የደህሚት ድምጽ እንደዘገበው በርካታ የአማራ ክልል ተወላጅ የሆኑ ነባር የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ወታደሮች ስርዓቱን በመቃወም ወደ ሱዳን ሃገር እየሄዱ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በምንጮቻችን መረጃ መሰረት ለረዥም አመታት በውትድርና ሲያገለግሉ ቆይተው ከሃዲው ስርዓት የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር እያባረራቸው እንደሆነ የገለጸው መረጃው ከእነዚህም መካከል አወል አሊና ገብረማሪያም ታከለ የተባሉ የደቡብ ወሎ ተወላጆች እንዲሁም ምንዋጋው ቸኮልና አሸናፊ የተባሉ የጎንደር ተወላጆች የሚገኙባቸው 4 ነባር ወታደሮች ስርዓቱን በመቃወም ወደ ሱዳን ሃገር ሲሄዱ መያዛቸውን ታውቋል።
እነዚህ በስርዓቱ ታስረው የሚገኙ ወገኖቻችን ለበርካታ አመታት ስርዓቱን ሲያገለግሉ ቆይተው ያለምንም መቋቋሚያ ከተባረሩ በኋላ መሬት ጠይቀው የሚሰጣቸው አካል ባለማግኘታቸው ኑሮ መሯቸው ወደ ሱዳን ሃገር እንዲሰደዱ መገደዳቸውን ለማወቅ ተችሏል።
The post ሥርዓቱን ለረጅም ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩ 4 ወታደሮች ወደ ሱዳን ተሰደዱ appeared first on Zehabesha Amharic.