ከአምባገነን አገዛዝ ወደ ፍት ሃዊ ስርአት ለመቀየር ባገራችን እየተካሄደ የሚገኘዉን እረጂም አና እልህ አስቆራጭ (ላንዳዶችተስፋ አስቆራጭ) ትግል ወደፊት ለማራመድ የሚያስፈልገውን መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ሆነው በቆራጥነት ከሚታገሉሃይሎች ዉስጥ የሰማያዊ ታርቲ አንዱና ግንባር ቀደም ፓርቲ ነው። የዚህ ፓርቲ የሰላማዊ ትግል ስልት በኢትዮጵያ ተጨባጭሁኔታ አኳያ ሲታይ ዉጤት ሊያስገኝ የሚችል አካሄድ ነወይ? የሰማያዊ ፓርቲ በአገዝዙ እንደሌሎች ፓርትቲዎች እንዳይኮላሽእራሱን የሚጠብቅበት ስልት አለውን? በስርአቱ የይስሙላ ምርጫ በመሳተፍ ፓርቲው ለኢትዮጵያ ህዝብ ሊያስገኝ ያቀደውፋይዳ ምንድን ነው?
እነዚህንን እና ለሎችንም እጠያያቂ ጉዳዮችን ከኢትዮጵያዊያን ጋር ለመወያየት እንዲሁም ፓርቲዉ ለሚያደርገው ጥረት እገዛለመጠየቅ የታርቲው የወቅቱ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ገትነት በሰሜን አሜሪካ ጉብኝት ለማድረግ ሰሞኑን ይመጣሉ።
የዚህ ጉብኝት የመጀመሪያ ፕሮግራም በዋሺንግቶን ዲሲ በመጪው ቅዳሜ አፕሪል 4 ቀን ከቀኑ በ 2 ሰአት አርሊንግቶንቨርጂኒያ በሚገኘው ሸራቶን ፔንታገን ሲቲ ሆቴል ይካሄዳል። ሁለተኛዉ ፕሮግራም በቦስተን ከተማ እሁድ ኤፕሪል 5 ቀን ከቀኑብ 3 ሰእት በ 203 ሰመርቪል አቬኑ ሰመርቪል ማሳቹሴት ይካሄዳል
ይህን ፕሮግራም በጋራ በመተባበር ያዘጋጁት የአንድነት እና የሰማያዊ የሰሜን አሜሪካ የድጋፍ አሰባሳቢ ድርጅቶች ሁሉምኢትዮጵያዊያን በቦታው ተገኝተው የዚህ ዉይይት ተካፋ እንዲሆኑና ድጋፋቸዉን እንዲያሳዩ ባክብሮት ጥሪ ያቀርባሉ
ለበለጠ መረጃ
ኢሜል: info@semayawiusa.org
በስልክ: (202) 556-3078
ድረገጽ: www.semayawiusa.org
The post የሰማያዊ ታርቲ የስብሰባ ጥሪ appeared first on Zehabesha Amharic.