Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

“ሁሉም ሰው ከብሔሩ ወይም ከሰፈሩ ይልቅ ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ ቢሰጥ ሀገራችን ታድጋለች” ዳዊት ፍሬው ኃይሉ

$
0
0
“ሁሉም ሰው ከብሔሩ ወይም ከሰፈሩ ይልቅ ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ ቢሰጥ ሀገራችን ታድጋለች” ዳዊት ፍሬው ኃይሉ

“ሁሉም ሰው ከብሔሩ ወይም ከሰፈሩ ይልቅ ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ ቢሰጥ ሀገራችን ታድጋለች”
ዳዊት ፍሬው ኃይሉ

ትዕግስት ታደለ

የአንጋፋው ድምጻዊ የፍሬው ሀይሉ ልጅ ነው፡፡ የአባታቸውንን ፈለግ ተከትለው ወደ ሙዚቃ ዓለም ከተቀላቀሉ የአንጋፋ ሙዚቀኛ ልጆች መሀከል የተሳካለት የክላርኔት ተጫዋች አንዱ የሆነው ዳዊት ፍሬው ኃይሉ በሙዚቃ መሳሪያ ብቻ የተቀነባበሩ ሁለት ሲዲዎችን ለእድማጭ አቅርኋዋል፡ ፡የሙዚቃ ትምህርቱንም በያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት ተምሯል፡፡ ‹የሰው ልጅ በአብዛኛውን በምሳ ሰዓትም ሆነ ማታ ወደ እንቅልፉ የሚሄደው በሙዚቃ መሳሪያ ብቻ በተቀነባባሩ ሙዚቃዎችን እየሰማ ነው፡፡› የሚለው ዳዊት እስካሁን በሰራሁት ስራ የሚገባኝን ያህል ገቢ አግኝቻለሁ ለማለት ባልችልም ሲዲዬን ገዝቶ ያዳመጠ ሰው ግን ነፍሱን አስደስቷል ብዬ አምናለሁ› ይላል፡፡እኛም የመሿለኪያ አምዳችን እንግዳ አድርገነው እንዲህ አውግቶናል፡፡

ቁም ነገር፡- የደስታና የሐዘንን ስሜት አውጥቶ ከመግለጽና ተቆጣጥሮ ከማለፍ የትኛው ይሻላል?

ዳዊት፡- ሁለቱም ስሜቶች መደበቅ የለባቸውም፤ ግን ደስታ ላይ ገደብ ሊኖረው ይገባል፣ ሐዘንም ላይ እንዲሁ ገደብ ሊኖረው ይገባል፡፡ ሲለቀስም አልቅሰው ሲመጣላቸው ፤ሲደሰቱም መደነስ የሚችለው ደንሶ፣ መጨፈር የሚችለውም ጨፍሮ ጨፍሮ ሲወጣለት ደስ ይላል፡፡ ድብቅ መሆንን አልደግፍም፡፡

ቁም ነገር፡- የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ሲባል ወደ አዕምሮህ ምንድን ነው የሚመጣው?

ዳዊት፡- እኔ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎትን ሳስብ መድረክ መሪዎቹ ላይ ነው የማዝነው፤ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት እናድርግ ይባልና ሰውን አስነስተው ማስቀመጣቸውን እንጂ የሚያዩት በትክክል ደቂቃውን አያዩትም፡፡ የአንድ ደቂቃ የሚሰጠው ሰው እዛ ጋር ቁሞ ሀሳብን ሰብስቦ ጸሎት የሚደረግለትን ስው ለማሰብ ነው፡፡ እነሱ ግን አስራ አምስተኛው ሰኮንድ ላይ ተቀመጡ ይላሉ፤ ያ ይረብሻል፡፡ መድረክ መሪዎቹ ይህን የሚያደርጉት ዝም ብለው ለፎርማሊቲ ነው፡፡ እኔ ግን አዕምሮዬ ውስጥ የሚመጣው ያረፈውን ሰው ነፍስ በገነት ያኑርልኝ የሚለው ነው፡፡

ዳዊት፡- እንግዲህ እኔ ፍቅር ይዞኝ ያውቃል፤ የእውነተኛ ፍቅር ምክንያታዊ ነው፡፡ ወይ በአይንሽ በምታይው ነገር ተማርከሽ አለበለዚያ በተግባር ከምታየው ባህሪ ሊሆን ይችላል፤ በምክንያት ነው ፍቅር የሚዝሽ እንጂ ምክንያታዊ

ሳይሆን ፍቅር አይኖርም፡፡ ፍቅር ፈጣን ሎተሪ አይደል /ሳቅ/

ቁም ነገር፡- የዛሬ መቶ አመት ኢትዮጵያ በአንተ አመለካከት ምን አይት ገጽታ የሚኖራት ይመስልሃል?

ዳዊት፡- የዛሬ መቶ ዓመት በጣም ረጅም ጊዜ ነው፡፡ ምን ትሆናለች?

የሚለውን ሳይሆን የኔን ምኞት ብናገር ይሻለኛል፡፡ ምክንያቱም መገመት ይከብዳል፤ የዛሬ መቶ ዓመት የእኔ ምኞት የአፍሪካ ዋና ከተማ ሳይሆን የዓለም ዋና ከተማ እንድትሆን ነው፡፡ በአይናችን የምናያቸው ነገሮች አሉ የሚካድ ነገር አይደለም፤ ይሄ ነገር በመቶ ሳይሆን በመቶ ሺህ ተባዝቶ ተባዝቶ ሰዉ የሚሰጥ

እንጂ የሚቀበል እንዳይሆን እመኛለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- ፖለቲካና ኮረንቲ በሩቅ ለምንድን ነው የሚባለው?

ዳዊት፡- ይሄ የአስተሳሰብ ጉዳይ ነው፡፡ ያው እንግዲህ ሰው መኖርን ስለሚፈልግ ፖለቲካው ለመጥፊያው ምክንያት እንዳይሆንበት ከመፍራት ነው፡፡ ኤሌክትሪክ የሚሸሸው እንዳያጠፋን ነው አይደል፤ ፖለቲካም ለመጥፊያችን ምክንያት እንዳይሆን ነው፡፡

ቁም ነገር፡- ሙዚቃ ባይኖር ኖሮ የሰው ልጅ ህይወት ምን ይመስል ነበር?

ዳዊት፡- በሙዚቃ እኮ ነው ስሜት የሚገለፀው፤ ዓለም ጎዶሎ የምትሆን ነውየሚመስለኝ፡፡ሙዚቃባይኖርሰውደስሲለውሲያዝንስሜቱንየሚገልጽበት ያጣል፡፡ በንግግር ከሚነገረው መልዕክት እኮ በዜማ የሚሰማው መልዕክት ብቃቱ የትየለሌ ነው፡፡ አሁን የጥላሁን ‹‹ዳግመኛ ቢፈጥረው›› ዘፈን ስትሰሚ ሰው ደጋግሞ በንግግር ከሚነግርሽ ሁለቷን የጥላሁንን ስንኝ

‹‹ሞት እንኳን ጨክኖ ወስዶ ከሚያስቀረው››
‹‹ምናለ ደጋጉን ዳግመኛ ቢፈጥረው›› የሚለውን በዜማ ብትሰሚ

ትልቅ ጉልበት አለው፡፡ ሙዚቃ ሁሉ ነገራችን ውስጥ አለ፡፡ ሲሸለል ሲፎከር ሁሉ ሙዚቃ አለ፤ ስለዚህ ሙዚቃ ባይኖር ብዙ ነገር ይጎልብናል፡፡ ሙዚቃ የዓለም የልብ ምት ነች፡፡

ቁም ነገር፡- በሰው በሀገራት ስም የሚጠሩ የከተማችን ሰፈሮች የትኞቹን ታውቃለህ?
ዳዊት፡- ሪቼ የሚባል አለ አይደል? ሪቼ የሰው ሀገር ስም ነው እንዴ? እኔ ምን እንደሆነም አላውቅም፤ የሰው ሀገር ስም ይመስላል /ሳቅ/፤ ካሳንችስ ምንድን ነው? ምናልባት ሩዋንዳ የሚለው በሰው ሀገር ስም ነው መሰለኝ /እ…. እንደማሰብ / እንግዲህ የሩዋንዳው ብቻ ነው የመጣልኝ፡፡

ቁም ነገር፡- መጋኛ ምንድን ነው?

ዳዊት፡- መጋኛ የሰይጣን ታናሽ ወንድም ይመስለኛል፡፡ በፊት ጠዋት ላይ ሆዴን ይቆርጠኝ ነበረ፤ ስጠይቅ በር ከፍተህ ስለወጣህ ነው፡፡ መጋኛ መቶህ ነው ይሉኛል፡፡ ቁርጠት ነው በሽታ ያመጣብኝ፣ በሽታ ደግሞ ሰይጣን ነው፡፡ ስለዚህ

መጋኛ የሰይጣን ታናሽ ወንድም ነው ወይም ደግሞ የሰፈሩ ልጅ /ሣቅ/ ፡፡

ቁም ነገር፡- ስዕል ፣ ሙዚቃ፣ ቴአትር እና ፊልም ከነዚህ ላንተ የትኛው ነው ህይወትን በደንብ የሚገልፅልህ? ለምን?

ዳዊት፡- ሙዚቃ ጉልበት አለው፡፡ እኔ ሙዚቀኛ ስሆንኩ አይደለም፤ አንዳንድ ጊዜ የኛ ያልሆኑ ሙዚቃዎችን ከፍቼ ሳዳምጥ የማላውቀው ቦታ ይዞኝ ይሄዳል ፣ የሚፈጥረው ስሜት አለው፡፡ ለዚህ ነው ሙዚቃ የአለም ቋንቋ ነው የሚባለው፤ አሁን ለምሳሌ የቻይና ሙዚቃ ብንሰማው የማናውቀውን ዓለም ነው የሚያሳየን፡፡ ቋንቋውን የማናውቀውን ፊልም ወይም ቴአትር ብናይ ግን ዝም ብለን ምስሉን፣ እንቀስቃሴውን እናያለን እንጂ አይገባንም፡፡ ሙዚቃ ግን ኖታ ነው፡፡ ስትሰሚው ሌላ ዓለም ይዞሽ

ይሄዳል፡፡ቁም ነገር፡- ጫማው ከጠበበው ሰው እና ሽንቱ ከወጠረው ሰው የትኛው ይሻላል?

ዳዊት፡- እንዴ ጫማው የጠበበው ሰው ነዋ! የሚሻለው /ሣቅ/ ፤ጫማው የጠበበው ሰው ምን ቢጠበውም እግሩ አይቆረጥም ምንም አይሆንም ፡፡ሽንቱ የወጠረው ሰው ግን መንገድ ላይ ቢሆን የወጠረው ምን እንደሚፈጠር ማወቅ

አያዳግትም፡፡ በተፈጥሮ መያዝና በሰው ሰራሽ መያዝ ምን አንድ አደረገው /ሣቅ/፡፡

ቁም ነገር፡- ሀገራችን ከድህነት በቀላሉ መላቀቅ ያልቻለችው ለምንድን ይመስልሃል?

ዳዊት፡- ይህ እንግዲህ ሰፊ ነው ጉዳዩ ፤አንደኛ መናበብ ካለመቻል ነው፡ ፡ ሁሉም ሰው ከብሔሩ ወይም ከሰፈሩ ይልቅ ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ ቢሰጥ

ሀገራችን ታድጋለች፡፡ ችግሮችና ቢኖሩም ሁሌም ማስቀደም ያለብን ኢትዮጵያን ነው፡

፡ በዚህ ምክንያት ይመስለኛል፡፡

ቁም ነገር፡- በአሁኑ ወቅት የወጣቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ምንድን ነው ትላለህ?

ዳዊት፡- ለስራ የተዘጋጀ ስነ ልቦና አለመኖር ይመስለኛል፤ ለስራ ዝግጁ

አለመሆን ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ባህላችን ሆኖ የበታችነትን እንጠላለን፤ አንድ ሰው

ራሱንበአካዳሚዕውቀትሳያዳብርሥራአጣሁብሎቢያወራምንይገርማል፡፡ ለስራ

ዝግጁ አለመሆን ይመስለኛል አንገብጋቢው ነገር፡፡

ቁም ነገር፡- ነገረኛ ጎረቤት ምን አይነት ነው?

ዳዊት ፡- ምነሻ ሃሳብ የሚፈልግ ነዋ ! /ሳቅ../ ሙዚቃ እንኳን ብትከፍቺ

ከቀኑ አምስት ሰዓት ላይ አረ ድምጹን ቀንሱ እንተኛበት የሚል! ያው አንዳንዴ

ትደበሪበታለሽ! የሚለውን እየሰማሽ! እንደዚህ ነው ከልምዴ የማቀው፡፡

ቁምነገር ፡- አመሰግናለሁ፡፡

The post “ሁሉም ሰው ከብሔሩ ወይም ከሰፈሩ ይልቅ ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ ቢሰጥ ሀገራችን ታድጋለች” ዳዊት ፍሬው ኃይሉ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles