Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ዳኛ ብርቱካን አቶ ማሙሸት አማረን ክሱ ተቋርጦ ይፈቱ ስትል ፖሊስ አለቅም አለ

$
0
0

Zehabesha News
* የአይ.ሲ.ስን ግድያ ለማውገዝ ሰልፍ የወጣው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ከሶስት ዓመት በላይ እስር ተፈረደበት

(ሕብር ሬዲዮ-ላስ ቬጋስ ) የመኢአድ ሕጋዊው ፕ/ት አቶ ማሙሸት አማረ ሚአዚአ 14 ቀን 2007 በመስቀል አደባባይ በተጠራው ሰልፍ ላይ ብጥብጥ አስነስተዋል በሚል ለተከሰሱበት የፈጠራ ክሱንና የሀሰት ምስክርነቱን ዋጋ የሚያሳጣ በዕለቱ በሌላ ፍርድ ቤት ምርቻ ቦርድን ከሰው ሙግት ላይ መሆናቸውን የሚአስረዳ የሰውና የሰነድ መከላከያ ምስክር ባለፈው አርብ ያቀረቡለት ቦሌ ምድብ የመጀመሪአ ፍርድ ቤት ሶስተና ችሎት ዛሬ በሰጠው ትዕዛዝ አቶ ማሙሸትን ያሰረው ቦሌ ፖሊስ መምሪያ ክሱ በመቋረጡ እንዲፈታቸው ትዕዛዝ ቢሰጥም ፖሊስ ሳይፈታ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳዛወራቸው ያገኘነው መረጃ ይገልጻል።

አቶ ለገሰ ወ/ሃና የዛሬውን የአቶ ማሙሸት የፍርድ ቤት ውሎ ተከታትለው በላኩልን መረጃ መሰረት ባለፈው አርብ በዋለው ችሎት የአቶ ማሙሸት አማረን የመከላከያ ምስክር የሰማው የፌዴራል መጀመሪአ ደረጋ ቦሌ ምድብ ሶስተኛ ችሎት ለዛሬ ለውሳኔ ቀጥሮ የነበረ ሲሆን ክሱን ሲያዩ የቆዩት ዳኛ ብርቱካን ገላው በሰጡት የፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት አቶ ማሙሸት አማረ ድልነሴ በተከሰሱበት ስብሰባን ወይም ጉባዔን ማወክ ክስ ተከሳሹ የተከሰሰበት መዝገቡ የተቋረጠ ስለሆነ ይፈታ ሲል ማክሰኞ ጠዋት በሶስት ሰኣት ሲል ያዛል።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ማክበር የነበረበት ፖሊስ ውሳኔውን ወደ ጎን በማድረግ የቦሌ ፖሊስ መምሪአ ቤተሰብና የአቶ ማሙሰት አማረን የትግል አጋሮች ጠብቁ ሲል ቆይቶ ሌላ ክስ ሳይቀርብ ፣የፍርድ ቤቱም ውሳኔ ሳይከበር ከሰኣታት ጥበቃ በሁዋላ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከእስር ቤት ወደ እስር ቤት ተዛውሯል መባላቸውን የደረሰን መረጃ ያስረዳል።

የመኢአድ ሕጋዊው ፕ/ት አቶ ማሙሸት አማረ ግንቦት 5 ቀን 2007 ከመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ በደህነቶች ታፍነው ተወስደው በዚሁ ፍርድ ቤት በሊቢያ ለሞቱት ወገኖች ሐዘን ለመግለጽ ሚአዚአ 14 ቀን 2007 መስቀል አደባባይ የወጣውን ሕዝብ አሳምጸዋል ብትብት አስነስተዋል በሚል የፈጠራ ክስ ተከሰው አገዛዙ የሀሰት ምስክሮች አቅርቦ አስመስክሮ የነበረ ቢሆንም ባለፈው አርብ አቶ ማሙሰት አማረ ባቀረቡት የመከላኬአ የሰነድና የሰው ማስረጃ በዕለቱ መስቀል አደባባይ እንዳልነበሩ ይልቁንም ምርጫ ቦርድ በመኢአድ ላይ የወሰደውን አመራሩን በሕገ ወጥ የማባረር እርምጃ በመቃወም በቦርዱ ላይ ያቀረቡትን ክስ ለመከታተል ልደታ ምድብ የፌዴራሉ አንደና ደረጃ ፍርድ ቤት እንደነበሩ ፍርድ ቤቱ በሰነድ ያረጋገጠውንና በዕለቱ አብረዋቸው የነበሩትን አስመስክረዋል። ይሄን የአርብ ምስክርነት የሳው ፍርድ ቤት በዛሬው ቀጠሮ ክሱን አቋርጦ ይፈቱ ቢልም ፖሊስ ሳይፈታ ቀርቷል።

አገዛዙ ፍርድ ቤት የሚፈልገውን ካልወሰነ ቱንም ትዕዛዝ የማያከብር ሲሆንየዛሬዋ ዳኛ ብርቱካን ገላው የሰቱትን ውሳኔ አለመከበር ከዚህ ቀደም በስፋት የሚታወቀውን የዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳን ውሳኔ የሚአስታውስ ሆኗል። ዳና ብርቱካን ሚደቅሳ የቀድሞው የአገዛዙ ባለስልጣን አቶ ስዬ አብርሃን የቀረበውን የሙስና ክስ መዝገብ በመመልከት በጊዜ ቀጠሮ ፖሊስ አለ በቂ ምክንያት የምርመራ ጊዜ እየጠየቀ ተገቢውን ባለመስራቱ የመሀል ዳኛ በሆነችበት አራዳ ምድብ በችሎት ፖሊስ በዋስ ይፈቱ የተባለውን ውሳኔ ባለማክበሩ በነጻ ማሰናበቷ ይታወሳል። ይሁንና ፖሊስ ውሳኔውን ተግባራዊ ላለማድረግ የፍርድ ቤቱን ግቢ በር ለጊዜው ዘግቶ መልሶ ከአለቆቹ ትዕዛዝ ሲደርሰው ከፍርድ ቤቱ እንደወጡ ጥቂት በእግራቸው እንደተጓዙ ሁኔታውን ለመከታተል ካጀባቸው ሕዝብ፣ቤተሰቦችና ጠበቃቸው ነጥሎ መልሶ ማሰሩ ይታወሳል። ዛሬ አቶ ማሙሸት በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሳይፈቱ ከእስር ቤት ወደ እስር ቤት ተዛውረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት በሚያዚያ 14/2007 በሊቢያ በአይ.ሲስ አሸባሪ ቡድን በሊቢአ በግፍ የተገደሉ ወገኖች ላይ ተወሰደውን በመቃወም በተጠራው ሰልፍ ላይ አደባባይ በመገኘቱ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ›› ፈጥረሃል በሚል ተይዞ የቆው ናትናኤል የዓለም ዘውድ የ3 አመት ከ3 ወር እስራት ዛሬ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ የመናገሻ ፍርድ ቤት እንደተፈረደበት ፓርቲው ይፋ አድርጓል።

ከፓርቲው የተገኘው መረጃ እንደሚገልጸው ናትናኤል የኣለም ዘውድ ዛሬ ግንቦት 25ቀን 2007 ዓ.ም የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት የቀረበው ወጣት ናትናኤል የዓለም ዘውድ ላይ የቀረበው ክስ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ መፍጠር›› የሚል ሲሆን አቃቤ ህግ ከፍርዱ በፊት ‹‹ሁከትና ብጥብጡን የፈጠረው ኢትዮጵያውያን ላይ ግድያ የፈፀመውን አይ ኤስ አይ ኤስ ለማውገዝ የተጠራው ሰልፍ ላይ በመሆኑ፣ በተፈጠረው ረብሻ በርካታ ሰዎች የተጎዱ በመሆኑ እና ረብሻውን የፈፀመው አምስተኛው አገራዊ ምርጫ እየተቃረበ ባለበት ወቅት በመሆኑና ይህም አደጋውን ያባብስ የነበር መሆኑን በማገናዘብ›› የሚል የቅጣት ማክበጃ መጨመሩንም ይሄው መረጃ ገልጿል።

በሌላ በኩል በተመሳሳይ ክስ ተከሰው በዚሁ ፍርድ ቤት የቀረቡት ማቲያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤና መሳይ የተባለ ሌላ ወጣት መከላከያ ምስክር ለማቅረብ ለሰኔ 4 ተቀጥረዋል፡፡ እነ ማቲያስ ‹‹ሰልፉ ላይ ሀሰተኛ ወሬ በማውራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተናገሩ በነበረበት ወቅት ወደ ፖሊስ ድንጋይ በመወርወር፣ ህዝቡን አትነሳም ወይ በማለት…›› የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ያስታወሰው ይሄው ፓርቲው መረጃ በጉዳዩ ላይ ዛሬ ይቀርባል ተብሎ የነበረው የቪዲዮ ማስረጃ ባለመቅረቡ በሚቀጥለው ቀጠሮ እንዲቀርብላቸው መጠየቃቸው ታውቋል።

The post ዳኛ ብርቱካን አቶ ማሙሸት አማረን ክሱ ተቋርጦ ይፈቱ ስትል ፖሊስ አለቅም አለ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles