Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ድጋፍ ለማሰባሰብ ወደ ሰሜን አሜሪካ ያቀናሉ

$
0
0

የአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና የሰማያዊ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ የጋራ መግለጫ

በሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ እና የአንድነት ፓርቲዎች ድጋፍ አሰባሳቢ ድርጅቶች በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ይታወሳል። በስምምነቱ መሰረት የመጀመሪያው የጋራ ስራቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን የሰሜን አሜሪካ የስራ ጉብኝት በጋራ ማስተባበር አድርገው ጀምረዋል፡፡ በዚህም መሰረት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት በጋራ ኮሚቴው በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት በመጪው ሚያዚያ (ኤፕሪል) ውስጥ በሰሜን አሜሪካ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ፤ በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ምርጫ ውስጥ ለሚሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች ገንዘብ ማሰባሰብ ሲሆን፤ በተጨማሪም፤ በኢትዮጵያ የምርጫ ሂደት ምን ይመስላል፣ ምርጫው ውስጥ መቆየት ያለው ፋይዳ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አጠቃላይ ገፅታና እንቅስቃሴ ምን ይመስላል፣ በሚሉት ጥያቄዎች ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡ የፓርቲውን የሰላማዊ ትግል ስትራቴጂዎች በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ማስረዳትና በነዚህ ጉዳዮች እንዲሁም ባጠቃላይ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያዊያን ጋር ዉይይት ማኪያሄድም የዝግጅቱ አካል ነው፡፡

የጉብኝቱ ጊዜያዊ መርሃ ግብር እንደሚከተለው ሲሆን ወደፊት እነደየሁኔታው ሊቀየር፤ ሊጨመር፤ ወይም ሊቀነስ የሚችል መሆኑንም አስቀድመን እናሳስባለን።

የየከተሞቹ ዝርዝር ፕሮግራም በቅርቡ በመገናኛ ብዙኋን ይፋ የሚደረግ ሲሆን፤ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ባቅራቢያቸው በሚደረጉት የዉይይት መድረኮች ላይ ተሳታፊ በመሆን ስለኢትዮጵያ አገራችን እንዲሁም ስለወገናችን የወደፊት እጣፈንታ ዉይይት እንዲያካሂዱ ኮሚቴዉ ጥሪዉን ያስተላልፋል።

በየከተሞች የምትገኙ የሰማያዊ እና የአንድነት ድጋፍ ሰጪ ማህበራት አባላትም ይህ ፕሮግራም የተሳካ እንዲሆን የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድትለግሱ የጋራ ኮሚቴዉ ጥሪ ያደርጋል።

ከአክብሮት ሰላምታ ጋር

የሰማያዊ እና የአንድነት የሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች የጋራ ኮሚቴ

ለበለጠ መረጃ info@semayawiusa.org ኢሜል በማድረግ ወይም በ (202) 556 – 3078 መልክት በመተው አዘጋጅ ኮሚቴዉን ሊያገኙ ይችላሉ።

semawi

The post የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ድጋፍ ለማሰባሰብ ወደ ሰሜን አሜሪካ ያቀናሉ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>