የወያኔ የመከላከያን ከፍተኛ በጀት ለትግራይ ክልል እንደ ተጨማሪ ልዩ በጀት አድርጎ ይጠቀማል፡፡ በሰራዊቱ ውስጥ ዘረኛ መድሎን ይፈጽማል፡፡ የትግራይ ሪፑብሊክ ምስረታ ህልሙንም አልረሳም፡፡
በአሁኑ ጊዜ 85% የሚሆነው የመከላከያ ሠራዊት ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ክልል ሠፍሮ ይገኛል፣ ይህንንም አጋጣሚ
በመጠቀም ፦
- ለሠራዊቱ ቀለብ አቅርቦት ያለ ጨራታ ከአዛዧች ጋር በመመሳጣር፣ የትግራይ ሰዎች ብቻ እንዲያቀርቡ ተደርጓል። አቅራቢ ከሆኑትም መሀል አቶ ጉዕሺ፣ ወ/ሮ ዘውዴ ፣ አቶ ስብሀት ፣ ወ/ሮ አዲስ፣ አቶ ገብረስላሴ፣ አቶ ሃጎስ በመባል የታወቁ ሰዎች ይገኙበታል፡፡ ለሰራዊቱ የሚያቀርቡትም አትክልት ፣ በርበሬ፣ የወጥ እህሎችና ሥጋ፣ ዱቄት ፣ ዘይት ወዘተ. መሆኑ ታውቋል። አቅራቢዎቹ የትግራይ ሰዎች አቅርቦቱም ከትግራይ ክልል እንዲገዛ ተደርጓል።
- ሰራዊቱ በከፍተኛ ቁጥር ትግራይ ላይ በመስፈሩ ብቻ ምን ያህል የክልሉን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንደጠቀመ አንድ ምሳሌ እንስጥ፡፡ የወያኔ አንድ ወታደር በቀን 8 ዳቦ ይበላል፡፡ ይህም ማለት ወደ መቶ ሽህና ከእዛም በላይ የሚቆጠረው በትግራይ ውስጥ የሰፈረው ሰራዊት በአማካይ በትንሹ በቀን 800000 ዳቦ ያስፈልገዋል ማለት ነው፡፡ በቀን ይህን ያህል ዳቦ የማቅረብ ስራ ብቻ ምን ያህል ኢንቨስትመንት የሚያስፈልገው እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ ወያኔ ሰራዊቱ በሆዱ እንዳይከፋበት ካለው ፍላጎት ለምግብ ከፍተኛ ወጪ ያደርጋል፡፡ ካዳቦ ውጭም በእዚሁ በትግራይ ክልል ውስጥ ሰራዊቱን መሰረት በማድረግ የሚመረተው የተለያየ የምግብ ውጤትና ሽያጭ በገንዝብ ሲለካ በብዙ መቶ ሚሊዮኖች ብር የሚቆጠር ይሆናል፡፡
- ሌሎች ከቀለብ ውጭ በመደበኛ በጀት የሚገዙ አላቂና ቋሚ እቃዎች፣ የኤሌትሪክ ማሽነሪዎች ፣ የጽህፈት ዕቃዎች፣ ማንኛውም የቢሮና የመኖሪያ ቤት መገልገያ ዕቃዎችና የስልጠና መገልገያ ዕቃዎች፣ በሙሉ ከትግራይ ክልል ብቻ እንዲገዙ በመመሪያ ታዟል። ሌላው ቀርቶ ጠቅላላ የመከላከያ ወታደራዊ አገልግሎትና ሌሎች ጨርቃ ጨርቆች በሙሉ፣ ያለ ጨረታ አድዋ ከሚገኘው ከአልሜዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ብቻ እንዲገዛ ተወስኖ፣ ተግባራዊ ከሆነ ብዙ አመታት አስቆጥሯል። ይህ ሰራዊት በአመት ሁለት ግዜ የደንብ ልብሱን እንዲቀይር ከወጣው መመሪያ ጋር ተደምሮ እነአልሜዳ ምን ያህል ገንዝብ ከመከላከያ ሚኒስቴር እንደሚዘርፉ ማየት ይቻላል፡፡
- በኢትዮ – ኤርትራ ጦርነት ጊዜ የጦርነቱን አጋጣሚ በመጠቀም 50000 (ሃምሳ ሽህ ) የትግራይ ሚሊሻ በጦርነቱ ትሳትፏል፣ ጦርነቱ ከቀጠለም ይዋጋሉ፣ በሚል ምክንያት ሥራ ላይ ሣይገኙ በየቤታቸው ተቀምጠው፣ በመከላከያ የደሞዝ መክፈያ ሰነድ፣ ከሰኔ 1991 ጀምሮ እስከ ሰኔ 1993 ዓ.ም ድረስ በተራ በወታደር ማዕረግ በወር 500.00 (አምስት መቶ ) ብር ተክፍሏቸዋል። ይህ አሰራር መቋረጡን ማወቅ የቻልንበት ማስረጃ የለም፡፡
- በግንባር አካባቢ ወታደራዊ ልምምድ ሲደረግ ልምምዱ የገበሬዎች ሰብል አውድሟል፣ የግጦሽ ሳራቸውን ጎድቷል፣ አትክልታቸውን ሰባብሯል፣ በሚል ሰበብ የልተመጣጠነ ከፍተኛ ዋጋ ይከፈላል። ለምሳሌ አዲግራት ደንጎል አካባቢ፣ በሁለት ሄክታር መሬት ላይ የተዘራ ገብስ ላይ ‹‹የተወሰነ የእግረኛ ልምምድ ተደርጎበት ወደመ›› ተብሎ የግብርና ባለሙያዎች መጥተው ‹‹ከ30-40% ምርት ሊቀንስ ይችላል›› ብለው ሄዱ። ለሰዎቹ ግን የተሰጠው የካሳ ክፍያ 780000 (ሰባት መቶ ሰማኒይ ሺ) ብር ነበር። ይህ ገንዝብ ግን በሙሉ በተራው ገበሬ እጅ የገባ ሳይሆን ሰራዊቱን በዋንኛነት የሚቆጣጠሩትን የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ከፍተኛ መኮንኖች ኪስ እንዳደለበ ይታወቃል፡፡
- ሠራዊቱ በትግራይ ከተሞችና ገጠሮች በብዛት ሰፍሯል። በሠፈረባቸው አካባቢዎች ሁሉ ለመኖሪያ፣ ለቢሮና ለመጋዘኖች፣ ቤቶችን በውድ ዋጋ ተከራይቶ ይጠቀማል። ሰራዊቱ በሚኖርባቸው ቤቶች፣ ካምፖች፣ በሚገለገልባቸው ቢሮዎች ውስጥ ለቤት ሰራተኛነት፣ ለጽዳት ሰራተኛነትና ለሌሎችም ስራዎች የሚቀጠረው የአካባቢው ተወላጅ ቁጥር በትግራይ የስራ አጡን ቁጥር በመቀነስ ትልቅ ሚና አለው፡፡ ሰፊ የስራ መስክ ሆኗል፡፡
- ሰራዊቱ በየወሩ ደሞዙን ተቀብሎ መልሶ የሚያወድመው በእዚሁ ክልል ውስጥ ስለሆነ ከሰራዊቱ የመዝናኛ ፍላጎቶች ጋር የተያያዙ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ ተጠቃሚዎች የሆኑበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ እነዚህ ደግሞ በዋንኛነት በወያኔ ወይም በወያኔ አባላት የተያዙ ናቸው፡፡
- ወያኔዎች የወታደሩን ነፃ ጉልበት ተጠቅመው ሠራዊቱን በአፈርን ውሃ ዕቀባ፣ በእርሻና በእርከን ሥራ በአረምና በአጨዳ ሥራ ይጠቀሙበታል።
- የመከላከያን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ባለሙያዎች ክልሉ እንደፈለገ በነፃ ይጠቀምባቸዋል። ይህንን በመጠቀም በርካታ መንገዳች ተሰርተዋል። ግድቦች ተገንብተዋል።
- ዘረኛነትንና አድሎን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለው በደል ይፈጸማል። ከሰራዊቱ በተለያዩ ምክንያት የሚቀነሱ፣ በአካል መጉደል ወይም በሌሎች ምክንያቶች ሊሆን ይችላል፣ የሰራዊቱ አባላት መሃከል በዘር ላይ የተመሰረተ አድሎ ይፈጸማል፡፡
ከሌሎች ብሄረሰቦች የመጡ የሰራዊቱ አባላት የሚሰጣቸው ገንዝብ ከሚሰናበቱበት ግንባር ተነስተው ከሚኖሩበት ክልል የማያደርስ ነው፡፡ ለትግራይ ተወላጆች የሰራዊቱ ተቀናሾች ከመከላከያ ሚኒሰቴር በጀት ወጪ እየተደረገ የሚሰጠው ካሳ በአስር ሽዎች ብር የሚቆጠር ብቻ ሳይሆን፣ እነዚህ የሰራዊቱ አባላት በተለያዩ ስራዎች መቀጠል እንዲችሉ የስልጠና የብድር ሌሎችም አስፈላጊ ግብአቶች ይሟሉላቸዋል፡፡ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ማብቂያ ከሰራዊቱ በተለያዩ ምክንያቶች የተቀነሱ የሌሎች ብሄረሰብ አባላት የተሰጣቸው ገንዝብ በግለሰብ ደረጃ ከ2000 እስከ 3000 ብር የሚደርስ ብቻ ነበር፡፡ ለትግራይ ተወላጆች ግን ከ30 እስከ 40 ሽህ ብር ነበር፡፡ ሌሎቹ ከሰራዊቱ ከተበተኑ በኋላ ምንም አይነት የመቋቋሚ ድጋፍ ያልተደረገላቸው ሲሆን የትግራይ ብሄረሰብ ለሆኑ የሰራዊቱ አባላት ግን የሚደረገው አጠቃላይ የማቋቋሚ ድጋፍ በብዙ ሚሊዮን ብሮች በሚሰላ ሃብት የተደገፈ ነው፡፡ ይህን አሳዛኝ ዘረኛ አድሎ ወያኔ የሚፈጸመው ወያኔ እንደሚለው 70 ሽህ ዜጎች ሳይሆን 98ሽ ዜጎች ትግራይ ምድር ድረስ ተጉዘው መለስ ዜናዊ ‹‹ለወላይታው ምኑ ነው›› ያለውን የአክሱም ሃውልት ምድር ለመከላከል በረገፉበት ዘግናኝ ጦርነት ማግስት ነበር፡፡ እግረ መንገዳችንን በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ከሞቱት መሃል አብዛኛው አማሮች ሲሆኑ ከስምንት ሽህ በላይ የሚሆኑ የአፋር ተወላጆች በእዚህ ጦርነት ውድ ህይወታቸውን መክፈላቸውን ማወቅ ችለናል፡፡ አጅግ በርካታ የሆኑ የአካል ጉዳተኞችም ያለምንም ድጋፍ በየክልሎቹ ተበትነው፤ በጦርነት የተቆረጠ እግራቸውንና እጃቸውን መለመኛ አድርገው የመከራ ኑሮአቸውን ይገፋሉ፡፡ በሰዎች መታወቂያ ላይ ሳይቀር የዜጎችን ዘር ለመጻፍ ድፍረቱ ያለው አገዛዝና በሆነ ባለሆነ ስለብሄራዊ ተዋጽኦ ዲስኩር መስጠት የሚቀናቸው የወያኔ ባለስልጣናት ለምን በየጦርነቱ አውድማ የሚማግዱተን የህዝብ ቁጥርና የሟቾቹንና የተጎጂዎችን ብሄራዊ ተዋጽኦ ሊነግሩን
እንደማይፈቅዱ ከእዚህ መረጃ መገንዘብ ይቻላል ፡፡
ለማጠቃለል፡ ወያኔ የኢትዮ – ኤርትራ ፍጥቻ እንዲቀጥል የሚያደርገው፣ አብዛኛውን የሃገሪቱን የመከላከያ ሃይል በቀላሉ ሊቆጣጠረው ከሚችልበት አካባቢ ለማስቀመጥ እድል እንደሚሰጠው ስለሚያውቅ ነው፡፡ የኢትዮ-ኤርትራ ፍጥጫ እስከቀጠለ ድረስ የሃገሪቱ መከላከያ ሃይል ቁጥሩም በጀቱም አይቀንስም፡፡ የሚሰፍረውም በትግራይ ውስጥ ይሆናል፡፡ ይሀ ማለት ከአመት አመት የመከላከያ በጀት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከላይ በጠቀስናቸው መንገዶች በትግራይ ክልል የሚደረገውን የልማት ስራ አጋዥ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ይህንን ጠባብ፣ ዘረኛና ዘራፊ የሆነ የወያኔ ቡድን ፍላጎት እስካሟላ ድረስ፣ ኢትዮጵያ ከድህነቷ ጋር የማይመጣጠን ትልቅ የመከላከያ ሃይል ተሸክማ ኖረች አልኖረች ወያኔን አያሳስበውም፡፡ ወያኔ ሌላው የኢትዮ-ኤርትራ ፍጥጫ እንዲቀጥል የሚፈልግበት ምክንያት፣ ወደፊት ወያኔ በተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሊፈጽም ላሰበው ወንጀል የመከላከያ ሃይሉን የጦር መሳሪያዎች በቀላሉ መጠቀሚያ ለማድርግ በሚያመች ቦታ ማከማቸት ስላስቻለው ነው፡፡ ዛሬ የሃገሪቱ የመከላከያ ሃይል፣ አየር ሃይሉ በሙሉ፣ ሜካናይዝድ ብርጌዱ ከነዘመናዊ ታንኮቹና መድፎቹ፣ በሰራዊት ውስጥ አለ የተባለው ሌላ ዘመናዊ መሳሪያ በሙሉ የሚገኘው በትግራይ ክልል ነው፡፡
The post የወያኔ የመከላከያ ከፍተኛ በጀት appeared first on Zehabesha Amharic.