የ2017ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ድልድል በካፍ ዋና መቀመጫ በግብጽ ካይሮ ዛሬ ወጣ:: ኢትዮጵያ በ2017ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከአልጀሪያ፣ ሌሴቶና ሲሸልስ ጋር መመደቧን ሱፐር ስፖርት ድረገጽ ዘገበ::
በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ከአልጀሪያ፣ ሌሴቶና ሲሸልስ ጋር በምድብ ጄ ስትደለደል ከሌሲኤቶና ሲሸልስ ሃገራት ደካማነት አንፃር ኢትዮጵያ ጠንክራ ከሰራች ከአልጄሪያ ጋር ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ያላት ዕድል ሰፊ እንደሆነ የስፖርት ተንታኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::
በ2015ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከማሊ፣ ማላዊ እና አልጄሪያ ጋር ተደልድሎ በአልጀሪያ በሜዳው 2 ለ 1 አልጀርስ ላይ ደግሞ 3 ለ 1 መረታቱ አይዘነጋም።
እንደ ሱፐር ስፖርት ዘገባ ጋቦን የ2017ቱን የአፍሪካ ዋንጫ እንድታዘጋጅ ስትመረጥ ከኮቲዲቯር፣ ሱዳን እና ሴራሊዮን ጋር ተመድባለች። ይሁን እንጂ ከጋቦን ጋር የሚደረጉት ጨዋታዎች ምንም አይነት ነጥብ አይያዝባቸውም።
ጋቦን በአለመረጋጋት ላይ የምትገኘውን ሊቢያን ተክታ ነው የ2017ቱን የአፍሪካ ዋንጫ እንድታስተናግድ የተመረጠችው።
ድልድሉ ሙሉው የሚከተለው ሲሆን ከየመድቡ በነጥብ አንደኛ እና ሁለተኛ የሆኑ በቀጣዩ የጋቦን አፍሪካ ዋንጫ ይሳተፋሉ::
The post የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ድልድል ወጣ – ኢትዮጵያ ከአልጄሪያ ሲሸልስና ሌሴቶ ጋር ተደለደለች appeared first on Zehabesha Amharic.