ከኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጋር በውዝግብ ውስጥ ሆኖ የሰነበተው ዳና ድራማ አንዴ ሲቆም አንዴ ሲጀመር እዚህ ደርሷል:: ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ድራማውን እናንተ የማትጨርሱት ከሆነ እኔ እጨርሰዋለሁ በሚል እስከማገድም ደርሶ ነበር:: ሆኖም ግን ድራማው ከተወሰኑ ሳምንታት መቋረጥ በኋላ እንደገና የተጀመረ ሲሆን ሊጠናቀቅም ከ7 ክፍል የማይበልጥ እድሜ እንደቀረው ይነገራል::
የድራማው አዘጋጆች በዳና ድራማ ላይ ወሳኝ ገጸባህርይ የነበራትን አርቲስት ሜሮን ጌትነትን ያሰናበቱ ሲሆን እርሷን ተክታ ወጣቷ አርቲስት ዕጸሕይወት አበበ የህሊናን ቦታ እንደምትጫወት የደረሰን መረጃ ያመለክታል::
ከወራት በፊት በአዲስ አበባ በተዘጋጀ የግጥም መድረክ ላይ ባቀረበችው ግጥም በስርዓቱ ባለስልጣናት ጥርስ እንደተነከሰባት ሲገለጽ የነበረችው አርቲስት ሜሮን ጌትነት በአሁኑ ወቅት በሰሜን አሜሪካ እንደምትገኝ ዘ-ሐበሻ ያላት መረጃ ያመለክታል::
ሜሮን አሜሪካ የመጣችው ቀለበት ያሰረችለት ሰው ጋር አብራ ለመኖር ነው የሚሉ የቅርብ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ ቢገልጹም ከአርቲስቷ በኩል የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም::
የዳና ድራማዋ ሕሊና ካለ ሜሮን በ ዕጸህይወት እንዴት ይተወን ይሆን? – በቀጣይ ሳምንት የምናየው ይሆናል::
The post ሜሮን ጌትነት ከዳና ድራማ ተሰናበተች appeared first on Zehabesha Amharic.