በእነ ወይንሸት ሞላ የክስ መዝገብ መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ በእስር ላይ የሚገኙት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለወርቅ ላይ ፖሊስ በድጋሜ ያቀረበውን የምርመራ መዝገብ ዳኞቹ አንቀበልም ብለዋል፡፡
እነ ወይንሸት ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ቀርበው እንዲፈቱ ተወስኖ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ፖሊስ ከእስር ሲወጡ በር ላይ በድጋሜ አስሮ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዳቸው ይታወቃል፡፡
ዛሬ ሰኔ 18/2007 ዓ.ም ቀደም ብለው ተከሰውበት በነበረው ተመሳሳይ ‹ወንጀል› ፖሊስ የምርመራ መዝገብ ይዞ ቀደም ብለው ውሳኔ ባገኙበት በተመሳሳይ ቄራ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበር ቢሆንም ዳኞቹ ‹‹እኛ ፈርደናል፤ እንዲለቀቁም ወስነናል፣ ከዚህ በኋላ ይህን ጉዳይ አናይም›› በሚል መዝገቡን እንደማያዩ ገልጸው መልሰዋቸዋል፡፡
ፖሊስ ፍርድ ቤቱ ክሱን እንደማያይ ከገለጸ በኋላ እነ ወይንሸትን ወደ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የመለሳቸው ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ እንዲፈቱ የወሰነላቸው አራቱም እስረኞች ጉዳይ ምን ሊሆን እንደሚችል ግን ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አልታወቀም፡፡
The post እነ ወይንሸት ሞላ ላይ ድጋሜ የቀረበውን መዝገብ ዳኞች አንቀበልም አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.