አቶ ተክሌ አበራ ይባላሉ። በአሰብ መርከበኛ ሆነው ሰርተዋል። ከአገር ከወጡ 47 አመት ሲሆናቸው፣ በደቡብ አፍሪካ መኖር ከጀመሩ 20 አመት አስቆጥረዋል። በከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀው የሚገኙት አዛውንቱ አቶ ተክሌ ወደ አገር ቤት መመለስ ቢፈልጉም የማስታወስ ችግር አለባቸው። አቶ ምናሴ አበራ የሚባል ወንድም እንዳላቸውና ጌጃ ሰፈር እንደሚኖር ይናገራሉ። በደ/አፍሪካ የሚኖሩ ወገኖች አዛውንቱን ወደ አገር ቤት ለመመለስ አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ኢትዮጵያ ኤምባሲን በስልክ ሲጠይቁ የተሰጣቸው ምላሽ « የኢትዮጲያዊነት ማስረጃ ከሌላቸው እንዳታመጧቸው» የሚል ነበር። ኢትዮጵያዊነት ማስረጃ ማለት ምን ማለት ነው?..ማነው ይህን የሚሰጠው?…ኤምባሲው እንደሌላ ዜጋ ኢትዮጵያውያንን ምስረጃ አምጡ ይላል!? ..እጅግ ያሳዝናል! ኤምባሲው ይህን ቢልም ኢትዮጵያውያን ጥረታቸውን ቀጥለዋል። የአዛውንቱን ማስረጃ በመፈለግ በሊሴፓሴ አገር ቤት ለመላክ እየሞከሩ ነው።
(በፎቶው አዛውንቱ አቶ ተክሌ አበራ)
The post የአዛውንቱ እንግልት – አርአያ ተስፋማሪያም appeared first on Zehabesha Amharic.