Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እየታደኑ እየታሰሩ ነው

Previous: Hiber Radio: በእስራኤል የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የጠነከረ ተቃውሞ ተከትሎ ባለስልጣናት ዘረኛ እርምጃ የወሰደውን ፖሊስ እናባርራለን ማለታቸው፣ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም እንድትመረምር መጠየቁ፣በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያን ሞተን ሻማ ከማብራታችሁ በፊት በሕይወት ታደጉን ሲሉ ጥሪ አስተላለፉ፣ዶ/ር መረራ በአገር ቤት ያለው የወጣቱ ሁኔታ ምርጫ 97ን ያስታውሳል ማለታቸው፣ የመኢአድ አባላት እየታፈኑ መወሰድ መቀጠሉ፣ የጦማሪ ሶሊያና ሺመልስ ቃለ መጠይቅ እና ሌሎችም
$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ
• በየ ክፍለ ሀገሩ የሚገኙ አባላት ላይ የሚፈፀመው ድብደባ ቀጥሏል
• ‹‹የተጀመረውን የሀሰት ክስ እውነት ለማስመሰል የታቀደ ነው››
ethiopia-blue-party-300x164የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ሰበብ እየታደኑ እየታሰሩ መሆኑን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ሀሙስ ሚያዝያ 22/2007 ዓ.ም ብሌን መስፍንና ተዋቸው ዳምጤ ከመስሪያ ቤት ተይዘው የታሰሩ ሲሆን ሚያዝያ 24/2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ‹‹ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተደረገውን አመጽ መርታችኋል፡፡›› በሚል ፖሊስ ክስ እንዳቀረበባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተመሳሳይ ዛሬ ሚያዝያ 26/2007 ዓ.ም ማቲያስ መኩሪያ ቤቱ ውስጥ እያለ በፖሊስ ተይዞ ታስሯል፡፡ ማቲያስ፣ ብሌንና ተዋቸው ወረዳ 10 (ላዛሪስት ፖሊስ ጣቢያ) ታስረው ይገኛሉ፡፡ ይህንን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የሚደረገው እስርም ‹‹መንግስት በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የጀመረውን የሀሰት ክስ እውነት ለማስመሰል የታቀደ ነው፡፡ ፖሊስ ምርመራ ሳይጨርስ በሀሰት 20 አባላትንና 6 አመራሮችን አስረናል ብለው ነበር፡፡ እነሱ የፈለጉት ይህን ሚዲያ ላይ ወጥተው በሀሰት የፈፀሙትን ውንጀላ ማሰመሰል ነው፡፡›› ሲል አቶ ዮናታን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
በሌላ ዜና በየ ክፍለ ሀገሩ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ደህንነትና ፖሊስ የሚፈፅመው ድብደባ አሁንም መቀጠሉ ተገልጾአል፡፡ በዛሬው ቀን የደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪና የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነችው የሀሳብ ጌታቸው ‹‹ለሰማያዊ ፓርቲ ወረቀት በትነሻል›› በሚል ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀሙባት ተገልጾአል፡፡

The post የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እየታደኑ እየታሰሩ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>