በሙለታ መንገሻ
ቡና በውስጡ አንቲኦክሲዳንት በመያዙ በሽታን ይከላከላል በተለይም ለአንጀት ካንሰር እና ሎሌች በሽታዎች በቀላሉ እንዳንጋለጥ ያድርጋል።
በተጨማሪም ቡና በውስጡ ካፌን የተባለ ንጥረ ነገር ስላለውም ሰዎች ብዙ ጊዜ ለመነቃቃት ይጠቀሙበታል።
በቡና ውስጥ ያለው አንቲኦክሲደንት በአትክልት እና ፍራፍሬ ውስጥ ያለው ክሎሪን ጄኒክ አሲድ ስብስብ መሆኑ ይነገራል።
ይህም ቡናን በባዶ ሆድ በምንጠጣበት ወቅት እኛ ላይ ጉዳት እንዲሚያስከትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው ይባላል።
ጠዋት ከእንቅልፋችን እንደነቃን በባዶ ሆድ ቡናን የምንጠጣ ከሆነም ምግብ በሆዳችን ውስጥ በቀላሉ እንዲፈጭ የሚያደርገውን ሀይድሮሊክ አሲድ ላይ ጉዳት በማድረስ በቀላሉ ጨጓራችንን እንዲያመን ያድርገናል።
ለምግም መፈጨት በሚረዳን ሀይድሮሊክ አሲድ ላይ በቡና አንቲከኦክሲደንት አማካኝነት ጉዳት ከደረሰበት ከበድ ያሉ እና ፕሮቲንነት ያላቸው እንደ ስጋ ያሉ ምግቦች ሆዳችን ውስጥ በቀላሉ መፈጨት ስለማይችሉ እንደ ሆድ መነፋት፣ የሰውነት መቆጣት፣ የአንጀት ቁስለት እና ለአንጀት ካንሰርም ሊያጋልጠን ይችላል ይላሉ ተመራማሪዎቹ።
ቡናን ከእንቅልፍ እንደተነሳን የምንጠጣ ከሆነ በሰውነታችን ውስጥ ያለ የኮርቲሶን ንጥረ ነገር መጠን እንዲጨምር በማድረግ ሆዳችን እንዲነፋ ያደርጋል እንዲሁም እንዲያስታውከን በማድረገ ሰውነታችን እዳይረጋጋ ያደርጋል።
ስለዚህም በተለያዩ ጊዜ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ቡናን ጠዋት መጠጣት ያለብን ከእንቅልፋችን ነቅተን ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያክል ከቆየን በኋላ እና ቢያንስ አንድ ዳቦ ከበላን በኋላ መሆብን አለበት ይሉናል።
በጠዋት ስንነሳ ቁርስ የመብላት ባህሪ ከሌለን ቡናን መተው የሚመከር ሲሆን፦ አይ እኔ ያለ ቡና ቀኔን መጀመር አልችልም የምትሉ ከሆነ ደግሞ ቡናው የሚደርስብንን ጉዳት ለመቀነስ ያክል ትንሽ ወተት ወይም ቅቤ ቡናው ላይ ጨምረን መጠጣት አይዘንጉም ይሉናል ተመራማሪዎች።
ምንጭ፦ homehealthyrecipes.com
The post Health: ቡናን በባዶ ሆድ መጠጣት በጤና ላይ የሚያመጣውን ጉዳት ያውቁ ኖሯል? appeared first on Zehabesha Amharic.