Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

መሰቦ ስሚንቶ ለአባይ ግድብ ስሚንቶ ማቅረቡን ማቋረጡ ተሰማ

$
0
0

ኢሳት ዜና :-የህወሃት የልማት ድርጅት ፣ ኢፈርት ንብረት የሆነው መሶቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ላለፉት ሶስት አመተት ያለተቀናቃኝ በከፍተኛ ዋጋ ለአባይ ግድብ ስሚንቶ ሲያቀርብ ከቆየ በሁዋላ ፣ ስራውን አቋርጧል።

የአባይ ግድብ ግንባታ የኢኮኖሚ አዋጭነት ጥናት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይፋ ከተደረገ በኃላ በባለስልጣናት መካከል ውዝግብ መነሳቱ ታውቋል። ጉባ የሚገኘው የስሚንቶ ማምረቻ በመሰቦ ስር እንዲሆን መወሰኑ የውዝግቡ መነሻ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
Mesobe Cemnet
ይህን ተከትሎ ፋብሪካው ላልተወሰነ ጊዜ አቅርቦቱን አቋርጧል፡፡ በህወሃት ባለስልጣናት ተፅኖ ያለምንም ጫረታ ያሸነፈው መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ፣ ትራንስ እና ጉና በሚባሉ የህወሃት የትራንስፖርት ድርጅቶች ስሚንቶ ወደ ግድቡ በማመላለስ ባለፉት 3 አመታት
9 ቢልዮን 345 ሚልዮን 289 ሺ ብር ገቢ አግኝቷል። መሰቦ የሲሚንቶ ፋብሪካ በ240 ሚሊዩን ብር የተከፈለ ካፒታል ከመቀሌ 15 ኪሜ እርቆ በሚገኝ ስፍራ ላይ በፈረንጆች አቆጣጠር በ1995 የተመሰረተ ነው፡፡

1 ሺ 1 መቶ 95 ቆሚ ሠራተኞች ፣ 240 ኮንትራት ሠራተኞችና 51 ጊዜያዊ ሠራተኞች ያሉት መሰቦ በአመት 900 ሺ ቶን ስሚንቶ ያመርታል።

ፋብሪካውን የቻይና ማኔጀሮች በኮንትራት ሲያስተዳድሩት ቆይተው እኤአ በ2000 ውላቸው ተቋረጠ፡፡ እስከ 2003 ፋብሪካው በኪሳራ ለመዘጋት ተቃርቦ የነበረ ሲሆን፣ ማኔጅመንቱን ፓኪስታኖች እንዲወስዱት ተደርጓል።

ከ6 አመታት በፊት መሶቦ ፋብሪካ የማስፋፍያ ስራውን ሃንፊ ለሚባል የቻይና ኩባንያ በ3 ቢሊዩን ብር ወይም 180 ሚሊዩን ዶላር በመስጠት ምርቱን አሁን በቀን ከሚያመርተው 3 ሺ ኩንታል ስሚንቶ ወደ 6 ሺ ኩንታል ስሚንቶ ለማሳደግ እቅድ ነድፎ ነበር።
ኩባንያው ለዚህ ስራው 141.6 ሚሊዩን ብር ወይም 8.4 ሚሊዩን ዶላር ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተበድሯል።

መሰቦ የሲሚንቶ ፋብሪካ ሲቋቋም የደንበኛ ጥናት ባለማካሄዱ ለብዙ አመታት በኪሳራ ተንቀሳቅሷል፡፡ የፋብሪካው ርቀት በመላ ሀገሪቱ ምርቶቹን ለማከፈፈልና መሸጥ አላስቻለውም ነበር፡፡ ህወሃት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለሚያሰሩዋቸው ፕሮጀክቶች ስሚንቶ ከመሶቦ እንዲገዙ በማድረግ ኪሳራውን በህዝብ ኃብት ለመሸፈን መሞከሩን የውስጥ ምንጮች ይናገራሉ።

ህወሃት በመሰቦ፣ በትራንስ ፣ በጉና ድርጅቶች በቀጥታ ከአባይ ግድብ ግንባታ ተጠቃሚ ሲሆን፣ የወ/ሮ አዜብ መስፍን የእህት ልጅ የሆኑት የወ/ሮ አኪኮ ስዩም ንብረት የሆነው ኦርኪድ ኩባንያ ደግሞ ማሽነሪዎችን ያቀርባል። የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንም እንዲሁከግድቡ ግንባታ ከፍተኛ ገንዘብ ያገኛል።

The post መሰቦ ስሚንቶ ለአባይ ግድብ ስሚንቶ ማቅረቡን ማቋረጡ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>