(ዘ-ሐበሻ) ድምፃችን ይሰማ ባስተላለፈው ጥሪ መሠረት በደቡብ አፍሪካ የድንበር ከተማ ላይ የምትገኘው መሲና ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በ እስር ላይ የሚገኙት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ነፃ መሆናቸውን መሰከሩ::
በስፍራው የሚገኘው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢ በፎቶ ግራፍ አስደግፎ በላከው ዜና መሰረት ኢትዮጵያውያኑ ሙስሊሞች ሕዝባዊ ስብሰባ ጠርተው በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ከተወያዩ በኋላ የታሰሩት የኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ ጠይቀው ነፃ ናቸው ብለዋል::በስብሰባው ላይ የታደሙት ወገኖች “የታስርነው እኛ ነን” የሚል ቢጫ ቲሸርት ለብሰው ለስብሰባው ድምቀት ሰጥተውታል::
ሕወሓት የሚመራው መንግስት በካንጋሮው ፍርድ ቤት በኩል ከሰሞኑ በነዚህ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ፍርድ ለማስተላለፍ ዝግጅ መሆኑን ተከትሎ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በመሰባሰብ ኮሚቴው ነፃ መሆኑን በመመስከር በነፃ እንዲለቀቁ እየጠየቁ ነው:: እንዲህ ያለው ስብሰባም እስካሁን ባልተደረገባቸው ሃገራት እንደሚቀጥል ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል::
The post በደቡብ አፍሪካ መሲና ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኮሚቴው ነፃ መሆኑን መሰከሩ appeared first on Zehabesha Amharic.