Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በዋሽንግተን ዲሲ የደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ አጠገብ ነገ ሰኞ ጠዋት ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ በስደተኞች ላይ የተፈጸመውን ግድያና ማዋከብን በመቃወም የደቡብ አፍሪካ መንግስት ይህን ጉዳይ በቶሎ እንዲያስቆም የሚጠይቅ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚደረግ አዘጋጆቹ ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::
south africa ethiopians
በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያኑ እና በሌሎች የአፍሪካውያን ስደተኞች ላይ የተፈጸመውን አሳፋሪ ድርጊት በመቃወም የተለያዩ ሃገር ወዳድ አርቲስቶች በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ሃዘናቸውን ሲገልጹ ነበር:: ከነዚህም መካከል በቅርቡ ‘ወገኔ’ የሚል ትልቅ መልዕክት ያለው ሙዚቃ የለቀቀው አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ ይጠቀሳል:: ብርሃኑ በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያኑ ላይ የተፈጸመውን ድርጊት አውግዞ ከወገኖቹ ጋር እንደሚቆምና እስካሁንም ጉዳት ያልደረሰባቸው ወገኖች ሁኔታው እስኪረጋጋ ድረስ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጠይቋል:: ብርሃኑ “ከዚህ በፊትም በአረብ ሃገር አሁንም በደቡብ አፍሪካ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይ ያሳዝናል” ብሏል::

ታዋቂው ተወዛዋዥ አብዮት (ካሳነሽም) እንዲሁ በደቡብ አፍሪካ ሕይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያን ፈጣሪ በገነት ነብሳቸውን እንዲያኖር ጠይቆ በጉዳዩ በጣም ማዘኑን ገልጿል:: ወጣቱ ተወዛዋዥ አብዮት በደቡብ አፍሪካ በስቃይ ላይ ለሚገኙት ወገኖቹ በሙያው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጿል:: በተጨማሪም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በያለበት ሃገር የደቡብ አፍሪካ ኢንባሲ ደጃፍ በመገኘት ለወገኖቹ ድምጹን እንዲያሰማ ጥሪም አቅርቧል::

እንቆቅልሽ የተሰኘ ተወዳጅ አልበም በቅርቡ የለቀቀው ድምፃዊ ፋሲል ደመወዝም እንዲሁ በደቡብ አፍሪካ የደረሰውን ሲመለከት እንዳመመው ገልጾ ሁሉም ጸሎት እንዲያደርግ ጠይቋል:: በዋሽንግተን ዲሲ በነገው ዕለት በደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ በሚደረገው ሰልፍ ላይም ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምጹን እንዲያሰማም ጥሪ አቅርቧል::

ሰኞ ኤፕሪል 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ በ9 ሰዓት በሚደረገው በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ታዋቂውን የሰብ አዊ መብት ተሟጋች እና አርቲስት ታማኝ በየነን ጨምሮ በርከት ያሉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል::

Monday …April 20th @ 9:am
South African Embassy
3051 Mass Ave NW, Wash, DC

The post በዋሽንግተን ዲሲ የደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ አጠገብ ነገ ሰኞ ጠዋት ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles