Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የ23ኛ ክፍለጦር፤ 1ኛ ሬጅመንት የፋይናንስ ሰራተኞች ገንዘብ እየያዙ በመጥፋት ላይ ናቸው

$
0
0

የደህሚት ድምጽ እንደዘገበው በኢህአዴግ ስርዓት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እምነት ያጡ የ23ኛ ክፍለጦር፤ 1ኛ ሬጅመንት የፋይናንስ ሰራተኞች ገንዘብ እየያዙ በመጥፋት ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ።
defense minster ethiopia
በማዕከላዊ እዝ የ23ኛ ክፍለ ጦር አባላት ለበዓል ማክበሪያ እየተባለ ከነፍስ ወከፍ ወታደር 87 ብር ያለፍላጎታቸው እንደተቆረጠባቸው የገለጸው መረጃው ሃምሳ አለቃ ብርሃኑ የተባለ የአንደኛ ሬጅመንት የፋይናንስ ሓላፊ ሃላፊነቱን ተጠቅሞ የፋይናንስ ካዝና በመክፈት የሬጅመንቱን አምሳ ሁለት ሽህ አምስት መቶ (52,500) ብር ገንዘብ ይዞ ከዝባን ገደና ተነስቶ ከሽራሮ ከተማ በመኪና ተሳፍሮ ለማምለጥ ሲሞክር እንደተያዘ ለማወቅ ተችሏል።

በእዙ ውስጥ የሚገኙ የሰራዊት አመራሮች በየወቅቱ ምክንያቶችን እየፈጠሩ የሰራዊቱን ደመወዝ በመቁረጥ ለግል ፍላጎታቸው ማሟያ እያዋሉት ስለሚገኙ እያንዳንዱ ወታደር ተቆራርጣ በእጁ ከምትደርሰው አነስተኛ ደመወዝ ቤተሰቡን ሊያግዝ ይቅርና ለራሱም መሆን እንዳልቻለ የደርሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል ሲል ደህሚት ድምጽ ዘግቧል::

The post የ23ኛ ክፍለጦር፤ 1ኛ ሬጅመንት የፋይናንስ ሰራተኞች ገንዘብ እየያዙ በመጥፋት ላይ ናቸው appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles