የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአራት የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ የእቃ አጓጓዥ አየር መንገዶችን ለማቋቋም እቅድ እንዳለው ብሉምበርግ የወሬ ምንጭ ዘገበ፡፡ አየር መንገዱ ከዚህ ቀደምም እንደ ማላዊ እንዲሁም የቶጎው አስካይ አየር መንገዶች ውስጥ ድርሻ እንደገዛና የባለቤትነት እጅ እንዳለው የሚዘነጋ አይደለም፡፡
አሁን ላይ ከናይጄሪያ መንግስት በኩል ለግዙፍ ባለኢኮኖሚ አፍሪካዊቷ ሀገር የእቃ ጫኝ አየር መንገድ በማቋቋም በኩል እንዲሳተፍ ጥሪ እንደቀረበለት የተነገረው አየር መንገዱ በሌሎች ሶስት የአፍሪካ ሀገራት ውስጥም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ለመጀመር በሚያስችል መንገድ ላይ ንግግሮች መጀመራቸውን የወሬ ምንጩ የአየር መንገዱን ዋና ስራ አስኪያጅ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ብሉምበርግ ዋና ስራ አስኪያጁን አቶ ተወልደ ገብረማሪያምን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ በሌሎች አየር መንገዶች ውስጥ ገብቶ የመሳተፍ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች አየር መንገዱ እንደቀረቡለትና ይህንን በሚመለከትም ተቋሙ የቢዝነስ ጥናቶችን በማካሄድ ላይ እንዳለ ተናግሯል፡፡
የኢትዮጵ አየር መንገድ በሰውም ሆነ በእቃ መጫን መጓጓዣ አገልግሎቶቹ ከአፍሪካ እጅግ ጠንካራ አየር መንገድ እንደሆነ ያስነበበው ዘገባው ለነዚህ በሽርክና የእንስራ ጥያቄዎች መቅረብም ዋነኛ ምክንያት ይሄው መሆኑን ነው የሚተነትነው
The post የኢትዮጵያ አየር መንገድን እንሻረክህ የሚሉ አየር መንገዶች መበርከታቸው ተዘገበ… appeared first on Zehabesha Amharic.