*** ለፍቅር በቀር*** (የቴዲ አፍሮ አዲስ ግጥም)
አትቁጠሩ ገንዘብ ንዋይ አትደርድሩ
በፍቅር በቀር ከንጉሱ ስለማታድሩ
ያላቹት አይገባውም ቋንቋው ይለያል
ፍቅር ብቻ ዘምሩለት ያኔ ይሰማቹሃል
መግባቢያው ነውና ፍቅር ያደገበት
ለህሊናው ሊኖር ኪሱን የጠላበት
ፍቅር ብቻ በሉት ካለበት ይመጣል
ከነፍስ ከስጋው ፍቅር ተዋህዷል
ግድ አይሰጠውም ገንዘብ ቢደረደር
ልቡ አይደነግጥም ለፍቅር በቀር
ሃብቴ ብሎ ይዟታል ቀሪ ንብረቴም
በፍቅር በቀር መንገስ አይፈልግም
አባት ነው አባትነት አይቼበታለው
ቸር ነው ያለውን ሲሰጥ አይቻለው
ፍቅር ነው ፍቅርን ሲዘምር ሰምቻለው
ይህ ብላቴና በመዋደድ ነው የሚያምነው
ከነፍስ ከስጋው ፍቅር ተዋህዷል
ፍቅር ብቻ በሉት ካለበት ይመጣልX2
The post ቴዲ አፍሮ ገንዘብ ለሚወዱና ለገንዘብ ለሚሞቱ አዲስ ግጥም ጻፈ appeared first on Zehabesha Amharic.