መርካቶ ሠፈሬ በሚለው ታዋቂ ዘፈኑ ከሕዝብ ጋር የተዋወቀው አብዱ ኪያር አዲስ ነጥላ ዜማ ለቀቀ:: አዲሱ ነጠላ ዜማው “መልካም አመት በዓል” ሲሆን መል ዕክቱም ጠንካራ እንደሆነ ግጥሙን ያነበቡ ሰዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::
ዘፈኑን ይመልከቱ; ከዘፈኑ በታች ደግሞ ግጥሙን አስተናግደናል:-
መልካም አመት በዓል – አብዱ ኪያር
ተሰብስበን እንዳማረብን
በአውዳመቱ ፍቅር ያዝንብብን
ቤት ለሌሉት ለራቁት በአካል
በያሉበት መልካም አመት በዓል
አንቺ የኢትዮጵያ እናት ይለፍልሽ
ከአመት እስከ አመት ይሙላ ጓዳሽ
አንተ የኢትዮጵያ አባት እሺ ይበልህ
ከሰው እንዳታይ እንዳይጎድልህ
ጀግናዋ እህቴ የናቷ ልጅ
ከብረሽ ቆይልን ውለጅ ክበጅ
ወንድሜ አንበሳው ያባቱ ልጅ
ክፉ አያሳይህ ደጋጉን እንጂ
ከአገር ርቀው ለተሰደዱት
በህመም በስቃይ ካልጋ ለዋሉት
በህግ ተይዘው እስር ቤት ላሉት
ያድርግላቸው እንደሚመኙት
እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየን
ካለም ሚለየን ከማንም ዜጋ
የሚያሳምመን ልክ እንደ አለንጋ
ልብ ውስጥ ታትሞ የማይዘነጋ
ያገር ፍቅር ነው የነፍሶች ዋጋ
ያገር ፍቅር ነው የነፍሶች ዋጋ
ከእየሩሳሌም ደግሞም ከመካ
እኛን አክብሮ ከሩቅ ጃማይካ
ኢትዮጵያን ብሎ በኛ ሲመካ
ተቀብለናል ትመስክር አፍሪካ
ተቀብለናል ትመስክር አፍሪካ
እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየን
የወንጌሉ ሰው ላገሬ እስላሙ
ወገኑ አይደል ወይ ደራሽ ወንድሙ
የቁርአኑ ሰው ለክርስቲያኑ
ወንድሙ አይደል ወይ ደራሽ ወገኑ
ወንድሙ አይደል ወይ ደራሽ ወገኑ
ረመዳን ስፆም በርታ የሚል ጓዴ
አይዞህ የምለው ሲሆን ኩዳዴ
የኔና የሱን ታላቁን ፍቅር
ኢትዮጵያን ያየ ወጥቶ ይመስክር
ኢትዮጵያን ያየ ወጥቶ ይመስክር
እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየን
The post አብዱ ኪያር አዲስ ነጠላ ዜማ ለቀቀ (ዘፈኑን እና ግጥሙን ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.