መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ የተነሳበትን ተቃውሞ ሰበብ በማድረግ ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን እያደነ መያዙን ቀጥሏል፡፡ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን በየመስሪያ ቤትና መኖሪያ ቤታቸው እያደነ ሲይዝ የቆየ ሲሆን ዛሬ ሚያዝያ 30/2007 ዓ.ም የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ቢሴ ብርሃኑ መኖሪያ ቤቱ አካባቢ ተይዞ ታስሯል፡፡ በአሁኑ ወቅት አዲስ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ይገኛል፡፡
በምስራቅ ጎጃም አስተባባሪና የደብረማርቆስ ዕጩ የሆነው ሳሙኤል አወቀ፣ በደቡብ ጎንደር ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ አለማየሁ አደመና ደብረማርቆስ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነችው የሀሰብ ጌታቸው ላይ የተፈፀመባቸው ድብደባ ይህን ይመስላል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia
The post አሁንም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በደህንነቶች እየታደኑ እየታሰሩ እየተደበደቡ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.