Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ኢህአዴግን የማልመርጥበት 50 ምክንያቶች

$
0
0

EPRDF
ከእሙ አብረኸት

1. የካቲት 26/2004 የቀረቡትን 3 ጥያቄዎች ሳይቀበል አለባብሶ ለማለፍ መሞከሩ
2. በሚዲያዎቹ ህጋዊና ፍትሐዊ እንቅስቃሴውን ለማጠልሸት በመሞከሩ
3. ኮሚቴውን በማሰሩ
4. የመጅሊሱን ምርጫ በራሱ ቀበሌ በ‹‹ማስመረጡ››
5. ኮሚቴዎቻችንን በማእከላዊ በቶርቸር በማሰቃየቱ
6. የሐሰት ክስ በመመስረቱ
7. “ጅሀዳዊ ሀረካት” ብሎ የሀሰት ቆርጦ ቀጥል ዶክመንታሪ በመስራቱ
8. ለአህባሽ ዲስኩር በመንግስት ሚዲያ ሰፊ ሽፋን በመስጠቱ
9. የፍርድ ቤትን ትእዛዝ በመጣስም በቴሌቪዥን በማሳየቱ
10. የሐሰት ምስክሮችን በማሰልጠኑና በማስመስከሩ
11. ፖሊስ ከፍርድ ቤት በላይ የሆነበት ስርአት በመዘርጋቱ
12. የታሳሪዎችን ህገ- መንግስታዊ መብት በመጣሱ
13. የታሳሪ ሴት ጠያቂዎችን ሂጃብ ካላወለቃችሁ ብሎ ጥየቃ በመከልከሉ
14. ከሌላው እስረኛ በተለየ የጠያቂዎች ኮሚቴውን እንዳይጠይቁ ገደብ በማድረጉ
15. በእለተ ጁሙዓ ለፖለቲካ ድራማ ሲባል ሙስሊሙ ላይ ጉዳት በማድረሱ
16. በዒድ ቀን ደም በማፍሰስ
17. በኮፈሌ፣ በአሳሳ፣ በገርባ፣ በሐረር ንፁሐን ሙስሊሞችን በመግደሉ
18. ቁርአንን በድብቅ ሳይሆን በይፋ በማቃጠሉ
19. የሙስሊም ሴቶችን ሂጃብ በማቃጠሉ
20. ክብርን በሚነኩ ስድቦች እንድንሰደብ በማድረጉ
21. መርማሪዎቹ ‹‹ህገ- መንግስቱን ቀድዳችሁ ጣሉት›› እያሉ በመዘባበታቸውና መንግስትም ይህንን አውቆ ዝም በማለት የመንግስት አቋም መሆኑን በማሳየቱ
22. ደህንነቶቹና መርማሪዎቹ ‹‹አቃቤ ህጉም፣ ዳኛውም የእኛ ናቸው›› በማለታቸውና መንግስትም ይህንን አውቆ ዝም በማለት የመንግስት አቋም መሆኑን በማሳየቱ
23. ሙስሊሙን በሆነ ባልሆነው አስረው በመግረፍና በማንገላታት ለፖሊሶቹ የ‹‹ገቢ ምንጭ›› በመፍጠሩ
24. ሙስሊሙን አስረው እየገረፉ በሀሰት እንዲመሰክሩ በማድረጉ
25. የመንግስት ፖሊሶች መስጊዶችን ገብተው በማርከሳቸው
26. የኮሚቴዎችን ቤተሰቦች በሚዘገንን ሁኔታ በማሰቃየታቸው
27. በሌሊት የሙስሊሞችን ቤት ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰብረው በመግባት በፍተሻ ስም በፖሊሶችና ደህንነቶች ዘረፋ በመፈፀማቸው
28. በርካታ መስጊዶችን ከሊባኖስ ባስመጣው አህባሽ አስተሳሰብ በሰለጠኑ ሰዎች በእጅ አዙር በመቆጣጠራቸው
29. በርካታ ኢማሞች እንዲባረሩ በማድረጉ
30. በርካታ የእስልምና አስተማሪዎች እንዲሰደዱ በማድረጉ
31. በቀበሌ ‹‹ያስመረጣቸውን›› የመጅሊስ አሻንጉሊት አመራሮች ገምግሞ በራሱ እንደገና በመሾም ‹‹የመጅሊሱ አድራጊ ፈጣሪ እኔ ነኝ›› በማለቱ
32. ባልና ሚስትን ከማፋታት ወደ ኋላ የማይመለሱትን ፅንፈኛና ቀንደኛ የአህባሽ ሐዋሪያዎች ወደ መጅሊስ ወንበር በማምጣቱ
33. ሙስሊም ተማሪዎችን ሃይማኖታቸው ግዴታ ባደረገባቸው አለባበስ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው በማባረሩ
34. ተማሪዎች ሃይማኖታዊ ግዴታቸው የሆነውን ሶላት እንዳይሰግዱ በመከልከሉ
35. ሙስሊሙን ተማሪ ነጥለው ለመምታት በተዘጋጁ መመሪያዎች በማውጣቱ
36. ሁሉንም እስላማዊ ጋዜጦችን በማገዳቸው
37. ሙስሊም ጋዜጠኞችን በማሰራቸው
38. መስጊዶችን ሙስሊም ባልሆኑ ጆሮ ጠቢዎች በማጥለቅለቁ
39. የአህባሽን ግዳጅ ስልጠና በማስቀጠሉ
40. የሀሰት ምስክሮች ህዝብና ታዛቢዎች እንዳያያቸው ዝግ ችሎት በማድረጉ
41. በመስጊዶች ውስጥ በቀበሌ መጅሊሶቹ የምርጫ ቅስቀሳ በማድረጉ
42. ዳኞች ሁሌም ለአቃቤ ህጉ ወግነው በመስራታቸው
43. ከዳኞች ውስጥ የኢህአዴግ አባል በመኖሩ
44. በተደጋጋሚ ፍተሻ በማድረግ የኮሚቴዎችን የማስታወሻ ደብተራቸውን በህገወጥነት በመውሰዱ
45. ኮሚቴዎቻችን ላይ ቤተሰብና ህዝበሙስሊሙ እንዳይጠይቃቸው ብሎ ከሌላ ታሳሪ ለይቶ የጊዜ ገደብ በማሳነሱ
46. ከፍርድ በፊት ኮሚቴዎችን ወደ ቃሊቲ በማዛወርና ነጣጥሎ በማሰር የስነልቦና ቸችግር ለመፍጠር በመሞከሩ
47. ከፍርድ በፊት ኮሚቴዎችን ሌላ እስረኛ አብሯቸው እንዳይሆን በማድረጉና የስነልቦና ችግር ለመፍጠር በመሞከሩ
48. ኮሚቴዎቻችንን ምግብ እንዳይገባላቸው በመከልከል በጨለማ ቤት በማሰሩ
49. የፍርድ ሂደቱን እንዳሻው እንዲጓተት በማድረጉና ኮሚቴዎች በእስር ለረጅም ጊዜ እንዲጉላሉ በማድረጉ
50. የሚያዝያ 30 2007 የፍርድ ቀኑን ለምርጫ እንዲመቸው ብሎ በማዘዋወሩ የኢህአዴግ ግፍ ተዘርዝሮ አያልቅም!

The post ኢህአዴግን የማልመርጥበት 50 ምክንያቶች appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>