በጃክሰንቪል ፍሎሪዳ የሻማ ማብራትና የጸሎት ሥነ ሥርዓት ተካሄደ
(ሐበሻ ሬዲዮ) በቅርቡ በሊቢያ የባህር ዳርቻ ፣ በግፍ የተረሸኑትንና የታረዱትን፣ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ፣ በየመን እና በሌሎችም የዓለማችን ክፍሎች በችግርና በስቃይ ውስጥ ያሉትን ወገኖችን ለማሰብ የተዘጋጀ የሻማ ማብራትና የጸሎት ስነ ሥርዓት፣ በጃክሰንቪል ፍሎሪዳ ተካሄደ። በዚሁ ከ መቶ የማያንስ የኢትዮጲያ እና ኤርትራዊያን ነዋሪ በተገኘበት ስነ ሥርዓት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተወካይ እና ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አባቶች ተገኝተው በየተራ ጸሎት በማድረግ መርሃ ግብሩን ከፍተዋል በዚሁ የጸሎትና የሻማ ማብራት ስነ ሥርዓት ፣ በሁሉም አባቶች መንፈሳዊ ምክር ተሰጥቷል የወገኖቻችን ሞትና እስራት፣ መከራና ችግር፣ ስቃይና መቃተት የሁላችንም ስሜት እንደሆነ በተነገረበት በዚህ ዝግጅት፣ የዕምነት ተቋማት መቀራረብና አንድ መሆን ወሳኝነት አለው ብለዋል።በንግግራቸውም በሊቢያ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን አስታውሰው በአይሲስ ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተዋል:: በደቡብ አፍሪካ እና በየመን እያለቁ ስላሉት ኢትዮጵያውያንም ተጸልይዋል:: ሁሉም የሃይማኖት መሪዎች ያሳሰቡት ነገር ቢኖር አንድነት እና ፍቅርን ሲሆን ሁሉም አንድ ሆኖ ለሃገሩና ለሕዝቡ እንዲቆም ጠይቀዋል::
ሜላት መኮንን ለሐበሻ ሬዲዮ ከጃክሰንቪል ፍሎሪዳ
The post በጃክሰንቪል ፍሎሪዳ የሻማ ማብራት -ሜላት መኮንን ለሐበሻ ሬዲዮ ከጃክሰንቪል ፍሎሪዳ appeared first on Zehabesha Amharic.