ደህሚት እንደዘገበው በቅርቡ የድርጅቱን ወቅታዊ መልእክትና የትህዴንን አላማ የያዘ ፓምሌት በአዲስ አበባ አውራ ጎደናዎች፤ ሚያዝያ ሰባት ላይ በዓድዋ መናሃሪያ፤ ፊሾ ተብሎ በሚጠራ አካባቢና ሰልፍ ሜዳ በተንቤን አብይ ዓዲ ከተማ፤ ሽሬ እንዳስላሴ ውስጥ በሚገኙ የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችና፤ ሚያዝያ 6 ላይም በአክሱም መናሃርያ፤ እንዳማርያም፤ ወጋገን ባንክ አካባቢ በሚኘው መናፈሻና ሌሎችን ህዝብ በብዛት በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች መበተኑና በርካታ የህብረተሰቡ አካላት ለማንበብ እድል እንዳገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ ከተማው ውስጥ በሚገኙ የተደራጁ አባላት የተበተነው የፓምፕሌት ይዘትና መልእክት የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ጭቁን ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር ሆኖ ለ 17 ዓመት ያህል ያካሄደውን አስቸጋሪ የትጥቅ ትግል ለግል ጥቅማቸው በሚያስቡ የህወሃት/ኢህአዴግ መሪዎች ተክዶ የመስዋእትነቱ ፍሬ ተጠቃሚ ባለመሆኑ ትህዴን ይህን የተካደ የሰማእታትን አደራ ዳሩ ላይ ለማድረስ መፍትሄው የትጥቅ ትግል ነው ብሎ በማመን እንደገና መስዋእትነት እየከፈለ ባለበት ባሁኑ ግዜ ህዝቡ ስርዓቱ ግንቦት ወር ሊያካሂደው ባሰበው አስመሳይ ምርጫ ላይ ጀሮ ሳይሰጥ የትጥቅ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው የሚጠራ ፅሁፍ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
ባለፉት ቀናቶች በዓዲ ግራትና መቐለ ከተማ ውስጥ ከሦስት ግዜ በላይ የትህዴን ፓምፕሌት ተበትኖ በነዋሪው ህዝብ በደረሰበት ግዜ ህዝቡ እንደ አንድ ትልቅ ተስፋ በመቁጠር ሲቀበለው በአንጻሩ የስርአቱ ካድሬዎች ግን እንቅልፍ እንዳሳጣቸው በተገኘው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
The post በተለያዩ ከተሞች የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ ዓላማዎችን የያዘ ፓምፕሌ መበተኑ ተገለፀ appeared first on Zehabesha Amharic.