ላለፉት ሃያ አራት ዓመታት ያለ ኢትዮጵያዊ መንግስት የኖረው ሕዝባችን፣ በወያኔ/ የትግሬ ነፃ አውጭ ግንባር ሁለንተናዊ ጥቃት፣ሞት እና ስደት ሲፈራረቁበት ኖሮአል። በአገሩ የመኖር ተስፋ በማጣቱ ፣ሰብዓዊ መብቱ ተጥሶ በውርደት እንዲኖር በመገደዱ የተነሳ ወጣቱ ትውልድ ስደትን እንደ አማራጭ እንዲወስድ በረቀቀ መንገድ ተገዷል። ሰሞኑን በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ በሳውዲ አረቢያ፣ በየመን ፤በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በተፈጸመው ኢሰብዓዊ ተጋባርና አሰቃቂ ግድያ ጥልቅና ከባድ ሃዘን ተሰምቶናል አስቆጥቶናልም።
የዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የሴቶች ድርጅት የወገኖቻችን የሰማዕታት ደም በከንቱ ፈሶ የማይቀር መሆኑን እያረጋገጥን የበለጠ ተጠናክረን ለስደትና ለሰቆቃ የዳረገንን የወያኔ ስርዓትን በቆራጥነት የምናስወግድበት ወሳኝ ወቅት ላይ ደርሰናል በለን እናምናለን። በኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ላይ የመከራ እጁን ያነሳ ሁሉ ተገቢውን ዋጋውን እንደሚያገኝ ጥርጥር የለንም። በቅድሚያ ግን ለዚህ አስከፊ ችግር እና ሰቆቃ የዳረገን ፀረ ኢትዮጵያ የሆነው ወያኔ የትግሬ ነፃ አውጭ ግንባር በመሆኑ የችግሩን ምንጭ ማድረቅና መንስዔውን አሁኑኑ ማስወገድ ሰብዓዊ፣ ኢትዮጵያዊና ታሪካዊ ግዴታችን ነው። ይህ ካልሆነ ግን ኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥም ይሁን በዓለም ዙሪያ ለከፍተኛ መከራና ችግር፣ ለወራሪዎች ኢላማ፣ የእልቂትና የሞት አውድማ የመሆን አደጋ ከፊታችን የሚጠብቀን መሆኑን ከወዲሁ መገንዘብ ይኖርብናል።
ስለዚህም ዛሬ ለተሰዉት ወገኖቻችን ማዘን ብቻ ሳይሆን፣ ዘላለማዊ ሕይወታቸው በአምላካቸው ጎን በመሆኑ ተጽናንተን ፣የፈሰሰው ደማቸው ለኢትዮጵያ ትንሳኤ ኃይልና ጉልበት እንዲሆን የሚያስፈልገውን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅብናል። ክብራችንና ነጻነታችን ያለው በእኛ በኢትዮጵያውያን እጅ ነው፤ ከሀዘንና ከውግዘት መገለጫ ባሻገር ቆርጠን በመነሳት እውን ልናደርገው ይገባል። ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የሴቶች ድርጅት በአገርም ውስጥ ሆነ በውጭ አገር የሚደርሰው በደልና የሚፈሰው የወገኖቻችንን ደም ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር በተባበረ ኢትዮጵያዊ የነጻነት መንፈስ እንነሳ ዘንድ፣ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ያለንበትን ተጨባጭ ሁኔታና ስሜትን የሚገልጸው የክላውድ ማኬ ታሪካዊ ግጥምን በማስታወስ ወገናዊ ጥሪ እናቀርባለን።
If We Must Die
Claude McKay, 1889 – 1948
If we must die—let it not be like hogs
Hunted and penned in an inglorious spot,
While round us bark the mad and hungry dogs,
Making their mock at our accursed lot.
If we must die—oh, let us nobly die,
So that our precious blood may not be shed
In vain; then even the monsters we defy
Shall be constrained to honor us though dead!
Oh, Kinsmen! We must meet the common foe;
Though far outnumbered, let us show us brave,
And for their thousand blows deal one deathblow!
What though before us lies the open grave?
Like men we’ll face the murderous, cowardly pack,
Pressed to the wall, dying, but fighting back!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የሴቶች ድርጅት
ሚያዚያ፣ 2007
The post የዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የሴቶች ድርጅት አጭር መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.