አምዶም ገብረሥላሴ ከትግራይ እንደዘገበው
በ11 / 09 / 2007 ዓ/ም በዓፅቢ ወንበርታ ወረዳ በቅስቀሳ የነበሩ ኣባሎቻችን ላይ በገዢው ፓርቲ በምስራቃዊ ዞን ኣመራሮች ትእዛዝና መሪነት የተፈፀመው ኣሰቃቂ ድብደባ 9 ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።በቅስቀሳ ላይ የነበሩ ኣባሎቻች የምስራቃዊ ዞን የፕሮፖጋንዳ ሃላፊ የሆነው ኣቶ ደሳለኝ ተፈራ መጥቶ ከኣፅቢና ሌሎች ኣካባቢዎች ወጣቶች ኣደራጅቶ ድብደባ እስኪፈፅም ቅስቀሳው ሰለማዊ ነበር።ኣባሎቻች በኣፅቢና ደራ ከተሞች ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍና ተቀባይነት ያገኙና ሲበረታቱ ነበር።በእጅ የሚያዝ ማይክሮፎንና በመኪና የተጫነ ሜጋፎን ኣድርገው በሰላምይቀሰቅሱ ነበር። የህዝቡ የለውጥ ፍላጎት ለዓረና መድረካባላት ከፍተኛ መነሳሳት ሲፈጥር ለምስራቃዊ ዞንና ለወረዳው ኣስተዳዳሪዎች ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረ ነበር።
የዚህ ድንጋጤኣቸው መገለጫም ተደባዳቢ ሰዎች በማደራጀት በ9 ኣባሎቻችንና በሜጋፎን ጭና ስትንቀሳቀስ ይንበረችውን መኪና የድንጋይ ናዳ በማውረድ በሰውና በመኪናዋ ኣካል ከፍተኛ ጉዳት ኣድርሰዋል።
በዚህ መሰረትም 8 ኣባሎቻችን ከፍትኛ ጉዳት የደረሳቸው ሲሆን የመኪናዋ መስተዋትና ሌሎች ኣካልዋ የመሰበር ጉዳት ኣድርሰዋል።
ጉዳት የደረሳቸው ኣባሎቻን
1) ሕድሮም ሃይለስላሴ ከባድ ጉዳት የደረሰው ከኣፅቢ ጤና ጣብያ ሪፈር ትብሎ፣ በውቕሮ ሆስፒታልም ሪፈር ተብሎ መቐለ በህክምና ያለው..
2) ወልደ ኣብራሃ ገብረመድሂን ከባድ ጉዳት የደረሰው ከኣፅቢ ጤና ጣብያ ሪፈር ትብሎ፣ በውቕሮ ሆስፒታል በህክምና ያለው
3) ወልደገብርኤል ሃይሉ የፌደራል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ከባድ ጉዳት የደረሰው ከኣፅቢ ጤና ጣብያ ሪፈር ትብሎ በውቕሮ ሆስፒታል በህክምና ያለ.
4 ) ነጋሲ ክንፉ ከባድ ጉዳት የደረሰው ከኣፅቢ ጤና ጣብያ ሪፈር ትብሎ፣ በውቕሮ ሆስፒታል በህክምና ያለ
5) ካሕሳይ ተስፋይ ጉዳት የደረሰው ከኣፅቢ ጤና ጣብያ እየታከመ ያለው
6) ሓጎስ ገብረስላሴ የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ጉዳት የደረሰው ኣፅቢ ጤና ጣብያ እየታከመ ያለው.
7) ሙሉ ኣባይ የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ጉዳት የደረሰው ኣፅቢ ጤና ጣብያ እየታከመ ያለው.
8) ኣበራ ኣስገዶም የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ጉዳት የደረሰው ኣፅቢ ጤና ጣብያ እየታከመ ያለው
9) ሃይለማርያም ግደይ ጉዳት የደረሰው ኣፅቢ ጤና ጣብያ እየታከመ ያለው ናቸው።
በመኪና ሁነው ቅስቀሳ ሲያካሂዱ የነበሩ እነ ሃፍታይ ገብረሩፋኤል እንደምንም በሹፌሩ ብቃት ከጉዳት ድነዋል። የዚህ ኣረመኒያዊ ተግባር ኣደራጅ የነበረው ኣተ ደሳለኝ ተፈራ በዓዲግራት፣ በኣብረሃ ወ ኣፅበሃ፣ በኣፅቢና ሓወዜን የደረሱብን ድብደባዎች የመራ ኣምባገነንና ወንጀለኛ ሰው ነው።
ይህ ከነ ለገሰ ኣስፋው የማይተናነስ ኣምባገነን ሰው ከድርጅቱ የተሰጠው ትእዛዝ በመፈፀም የኣባሎቻችን ደም እንደ ጎርፍ ያፈሰሰ ወንጀለኛ ነው። ህወሓት በመላ ትግራይ በኣባሎቻችን ላይ እያደረሰች ያለው ግፍ ፍፁም የኣንባገነን ስርዓት መገለጫና ጭፍጨፋ ነው።
በታሕታይ ቖራሮ በመምህር ገብረስላሴ፣ ኣቶ ደመቀ ገብረስላሴና በ4 የምርጫ ታዛቢዎቻችን ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመዋል።
በኮረምም ከምርጫና ዓረና-መድረክበተያያዘ ትናንት12/09/ 07 ዓ/ም ኣንድ ምልሻ በጥይት ሂወቱ ኣልፈዋል።
በኣላማጣ ባላ በተባለች ቀበሌ ህዝቡ በሙሉ”ዓረናነን” በማለቱ በስብሰባ ላይ ከወረዳ የተላከች ካድሬ “ዓረና ከመረጣቹ ወደ ጦርነት እንገባለን ለልጆቻቹ ስትሉ ህወሓት ምረጡ” ብለዋል።
የኣላማጣ ምርጫ ታዛቢዎቻችን በወረዳ ኣስተዳዳሪዎች የታዛቢነት መታወቅያ ተቀምተው ባዶ እጃቸው እንዲቀሩ ተደርገዋል፣ በውቕሮና ኣግበ ምርጫ ክልል የታዛቢነት ካርዱ “ራሳችን ነው የምናከፋፍለው” ብለው የምርጫ ኣስፈፃሚዎች ከልክለውናል፣ በመላ ትግራይ ያሉ ታዛቢዎቻችን ከታዛቢነት እንዲወጡ በፖሊስ፣ ምልሻ፣ ካድሬዎች፣ የሃይማኖት ኣባቶች፣ ቤተሰቦች ከፍተኛ ጫናና እንግልት እየደረሰባቸው ይገኛሉ።
ታዛቢዎቻችን ከፍተኛ ጫና በመ ፍጠር ከታዛቢነት እንዲያገሉና “ያለፍላጎታችን ነው ታዛቢ እንድንሆን የተደረግነው” ብላቹ ክሰሱ” እየትባሉ የክስ ደብዳቤ እንዱያስገቡእየተደረገ ነው። ብለው ብለው በስም መመሳሰል ወይም በስም ሞክሼነትም እስከ እስራት የደርሰ መንገላታት እያደረሱባቸው ይገኛሉ።
የዘንድሮ ምርጫ ዓረና-መድረክ ከፍተኛ ዝግጅት ያደረገበት እንደመሆኑ በተወዳደርንባቸው የምርጫ ክልሎች በቂ ታዛቢዎች ኣቅርበናል። ገዢው ፓርቲ ይህ የፈጠረበት ድንጋጤ ለመከላከል ከፍተኛ የወንጀል ተግባራት በመፈፀም ይገኛል።
የህዝባችን ድጋፍ ደግሞ እጅግ የሚያኮራ ነው። የመቐለ ህዝብ እንደ ምሳሌ ብንወስድ ድምፁ ለዓረና-መድረክ እንደሚሰጥ በተለያየ መንገድ እየገለፀልን ገኛል።
ህወሓት በትግራይ ህዝብ ፍፁም ተቀባይነትዋ ተማጦ ጠፍተዋል። ህወሓትም በትግራይ ህዝብ የነበራት እምነት ጨርሳለች። ለዚህ ነው ከወር በፊት በምርጫ መሰረት ኣድርጎ ይሰጥ የነበረው ስልጠና ምርቃት የተገኙ ኣቶ ሓሰን ሹፋው “ህወሓትና መንግስት በቸኛው እምነት የጣለው በፖሊስ ብቻ ነው፤ ህልውናችንም ጥፋታችንም በናንተው ነው።..” ብለው ንግግር ያሰሙት።
የኣፅቢ ወንበርታ ፖሊስም ይህ ጭፍጨፋ በኣባሎቻችን ሲደርስባቸው እያየ እንዳላየ የሆነው ከሓሰን ሽፋ ንግ ግር የተያያዘ ነው።
የዘንድሮ ካርድ በደም የጨቀየች እያደረጋት ያለው ገዢው ፓርቲ ኢህኣዴግ ለራሱ፣ ለኛም ለሃገራችንም ጥቅም ብሎ ከጀመረው የጥፋት መንገድ ሊመለስ ይገባል። ምርጫው ሰለማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲያልፍ በዓረና-መድረክና ኣባላቱ መስዋእትነት እየከፈልንም ቢሆን የተቻለን ጥረት እናደግርጋለን።
ካርዷ ከደም የፀዳች ለማድረግ የተቻለንን ጥረት እናድረግ።
ነፃነታችን በእጃችንነው..!
The post በደም የጨቀየች ካርድ! * በትግራይ የአረና-መድረክ አባላትና የምርጫ ተወዳዳሪዎች ደም ፈሰሰ appeared first on Zehabesha Amharic.