Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ታላቁ ዲፕሎማት አምባሳደር ኮነሬል ፀጋዬ መሸሻ ጉግሳ (ሮቤል አባቢያ) አረፉ

$
0
0

ዘሐበሻን ጨምሮ በተለያዩ ድረገጾች ስለሃገራቸው ሮቤል አባቢያ በሚል ስም ስለሃገራቸው ሲጽፉ የከረሙት ታላቁ ዲፕሎማት አምባሳደር ኮነሬል ፀጋዬ መሸሻ ጉግሳ ባደረባቸው ህመም ዩጋንዳ ካምፓላ ኢንተርናሺናል ሆስፒታል በ79 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

Robel Ababiya

በንጉሱ ዘመን የኢትዮጲያ አየር ሃይል አካዳሚ ከፍተኛ መምህርና ሃላፊ በደርግ ጊዜ ደሞ አገሪቱ በዚያድባሬ ጦርነት በተከፈትባት ቀውጢ ሰዓት የታላቋ ሶቬትህብረት የኢትዮጲያ አንባሳደር ሆነው ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። ከዛም የሲቪል አቬሽን ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ሆነው በኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ተሹመው ሰርተዋል።

በርካታ አየር ማረፍያዎችንም አስገንብተዋል። ደርግ ሊወድቅ አካባቢም በሲቪል ኢንጂነሪንግ ሙያ በተባበሩት መንግስታት ተቀጥረው ኡጋንዳና ቦትስዋና ላይ ሰርተዋል። በዩጋንዳ ካምፓላ የሚገኘውን የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ካምፓላ መካነሰላም መድሃንያለም ቤተክርስትያንን ከባለቤታቸው ወይዘሮ ወርቅነሽ በልሁ ጋር በመሆን በመመስረቱ ሂደት አብይ ድርሻ ያበረከቱ ሲሆን የስደተኛው ሲኖዶስ የአፍሪካና አውሮፓ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኤልያስ ልዩ አማካሪ በመሆንም አገልግለዋል።

ኮነሬል ጸጋዬ ሶስት ሴቶች ልጆችና ሁለት ወንድ የልጅ ልጅ አፍርተዋል። ላለፉት 24 አመታት ካገራቸው እርቀው የኖሩት ኮነሬል ፀጋዬ መሸሻ የቀብር ስነስርዓታቸው የፊታችን ሰኞ በትውልድ አገራቸው ኢትዮጲያ እንደሚፈጸም ለቤተሰቡ ቅርበት ካላቸው ወገኖች የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁም ፔን ዘኢትዮጲያ ዘግቧል።

The post ታላቁ ዲፕሎማት አምባሳደር ኮነሬል ፀጋዬ መሸሻ ጉግሳ (ሮቤል አባቢያ) አረፉ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>