የኢህአዴግ ባለስልጣኖች ቦንጋ አካባቢ የነበረ የተፈጥሮ ጫካ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱበት ነው በሚል ምክንያት እንዲቃጠል ማድረጋቸውን የትህዴን ድምጽ ዘገበ::
የትህዴን ምንጭ የዜና ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው በደቡብ ክልል ቦንጋ አካባቢ የሚገኝ ሰፊ የተፈጥሮ ጫካ በአካባቢው ህዝብ ለዘመናት ጠብቆት የኖረ ሃብት ሲሆን የገዢውን ስርአት በመቃወም እየታገሉ ያሉት ተቃዋሚዎች የሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ነው ብለው ስጋት ላይ የወደቁት የስርአቱ ካድሬዎች እሳት ለኩሰው እንዲቃጠል ማድረጋቸውና ይህን እኩይ ተግባር የታዘበው የአካካባቢው ህዝብም በስርአቱ ላይ ጠንካራ ተቃውሞ እንዳስነሳ ለማወቅ ተችሏል።
የአካባቢው ህዝብ እየተቃዎመ በነበረበት ሰዓት እንደገለፀው በአፋችሁ ልማት አልሙ፤ ድህነት አጥፉ እያላችሁ በተግባር ግን መተኪያ የሌላቸውን የተፈጥሮ ሃብቶችን እያቃጠላችሁ ነው በማለት ሃይለኛ ተቃውሞ ማንሳታቸውን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
The post ቦንጋ አካባቢ የሚገኝ የተፈጥሮ ጫካ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱበት ነው በሚል ምክንያት በገዢው መንግስት እንዲቃጠል ተደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.