Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የዘውዲቱ ሆስፒታል ሊፍት ሰው ገደለ

$
0
0

(መንግሥቱ አበበ)

የዛሬ ሳምንት ከሰዓት በኋላ ነው፡፡ የ72 ዓመቱ አዛውንት አቶ ካሣሁን አበበ ታምማ ዘውዲቱ ሆስፒታል የተኛች እህታቸውን ለመጠየቅ ሄዱ፡፡ ሆስፒታል ደርሰው እህታቸው ወደተኙበት ክፍል ለመሄድ የሊፍቱን መጥሪያ ሲጫኑት ተከፈተ፡፡

liftሊፍቱ ተበላሽቶ ስለነበር ሰው መጫኛው ወለል አልነበረም፡፡ አቶ ካሳሁን ወለሉ ያለ መስሏቸው ዘው ብለው ሲገቡ ጉድጓድ ውስጥ እንደገቡ ልጃቸው ፍቅርተ ካሳሁን ተናግራለች፡፡

አቶ ካሳሁን “እርዱኝ እርዱኝ” እያሉ ሲጣሩ አንድ የጽዳት ሠራተኛ ሰምታ ሰው በመጥራት ተረባርበው ካወጧቸው በኋላ ወደ ድንገተኛ ክፍል እንደወሰዷቸው የገለፀችው ፍቅርተ፤ ወደ 10 ሰዓት ገደማ ቤተሰብ ተጠርቶ ሲደርስ አቶ ካሳሁን በፅኑ ይተነፍሱ እንደነበርና ጣቶቻቸው ከመጋጋጣቸው በስተቀር የሚፈስ ደም እንዳልነበረ ጠቁማለች። ልብሳቸው በተቃጠለ ዘይት ተለውሶ እንደነበር ጠቅሳ ትንሽ ቆይቶ ሕይወታቸው እንዳለፈ ፍቅርተ ገልጻለች፡፡ አደጋው ስለተከሰተበት ሁኔታ ለማወቅ ዘውዲቱ ሆስፒታል ብንሄድም የሆስፒታሉ አስተዳዳሪ ዕረፍት ላይ ስለሆኑ ልናገኛቸው አልቻልንም። እሳቸው የወከሏቸው ሜዲካል ዳይሬክተር “አሁን ስብሰባ ላይ ነኝ፡፡ ስለጉዳዩ ድንገተኛ ክፍል ጠይቁ። ለእኔም የነገሩኝ እነሱ ናቸው” ብለውናል። ድንገተኛ ክፍል ስንጠይቅ በዕለቱ ተረኛ የነበሩትን ዶክተሮች አነጋግሩ የተባልን ሲሆን ተረኛ ዶክተሮቹ በበኩላቸው፤ ኦፕሬሽን እያደረግን ስለሆነ እስክንጨርስ ጠብቁ አሉን። ሆኖም ማተሚያ ቤት የመግቢያ ሰዓታችን በመድረሱ ምላሻቸውን ለማካተት አልቻልንም፡፡
አቶ ካሳሁን የ3 ወንዶችና የ5 ሴቶች አባት ነበሩ።

Source: Addis Admass Newspaper

The post የዘውዲቱ ሆስፒታል ሊፍት ሰው ገደለ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>