Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: ከማንቸስተር ሲቲ ማን ለቅቆ ማን ይቀጥላል?

$
0
0

Man. City
በቀጣዩ የውድድር ዘመን ከኤቲሃድ የሚለቅቁት እና ወደ ክለቡ የሚገቡት እነማን ይሆኑ?
ዊሎ ካባሌሮ (ግብ ጠባቂ)
ዕድሜ፡- 33
ፈረመ፡- 2014 (6 ሜ.ፓ)
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 2
ከባሌሮን ያስፈረሙት ፔሌግሪኒ ናቸው፡፡ በማላጋ አብሯቸው የሰራው ግብ ጠባቂ የጆ ሃርት ተጠባባቂ እንዲሆን ቡድኑን የተቀላቀለው በቺሊያዊው ይሁንታ ነው፡፡ አርጀንቲናዊው ከጉዳት ርቆ በበርካታ ጨዋታዎች ላይ የመሰለፍ ዕድሉ ውስን ነው፡፡ በመሆኑም የሃርት ተጠባባቂ ለመሆን የሚመጥን ይመስላል፡፡
ብይን፡- ለተጨማሪ የውድድር ዘመን በክለቡ ሊቆይ ይችላል፡፡
ይህን ያውቃሉ፡- ካባሌሮ ተሰልፎ በተጫወተባቸው ሁለት ግጥሚያዎች ላይ (ሰንደርላንድ እና ሃል) በእያንዳንዳቸው ሁለት ጎሎች ተቆጥረውበታል፡፡ እንደዚያም ሆኖ ቡድኑ ሁለቱን ጨዋታዎች አሸንፏል፡፡
ጆ ሃርት (ግብ ጠባቂ)
ዕድሜ፡- 27
ፈረመ፡- 2006 (500 ሺ.ፓ)
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 30
ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በተደረገው ጨዋታ ላይ በምርጥ ብቃቱ ላይ አልነበረም፡፡ ነገር ግን የእንግሊዙ ግብ ጠባቂ ሌሎቹ በዙሪያው ያሉ ተጨዋቾች ተዳክመው በታዩበት ወቅት እንኳን አቋሙን ጠብቆ ዘልቋል፡፡ በመጪው ክረምት ሲቲ ቡድኑን እንደ አዲስ የሚያዋቅር ከሆነ ያለምንም ጥርጥር ሃርት የቡድኑ ዋነኛ አካል ይሆናል፡፡
ብይን፡- በእርግጠኝነት ይቆያል
ይህን ያውቃሉ?:- በዚህ የውድድር ዘመን ሃርት ከየትኛውም የሲቲ ተጨዋች በላይ በፕሪሚየር ሊግ በርካታ ደቂቃዎችን (2700) ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡
ጋኤል ክሊቺ
(የመስመር ተከላካይ)
ዕድሜ፡- 29
ፈረመ፡- 2011 (7 ሚ.ፓ)
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 23
ጎል፡- 1
በአንድ ወቅት ጥሩ መንፈስ ያለው ጎበዝ ተጨዋች ነበር፡፡ ነገር ግን የብቃቱ ጣሪያ ላይ የነበረበት ጊዜ አልፏል፡፡ በመሆኑም ሲቲ በግራ መስመር ተከላካይ ስፍራ መላ ማፈላለግ ግድ ይለዋል፡፡ አለበለዚያ በቀጣዩ የውድድር ዘመንም ቢሆን ለዋንጫ ተፎካካሪ አይሆንም፡፡
ይህን ያውቃሉ?:- በዚህ የውድድር ዘመን ከ50 በላይ ሸርተቴዎችን ከወረዱ የሲቲ ተጨዋቾች መካከል የእርሱን ያህል ውጤታማ የነበረ የለም፡፡ 81 በመቶ የሚሆኑት ስኬታማ ነበሩ፡፡
Manchester City FC v FC Bayern Muenchen - UEFA Champions League
ማርቲን ዴሚቼሊስ
(የመሀል ተከላካይ)
ዕድሜ፡- 34
ፈረመ፡- 2013 (4.2 ሜ.ፓ)
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 25
ጎል፡- 1
ሲቲን የተቀላቀለ ሰሞን ክፉኛ ተተችቷል፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን ግን የቡድኑ ምርጥ ተከላካይ እርሱ ነው፡፡ ዕድሜው የገፋውን ቡድን ለማስወገድ ከተንቀሳቀሱ ግን ዕድሜው ደንቃራ ሊሆንበት ይችላል፡፡
ብይን፡- ለሲቲ ጥሩ ግልጋሎት ሰጥቷል፡፡ ለእርሱ የመውጫውን በር ለማሳየት መጣደፍም አያስፈልግም፡፡ ነገር ግን የክለቡ የረዥም ጊዜ እቅድ አካል እደማይሆን እርግጥ ነው፡፡
ይህን ያውቃሉ?:- በ2014/15 ደሚቼሊስ 131 ጊዜ ኳስን ከአደጋ ክልል በማፅዳት ከቡድኑ ጓደኞቹ ሙሉ ቀዳሚ ነው፡፡
አሌክሳንደር ኮላሮቭ
(የመስመር ተከላካይ)
ዕድሜ፡- 29
ፈረመ፡- 2008 (19 ሚ.ፓ)
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 15
ጎል፡- 8
በአሁኑ ወቅት ከቡድኑ አሰላልፍ ርቋል፡፡ በየትኛውም የረዥም ጊዜ እቅድ ውስጥ የመካተት ዕድል የለውም፡፡
ብይን፡- ከቡድኑ የመልቀቂያ ትክክለኛ ጊዜው ነው፡፡
ይህን ያውቃሉ?:- ኮላሮቭ በዚህ የውድድር ዘመን እስካን ጎል አላስቆጠረም፡፡ ከሲቲ ጋር ባሳለፋቸው ያለፉት አራት የውድድር ዘመናት በእያንዳንዳቸው ቢያንስ አንድ ጎል አስቆጥሯል፡፡
ቪንስ ኮምፓኒ
(የመሐል ተከላካይ)
ዕድሜ፡- 29
ፈረመ፡- 2008 (6 ሜ.ፓ)
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 23
ጎል፡- 0
የክለቡ መሪ እና አምበል ደካማ የውድድር ዘመን እያሳለፈ ይገኛል፡፡ በዋናነት እንደምክንያት የተጠቀሱት ጉዳት እና የአቋም መውረድ ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት ተጋላጭ ያልነበረው የኋላ መስመር ድብደባ ያስተናግድ ጀመር፡፡ ካምፓኒ ያለ ውድድር በሚያሳልፈው ክረምት ይጠቀም ይሆናል፡፡
ምናልባት ዘንድሮ ተቀዛቅዞ የታየው የዓለም ዋንጫ ላይ በመሳተፉ እና ተደራራቢ ጨዋታዎችን በማድረጉ ይሆናል፡፡ ሲቲዎች የተወሰነ እረፍት የቀድሞውን ኃይሉን ይመልስለታል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ፡፡
ብይን፡- የልዩ ብቃት እና ሰብዕና ባለቤት የሆነውን ተከላካይ ለማሰናበት ጊዜው አልደረሰም፡፡ በቀጣዩ የውድድር ዘመን በክለቡ ይቆያል፡፡
አሊያኪውም ማንጋላ
(የመሀል ተከላካይ)
ዕድሜ፡- 24
ፈረመ፡- 2014 (32 ሚ.ፓ)
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 19
ጎል፡- 0
በ32 ሚሊዮን ፓውንድ ፖርቶን ለቅቆ ሲቲን የተቀላቀለው ተከካላይ የታሰበውን ያህል ውጤታማ አልሆነም፡፡ ተጫዋቹ ለእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚመችም አይመስልም፡፡ ዝውውሩ በኤትሃድ ሂቱን በሚመሩ ሰዎች ላይ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው፡፡
ብይን፡- ለኃላፊነቱ የሚመጥን አይመስልም፡፡ ጥፋትን መቀነስ ብልህነት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሲቲ ለተጫዋቹ ከከፈለው የዝውውር ገንዘብ ጋር ተቀራራቢ የሆነ መጠን ያለው ሂሳብ ለማቅረብ የሚደፍር ያለ አይመስልም፡፡
ይህን ያውቃሉ?:- ማን ጋላ በዚህ የውድድር ዘመን በራሱ ሜዳ አጋማሽ ካደረጋቸው ፓሶች መካከል 94 በመቶ የተላኩ ነበሩ፡፡ ይህ አሃዝ ከየትኞቹም የሲቲ ተከላካዮ ይበልጣል፡፡
ባካሪ ሳኛ
(የመስመር ተከላካይ)
ዕድሜ፡- 32
ፈረመ፡- 2014 (በነፃ)
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 9
ጎል፡- 0
ሳኛ አርሰናልን ለቆ የማንቸስተሩን ሃሳብ ሲቀላቀል የፈረመው የሶስት ዓመት ኮንትራት ነው፡፡ ፔሊግሪኒ በብዙዎቹ ትልልቅ ጨዋታዎች ላይ ተጠቀመውበታል፡፡ ነገር ግን ወጣት አማራጮችን መፈለግ ብልህነት ነው፡፡ በቀጣዩ የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ተሰላፊ የመሆን ዕድሉ የጠበበ ነው፡፡
ብይን፡- በጭራሽ የመጪው ጊዜ እቅድ አካል ሊሆን አይችልም፡፡ ነገር ግን ተጠባባቂ ሆኖ ሊቀጥል ይችላል፡፡
ይህን ያውቃሉ?:- ሳኛ በሲቲ ባሳለፈው የመጀመሪያ የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊግ ላይ የመሰለፍ ዕድል ያገኘው በዘጠኝ ጨዋታዎች ብቻ ነው፡፡ አሸንፎ መውጣት የቻለው ደግሞ በአራቱ ብቻ ነው፡፡
ፓብሎ ዛባሌታ
(የመስመር ተከላካይ)
ዕድሜ፡- 30
ፈረመ፡- 2008 (6.5 ሚ.ፓ)
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 23
ጎል፡- 1
በደጋፊዎች እጅግ ከሚደዱት ተጨዋቾች አንዱ የሆነው አርጀንቲናዊ ድንቅ የሚባል የውድድር ዘመን በማሳለፍ ላይ አይገኝም፡፡ ዛባሌታ ከጠንካራ ማንነት የተሰራ በመሆኑ ችግሮቹን ቀርፎ በቀጣዩ የውድድር ዘመን የብቃቱ ጣሪያ ገና እንዳላለቀ ሊያስመሰክር ይችላል፡፡
ብይን፡- እርሱ የሚገኘው ካምፓኒ በሚገኝበት ምድብ ነው፡፡ በሲቲ የውጤታማነት ዘመን የቡድኑ ቁልፍ ተጨዋቾች ከነበሩት አንዱ እርሱ ነው፡፡ በመሆኑም በአንድ የውድድር ዘመን ጥሩ አቋም አላሳየም ብሎ ማሰናበት ችኩልነት ይሆናል፡፡
ይህን ያውቃሉ?:- ከአምስት በላይ ጨዋታዎችን ካደረጉ የሲቲ የሜዳ ላይ ተጨዋቾች መካከል ተቀይሮ ወደ ሜዳ ያልገባም ሆነ ተቀይሮ ያልወጣ ብቸኛ ተጨዋች ቢኖር እርሱ ብቻ ነው፡፡
ፈርናንዲንሆ (አማካይ)
ዕድሜ፡- 29
ፈረመ፡- 2013 (30 ሚ.ፓ)
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 27
ጎል፡- 2
ጥበበኛ ተጨዋች አይደለም፡፡ ነገር ግን የሚተማመኑበት አማካይ ነው፡፡ ማንኛውም ቡድን በስኳዱ ሲገናኝ ውጤታማ ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በስኳዱ ውስጥ ቢኖር ጠቃሚ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡
ብይን፡- በቀጣዩ የውድድር ዘመንም የቡድኑ አካል መሆን ይችላል፡፡
ይህን ያውቃሉ?:- ፈርናንዲንሆ ለ347 ኳሶች አንድ ለአንድ ተፋልሞ በ173 በበላይነት ወጥቷል፡፡
ፈርናንዶ (አማካይ)
ዕድሜ፡- 27
ፈረመ፡- 2014 (12 ሚ.ፓ)
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 21
ጎል፡- 2
ሌላኛው በ12 ሚሊዮን ፓውንድ ለሲቲ የፈረመ ያልተሳካ ዝውውር ነው፡፡ ቀርፋፋ ከመሆኑ በተጨማሪ ኳስን ወደ ፊት ፓስ የማድረግ ጥላቻ ያለበት ይመስላል፡፡ ወደ ሲቲ ምን ይዞ መጣ ወይም ሲቲ ምን ያስገኝልኛል ብሎ አስረመው? መልስ ያልተገኘለት ጥያቄ ይህኛው ነው፡፡
ብይን፡- ገዢ ከተገኘ ይለቀቃል፡፡
ይህን ያውቃሉ?:- ፈርናንዶ 62 በመቶ የማሸነፍ ንፃሬ አለው፡፡ እርሱ ባልተሰለፈበት ጨዋታ ሲቲ የሚያሸንፈው በ43 በመቶ ብቻ ነው፡፡
ጀምስ ሚልነር (አማካይ)
ዕድሜ፡- 29
ፈረመ፡- 2010 (26 ፣.ፓ)
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 27
ጎል፡- 3
ከሚገባው በታች ግምት የሚሰጠው ድንቅ ተጨዋች ነው፡፡ ነገር ግን ከማንቸስተር ሲቲ ጋር አዲስ ኮንትራት መፈራረም ባለመቻሉ ክለቡን መልቀቁ አይቀርም፡፡ አሰልጣኙ የሚፈልጉት አይነት ተጨዋች ነው፡፡ የሚለቀቅ ከሆነ በርካታ የሚያስፈርሙት የሚችሉ ክለቦች አሉ፡፡
ብይን፡- በክለቡ መቆየት ነበረበት፡፡ ነገር ግን ያ የሚሆነው አይመስልም፡፡
ይህን ያውቃሉ?:- በዚህ የውድድር ሲቲ ባስቆጠራቸው ዘጠን ጎሎች ላይ ተሳትፎ አድርጓል፡፡ በሲቲ በነበረው ቆይታ ከዚህ ቀደም ይህንን አይነት ስፖርት አስመዝግቦ አያውቅም፡፡
ሳሚር ናስሪ (አማካይ)
ዕድሜ፡- 27
ፈረመ፡- 2011 ()24 ሚ.ፓ
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 22
ጎል፡- 2
አልፎ አልፎ ካበረከታቸው ውስጥ አስተዋፅኦዎች በስተቀር ከእንደሱ ያለ በተሰጥኦ የታደለ ተጫዋች ከሚጠበቀው በታች እየሰጠ ያለ አማካይ ነው፡፡ ይህ በራሱ የውድድር ዘመኑን የሲቲ ሁኔታ ያንፀባርቃል፡፡
ብይን፡- በሲቲ አላማውን ከግብ አድርሷል፡፡ ጥሩ ክፍያ ፈፅሞ የሚወስደው ቢገኝ እንደ ትልቅ ኪራ አይቆጠርም፡፡
ይህን ያውቃሉ?:- በዚህ የውድድር ዘመን ሲቲ ናስሪ ከተሰለፈባቸው ጨዋታዎች 59 በመቶ አሸንፏል፡፡ እርሱ በሌለበት ግን የማሸነፍ ንፃሬው 50 በመቶ ብቻ ነው፡፡
ሄሱስ ናቫስ
(የመስመር ተጨዋች)
ዕድሜ፡- 29
ፈረመ፡- 2013 (14.9 ሜ.ፓ)
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 30
ጎል፡- 0
ከሲቪያ ሲመጣ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ተስፋ የተጣለበትን ያህል መሆን አልቻለም፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን 30 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ አንድም ጎል አለማስቆጠሩ በራሱ የሚነግረን ነገር አለ፡፡
ብይን፡- ትክክለኛ ጥያቄ የሚያቀርብ ወገን ከተገኘ አደጋ ላይ ነው፡፡ 29 ዓመት ስለሞላው ከዚህ የተሻለ አቋም የማሳየት ዕድሉ ጠባብ ነው፡፡
ይህን ያውቃሉ?:- በዚህ የውድድር ዘመን ናቫስ ሰባት ጎል የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
ያያ ቱሬ (አማካይ)
ዕድሜ፡- 31
ፈረመ፡- 2010 (24 ሚ.ፓ)
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 24
ጎል፡- 8
ትልቁ እንቆቅልሽሽ፡ ለዓመታት የሲቲ ስኬታማነት የነበረው ተጨዋች በዚህ የውድድር ዘመን የተሰላቸ የደከመ እና ከቡድኑ የተነጠለ መስሏል፡፡ የቀድሞ ማንነቱን ጥላ መስሏል፡፡ ሲቲ የእርሱን ግልጋሎት አጥብቆ በሚፈልግበት ወቅት ኃላፊነቱን መሸከም እየከበደው መጥቷል፡፡ ለሲቲ የፈፀመውን ነገር ክብር ሊነፍግ የሚሞክር የለም፡፡ ነገር ግን የሲቲ እና ቱሬ መለያያ የደረሰ ይመስላል፡፡
ብይን፡- እንደ ኢንተር ሚላን አይነት ቡድን ጥሩ ጥያቄ ካቀረበ እርሱን በሌላ የመተኪያው ትክክለኛ ወቅት ደርሷል፡፡
ይህን ያውቃሉ?:- ቱሬ በዚህ የውድድር ዘመን ከየትኛውም የሲቲ ተጨዋች በላይ ኳስ ነክቷል፡፡
ዴቪድ ሲልቫ (አጥቂ)
ዕድሜ፡- 29
ፈረመ፡- 2010 (26 ሚ.ፓ)
ተሰልፎ ተጫወተ፡- 26
ጎል፡- 11
ምናልባት በዚህ የውድድር ዘመን ከዚህ በፊት ካሳየው ድንቅ ብቃት ጋር የሚስተካከል እንቅስቃሴ አላደረገ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በየትኛው ሰዓት ልዩ ነገር መሥራት የሚችል ምትሃተኛ እግርኳስ ተጨዋች ነው፡፡ ፕሪሚየር ሊጉን ማድመቁንም ይቀጥላል፡፡
ብይን፡- ይቆያል፡፡

The post Sport: ከማንቸስተር ሲቲ ማን ለቅቆ ማን ይቀጥላል? appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>