ወያኔ ወደ የመን የሰላም አስከባሪ ሊኮ ዶላሮች ለመዛቅ ሳኡድ አረቢያን እየተለማመጠ ከሆነ በበደል ላይ በደል የከሳዉን መግደል ያሰኛል::ዜጎችን ለማስወጣት ያልተረባረበ ወንጀለኛ ስርአት በየትኛው ሞራሉ ሰላም አስከባሪ ልኮ የመኖችን ሊታደግ? የወያኔ ጥቅም ለማጋበስ የሚደረግ ሩጫ እስካሁን አልተሳካም:: አረብ ሊግ እኮ እንደማይፈልግ በተደጋጋሚ እየተናገረ ሳኡዲን መለማመጥ ለምን አስፈለገ?የወያኔ አገልጋይ የሆነው ሃይለማርያም ደሳለኝ የሳኡዲ አረቢያን የአየር ድብደባ በተመለከተ የሰጠው ድጋፍ የሰሙት የመናውያን በኤምባሲው ላይ ጥቃት እንዳደረሱ እና ኢንዲሁም ኢትዮጵያውያንን በየመንገዱ እየተሳደቡ እንደሚገኙ ከሰነአ የሚገኙ ወገኖች ጠቁመዋል::የሳኡዲ አየር ሃይል ኤምባሲውን አልመታም::በተሳሳተ መረጃ ለማደናበር ወያኔ እየሞከረ ነው::
Source- Minilik Salsawi
The post በበደል ላይ በደል የከሳውን መግደል !! የወያኔ ጥቅም ለማጋበስ የሚደረግ ሩጫ እስካሁን አልተሳካም:: appeared first on Zehabesha Amharic.