደራጃችሁ? ህገ-መንግሥቱን ለምን ማፈረስ ፈለጋችሁ? እስላማዊ መንግሥት ለመመስረት ትፈልጋላችሁ! የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ እያለ ለምን በአ.አ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራችሁ?›› ወዘተ በማለት እስከ 8 ሰዓት አቆይቶኝ እኔም ለእያንዳንዱ ጥያቄ ስለጉዳዩ የማላውቅና ያልፈጸምን መሆኑን ምላሴ እስከሚደርቅ ላብራራ ሞከርኩ። መርማሪዎቹም ዙሪያዩን ከበው አንዱ በሐይል ቃልና ዘለፋ፣ ሌላው በተለሳለሰ ዘዴ ምርመራ ሲያደርጉ ከቆየን በኋላ መጨረሻ ‹‹እንዲህ በቀላሉ የምንላቀቅ አይምሰልህ! ለማንኛውም ለዛሬ ይብቃ›› አስወጡኝ። በእጄ ላይ ያለው ካቴና ጠብቆብኝ ስለነበር እጄን እያሻሻሁ ወደ ጨለማ ቤት ቁጥር 10 ተመልሼ ገባሁ።

ለመተኛት ሞከርኩ። እንቅልፍ ከየት ይምጣ? የቀኑ ጾም፣ የቤት ብርበራ፣ የ32 ቁጥር የምርመራ ቆይታ፣ ያልተያዙት ጓደኞቼ ነገር፣ በአጠቃላይ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ላይ እየተከፈተ ያለው ጦርነት… ነገሮችን በማውጠንጠን አላህን በዱዓና በዚክር እየተማፀንኩ ከአንድ ሰኣት በላይ አለፈ። በክፍሉ ውስጥ ባለው ውሃ ዉዱ አድርጌ ሰላተል ለይል በመስገድ ላይ እያለሁ ሸህ ሱልጣን ተነሱ። እሳቸውም ዉዱ አደረጉ። ሶላት እየሰገድን ፈጅር ተቃረበ። ሱብሂን ሰላት በጀመዓ ሰገድን። በረጅም ቁኑት በምርመራ የደከመው ቀልባችን በረጅም ቁኑት ወደነበረበት ተመለሰ።

ከነጋ በኋላ 12 ሰዓት አካባቢ የእስረኖች ቁርስ ከመቅረቡ በፊት ለማደር በሩ ተከፍቶ ሽንት ቤት ተራ በተራ የ(8) ክፍል ታሳሪዎችን አስወጡን። ከዚያ ቁርስ ከበረንዳው ላይ ተራ በተራ ተሰልፎ መታደል ተጀመረ። እኔና ሸህ ሱልጣን ረመዳን ወር 2ኛ ቀን ምንም ሳንቀምስ ቀጥለናል። በነበረው ሁኔታ ራብና ጥም ብዙም አልተሰማንም።

ይሁን እንጂ ከአስር በኋላ የውሃ ጥም ፍላጎት ስሜት ጠንከር ብሎ ተሰምቶናል። እኛ ክፍል የነበሩት ታሳሪዎች የሚከተሉት ነበሩ፡- 1ኛ. መምሬ ደሳለኝ እምቢያለ – የግንቦት 7 ተጠርጣሪ 2ኛ. አቶ ኦፔኝ የጋምቤላ ተወላጅ – የጋምቤላ የደኅንነት ኃላፊ 3ኛ. የኦፔኝ ጓደኛ – የጋምቤላ ፖሊስ አባል 4ኛ. አቶ ወንድ አምላክ – በፒያሳው ባንክ ዝርፊያ ተጠርጥረው የታሰሩ (ዘበኛ) 5ኛ. አንድ ወጣት የጎንደር ልጅ – የግንቦት 7 ተመልማይ ተጠርጣሪ

ሁሉም ተራቸው ደርሶ አንዳንድ ዳቦና ሻይ በኩባያ ታደሉ

The post የሸሪዓ ፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንት ጣር በማእከላዊ (1) appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>