“የአንድነት አመራር በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከተለዬ በኃላ በተሰጠው የሰባት ቀን እጩ የማስመዝገቢያ ጊዜ ውስጥ ለተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤቶች በ80 ምርጫ ክልሎች ተደራሽ በማድረግ 230 እጩዎችን ለማስመዝገብ ችለናል፡፡”
በምርጫ ቦርድ አሰራር፣ ለምርጫ የሚሰጡ የገንዘብ ድጎማዎች ፣ በኢቢሲ/ኢቲቪ የሚቀርቡ የቅስቀሳ ጊዜያቶችን ፣ ፓርቲዎች ባቀረቡት ተመራጮች ቁጥርና አሁን በፓርላማ ባላቸው መቀመጫ ቁጥር እንዲሆን ነው የተደረገው። ይህ አሰራር በእጅጉ ሕወሃትን እንደሚጠቅም የታወቀ ነው።
በዚህ መሰረት የሰማያዊ ፓርቲ በሚደረገው ምርጫ 7 ጊዜ ለአሥራ አምስት ደቂቃ መቀስቀስ እንደሚችል ተገልጾለታል። «በቂ ባይሆንም ያን ያህል ኢቢሲ/ኢቲቪ መፍቀዱ ጥሩ ነው» ሊያስብል ይችላል። ሆኖም ሕወሃት በአንድ በኩል ሲከፍት በሌል በኩል እንዴት ለመዘጋት እንደሚሞከር እናሳይ፡:
1) ሰማያዊ የሚያቀርባቸው የቅስቀሳ መልእክቶች ሳንሱር የሚደረጉ ናቸው። ከስድስት ጊዜ በላይ ኢቢሲ « ይሄን ካላስተካከላችሁ አናስተላልፍም» ብሎ መልሷል። እንድ ጊዜ እንደዉም አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ለም አደረጋችሁ በሚል ነው።
2) ሰማያዊ እንዲያቀርባቸው ከተፈቀደለት ሰባት ፕሮግራሞች አምስቱ እንዲተላለፉ የተወሰኑት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ( በፈረንጆች ነው። ወላጆች ልጆቻቸዉን ትምህርት ቤት ለመላክ ፣ ወደ እስራም ለመሄድ ደፋ ቀን በሚሉበት፣ ብዙዎች ከእንቅልፋቸው ሊነሱ በማይችሉበት ሰዓት ነው ።
የሕወሃቱ ኢቢሲ/ኢቲቪ ሆን ብሎ ሕዝቡ የሰማያዊ ፓርቲን መልእክት ለማዳመጥ እንዳይችል፣ ሲስተማቲክ በሆነ መንገድ ለማከላከል ለምን ፈለገ ? መልሱ አጭር ነው። ሕወሃት ከመቼዉም ጊዜ በላይ የፈራበትና በራሱ መተማመን ያልቻለበት ጊዜ ነው።
በነገራችን ላይ ለፓርላማ ወደ 480 ፣ ለክልሎች ደግሞ 1200 በላይ እጩዎችን አንድነት ፓርቲ ሊያስመዘግብ ተዘጋጅቶ እንደነበረ ሁላችንም እናዉቃለን። በሶማሌ ክልል በስተቀር ከአምስት መቶ በላይ በሆኑ የምርጫ ወረዳዎች ነበር አንድነት የሚወዳደረው። መረቡን ዘርግቶ በስፋት እየተንቀስቀስ ነበር። ሆኖም ባፈጠጠና ባገጠጠ መልኩ ህወሃት የኃይል እርምጃ ወስዶ፣ የአንድነትን ፓርቲ ጠፍጥፎ ለሰራው የትግስቱ ቡድን ሰጧል። አንድነት ማሸነፍ ብቻ ስይሂኦን ድምጽን የማስከበር አቅም እንዳለው ስላወቀ፣ ለምርጫ ቦርድ ቀጥታ ት እዛዝ በመስጠት አንድነት አገደ።
የአንድነት አባላት ሰማያዊን ተቀላቀሉ። ሰማይዊ የበለጠ ተጠናከረ። ከ400 በላይ የፓርላማ እጩዎች አስመዝገበ። ከ200 በላይ የሚሆኑትን ያለ ምንም ምክንያት ምጫ ቦርድ ሰረዘ።
አይ የወያኔ/ሓወህት አስቂኝ ምርጫ ! ከዚህ በፊት በምርጫው ቀን ነበር የሚያወናብዱት። በዚህ አመትማ ለይቶላቸዋል። ምርጫዉ ከመድረሱ ሶስት ወር በፊት ሰዎቺ እየተደናበሩ ነው !!!!
በከዚህበፊት ምርጫ ሕዝብ መርጦ ፣ ድምጹ ነበር የሚሰረቀው። ሕወሃት የድምጽ ሌባ ሰራቂና አጭበርባሪ ነበር። አሁን ግን ሕወሃት መራጭ የሆነበት ምርጫ ነው። አንዱን ፓርቲ እንዲወዳደር፣ ሌላውም እንዳይወዳደር ያደረገ፣ እጩዎች እየሰረዘ አትወዳደሩም በማለት መራጭ የሆነበት ምርጫ ነው! ሕወሃት ድሮ ያደርግ የነበረዉን ማስመሰል እንኳ ትቶ ፍጹም አምባገነን መሆኑን ያሳየበት ምርጫ ነው።
The post አንድነት ራስ ምታቱ ነበር ፣ አሁን ደግሞ ሰማያዊ ሆድ ቁርጠቱ ሆነ – ግርማ ካሳ appeared first on Zehabesha Amharic.