ነቢዩ ሲራክ
በሳውዲ ጅዳ ሪያድና በተለያዩ ከተሞች ህገ ወጥ የተባሉትን የውጭ ዜጎች የማጥራቱ ዘመቻ ደመቅ ብሎ ባይሰማም በሂደት ላይ ነው ። በያዝነው ሳምንት ጅዳ ውስጥ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች በተደረገ ፍተሻ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህጋዊ መኖርያ ፍቃድ ያላቸው እህቶችና ወንድሞች ቤት ለቤት በሚደረገው አሰሳ ተይዘዋል ።
በአሰሳ ፍተሻው ተይዘው በወህኒ የሚገኙት እንዳደረ ሱኝ መረጃ ከሆነ አያያዛቸው መኖርያ ፈቃድ ከሌላቸው ጋር በመገኘታቸውን ጨምሮ በአንድ ህንጻ ውስጥ ህገወጦች ተገኙ ተብሎና ሌላም ሌላ ምክንያቶች የተሰጣቸውን መሆኑን መረጃ አድርሰውኛል። በተለይም ህጋዎ መኖርያ ፍቃድ እያላቸው ከነ ልጅ ቤተሰቦቻቸው የተያዙት ወገኖች ቢቻል የመንግስት ተወካዮች ጉዳዩን ከአሰሪዎቻቸውና ከሳውዲ መንግስት ሃላፊዎች ጋር ተነጋግረው በዋስ እንዲዎጡ እንዲረዷቸው ተማጽነዋል !
እኒህ ወገኖች እያለቀሱ ባስተላለፉት መልዕክት እንዲህ የሚል ይገኝበታል …” … የረባ ልብስ ሳንለብስ ቤተ ተሰብሮ ተይዘን ፣ በባዷችን ወደ ሀገር ግቡ እየተባልን ነው ! ለአመ ታት የሰበሰብነውን ቁሳቁስ ፣ ሀብት ንብረት ሳንሰበስብ ቤተሰቦቻችን በትነን ወደ ሀገር መሸኘት የለብንም ፣ የኢትዮ ጵያ መንግስት ተወካዮች ከአሰሪዎቻችንና ከመንግስት ጋር ተነጋግረው ያስፈቱን ፣ ማስፈታት ካልቻሉ ንብረታችን ሰብስበን የምንሄድበት መንገድ መንግስታችን ያመቻችልን ዘንድ ድምጻችን አሰማልን !” ብለውኛል ! መልዕክቱ ለሚመለከታችሁ ሁሉ ይድረስ !
እነሱ ስራቸውን እየሰሩ ነው ፣ አቁሙ አይባሉም ፣ እነማን እንደሆኑ እያወቅን ፍን ደጋግመን ተዘናጋን ! … ደጋግመን አበሳን ለመክፈል ተገደድን ፣ እንጠንቀቅ ፣ ከመጭው አደጋ ለመዳን !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ግንቦት 23 ቀን 2007 ዓም
The post (የሳዑዲ ጉዳይ) ስራቸውን እየሰሩ ነው፣ እኛ ተዘናግተናል ! * በሳውዲ እስር ቤት የኢትዮጵያውያን መልዕክት appeared first on Zehabesha Amharic.