የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 25 ቀን 2007 ፕሮግራም
< ...በእስር ቤት በሴቶችም በወንዶችም ላይ የሚፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የጭካኔ ቅጣት በእነ ኤዶም ላይ የተጀመረ አይደለም እነሱ ደፍረው በማዕካላዊ የተፈጸመባቸውን ማጋለጣቸው ነው። ይሄ ወንጀል በሰብዓዊነት ላይ የተሰራ በመሆኑ በይርጋ የሚቀር አይደለም ወንጀለኞች መቼም ቢሆን ለፍርድ የሚቀርቡበት ነው…እኛ ለራሳችን ነጻነት መቆም ያለብን እኛው የአሜሪካዋ ባለስልጣን ግን… >
ጦማሪ ሶሊያና ሽመልስ በማዕከላዊ ምርመራ ሳሉ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬና ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን በመርማሪዎች የተፈጸመባቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ያቀረቡትን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ለጠየቅናት ከሰጠችን ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<… በየመን ያለን ኢትዮጵያውያን እሳት ውስጥ ነው ያለነው አሸባሪዎቹ የሱኒ አማጽያንን ካረዱበት ቦታ እኔ ካለሁበት የየመን ዋና ከተማዋ ሰንዓ አርባ ኪሎ እርቀት ነው ያለው…ስንሞት ሻማ ቢበራልንና ሰልፍ ቢወጣልን ምን ይጠቅማል አስቀድሞ ወገን ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ ለዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር እና አይ.ኦ.ኤም ይጩህልን። በተለይ በኤደን ያሉት ወገኖቻችን ከፍተኛ ችግር ላይ ናቸው…>
ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሀይማኖት ከየመን ሰንዓ ለህብር ከሰጠው ወቅታዊ ማብራሪያና የድረሱልን ጥሪ መልዕክቱ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
በእስራኤል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በወገናቸው ላይ ለተወሰደው ዘረኛ እርምጃ ያሳዩት ቁጣ የተቀላቀለበት ተቃውሞና የባለስልጣናቱ ምላሽ (ልዩ ጥንቅር)
ውይይት በኦቲዝም ላይ
ኦቲዝም ምንድነው? የኦቲዝም ያለባቸውን ልጆች እንዴት ለይተን በጊዜ ተገቢውን የህክምና እርዳታ ማግኘት ይችላሉ? ኦቲዝም ያለባቸው ልጆችና ወላጆቻቸው በማህበረሰባችን የሚገጥማቸው ፈተና እና መፍትሄው
ከዶ/ር ኤፍሬም መኮንን ከአትላንታ፣ ሰናይት አድማሱ የስነ ልቦና ባለሙያ ከሎስ አንጀለስ እና ከዚያው ከተማ የሁለት ልጆች ወላጅ የሆነችው ወ/ሮ ፌቨን ፋንቱ ጋር ተወያይተናል(ሙሉውን ያዳምጡት)
<…መንግስት ለስልጣኑ ካድሬው ለሆዱ አስቸግሮናል ።ሕዝቡን ስብሰባ እንዳይወጣ ሞክረው አልተሳካላቸውም አርባና ሃምሳ ሺህ ሰው በተለይ ወጣቱ ግልብጥ ብሎ ወጥቷል። ሁኔታው ምርጫ 97ን ያስታውሳል…እኛን ደገፉ ባሏቸው ላይ የሚደረገው ጥቃት ቀጥሏል…>
ዶ/ር መረራ ጉዲና ስለ ወቅታዊው የፓርቲያቸው የምርጫ ቅስቀሳ እና በስርዓቱ ስለሚደረግባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ከሰጡን ማብራሪያ(ሙሉውን ያዳምጡ)
የክፍለ ዘመኑ የቡጢ ውድድር በቬጋስ እና የአሸናፊው ቡጢኛ ማይዌይዘርና የፓኩዋያ የቅዳሜ ምሽት ግብ ግብ(ውይይት)
አቶ ጸጋዬ አላምረው በስርዓቱ የፈረሰው የእውነተኛው አንድነት የም/ቤቱ ም/አፈ ጉባዔና የፓርቲው የፋይናንስ ሀላፊ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስደተኛው ሲኖዶስ የሊቢያ ሰማዕታትን በየዓመቱ ለመዘከር ወሰነ
ሕዝቡ አሸባሪዎቹን በወገኖቹ ላይ የወሰደውን የግፍ ግድያ ኢንዳያይና እንዳያሰራጭ ተጠይቋል
በየመን የሚገኘው አይሲስ የሱኒ አማጽያንን በጭካኔ ገደለ
የኢትዮጵያኑ እጣ ፋንታ አልታወቀም
የአሜሪካ መንግስት የአገር ቤቱን አገዛዝ ከማሞካሸት እንዲቆጠብና ስለ ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ ትክክለኛ ምልከታ እንዲኖረው ተጠየቀ
ኤርትራ የኬኒያ ፕሬዝዳንት ሁሩ ኬኒያታ በአየር ክልሌ እንዳያመሩና ወደ አሜሪካ የሚያደርጉትን ጉዞ አላስተጓጎልኩም ስትል አስተባበለች
በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያን የአሸባሪዎች ጥቃት ሰለባ ከመሆናችን በፊት በቁማችን ድረሱልን አሉ
ዶ/ር መራራ ጉዲና በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የወጣቱ ስሜት ምርጫ 97 የሚያስታውስ መሆኑን ገለፁ
የመኢአድ አባላት ታድነው እየታሰሩ ነው
የእስራኤል ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላዊ ላይ የዘረኝነት ጥቃት የፈፀመው ፓሊስ ከስራ እንደሚባረር አስታወቁ
ጠ/ሚ/ር ኔታኒያሁ የኢትዮጵያውያኑን ተወካይ ሊያነጋግሩ ነው
የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን
The post Hiber Radio: በእስራኤል የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የጠነከረ ተቃውሞ ተከትሎ ባለስልጣናት ዘረኛ እርምጃ የወሰደውን ፖሊስ እናባርራለን ማለታቸው፣ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም እንድትመረምር መጠየቁ፣በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያን ሞተን ሻማ ከማብራታችሁ በፊት በሕይወት ታደጉን ሲሉ ጥሪ አስተላለፉ፣ዶ/ር መረራ በአገር ቤት ያለው የወጣቱ ሁኔታ ምርጫ 97ን ያስታውሳል ማለታቸው፣ የመኢአድ አባላት እየታፈኑ መወሰድ መቀጠሉ፣ የጦማሪ ሶሊያና ሺመልስ ቃለ መጠይቅ እና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.