Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በአማራው ሕዝብ ላይ እምነት ያጣው ብአዴን በስጋት ምክኒያት የመንግስት ድርጅቶች በልዩ ኃይል እንዲጠበቁ ማስደረግ ጀመረ

$
0
0

Zehabesha News
በህዝቡ ላይ ያላቸው እምነት እያሽቆለቆለ በመመጣቱ በክልሉ ላይ የሚገኙት የመንግስት ድርጅቶች በልዩ ሃይል እንዲጠበቁ ማድረጋቸውን ተገለፀ:: የትህዴን ራድዪ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ባሰራጨው መረጃ መሰረት ግንቦት 16/2007 ዓ/ም የተካሄደውን አስመሳይ ምርጫ የአማራ ክልል ህዝብ በተገለፀው ግዜያዊ ውጤት ባለመርካቱ የተነሳ ድምፃችንን ተሰርቀናል በማለት እየገለፀ መሆኑና የክልሉ ካድሬዎች ግን ህዝቡ ተቃውሞ ሊያነሳ ይችላል የሚል ትልቅ ስጋት ስለፈጠረባቸው በክልሉ የሚገኙት እንደ ሱር ኮንስትራክሽን፤ ባንኮች፤ ቴሌና የመሳሰሉት ድርጅቶችን ቀደም ሲል በህጋዊ መንገድ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ የጥበቃ ሰራተኞችን በማባረር ልዩ ጥበቃ ተብለው በሚታወቁ ታጣቂዎች እንዲጠበቅ እያደረጉ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል::

ይህ አይነቱ በታጣቂ ሓይሎች ተደርጎ ህዝቡ ዓመፅ እንዳያካሂድ ተብሎ የሚደረግ የተጠናከረ የጥበቃ አካሄድ በአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን በመላው ያገራችን አካባቢዎች ውስጥ ለውስጥ እየተሰራበት እንደሆነ። መረጃው አክሎ አስርድቷል፣

The post በአማራው ሕዝብ ላይ እምነት ያጣው ብአዴን በስጋት ምክኒያት የመንግስት ድርጅቶች በልዩ ኃይል እንዲጠበቁ ማስደረግ ጀመረ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>