Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: በርናንድ ላጋት የኃይሌን ክብረወሰን ለማሻሻል ብዙ መስራት እንደሚጠበቅበት ተናግሯል

$
0
0

ከዳንኤል ዘነበ
lagat

የአምስት ጊዜው የቤት ውስጥ ና ከቤት ውጪ የዓለም ሻምፒዮኑ በርናርድ ላጋት በማንቸስተር ከተማ በሚካሄደው የ10ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር አዲስ ክብረወሰን ለማስመዘገብ እንደሚሮጥ አስታውቋል።

ትውልደ ኬንያዊው የአርባ ዓመት አሜሪካዊው ሯጭ ላጋት በቤት ውስጥ ውድድር ከአርባ ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸው አትሌቶች ያስመዘገቡትን ክብረወሰን ለማሻሻል በአውሮፓ ታላቅ በሚባለው የማንቸስተር ከተማ ሩጫ ለመወዳደር እቅዷል። ይህ ክብረወሰን የተያዘው በጀግናው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ሲሆን፣ ሰዓቱም 28 ደቂቃ ከ00 ሰከንድ ነው።

በፍላግ ስታፍና አሪዞና ጠንካራ የሆነ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው ላጋት « ነገሮች ቀላል ላይሆኑ ይችላሉ፤ ይህን ክብረወሰን ለማሻሻል አምስት ኪሎ ሜትርን በአስራ አራት ደቂቃ መሮጥ ይጠበቅብኛል፤ ይህን ፈጣን ሰዓት ማሻሻል ቀላል ባይሆንም የተቻለኝን ጥረት አደርጋለሁ» በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል።
ላጋት እ.ኤ.አ 2007 በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና ላይ 1500ና 5000 ሜትር ከማሸነፉ ባሻገር የዓለም የቤት ውስጥ 3000 ሜትር ሩጫንም ለሦስት ጊዜ አሸንፏል። የ5ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ሁለት ጊዜ ተካፍሎ ጥሩ ተፎካካሪ የነበረው ላጋት በአንድ የግማሽ ማራቶን ውድድር ተካፍሎም 10ኪሎ ሜትሩን በ29ደቂቃ ከ40 ሰከንድ ማገባደድ ችሏል።

በ1500ሜትር የክብረወሰን ባለቤት ከሆነው ከሞሮኳዊው ሂችሃም ኤልግሩዥ ቀጥሎ በርቀቱ ፈጣን ሰዓት ያለው ትውልደ ኬንያዊው ላጋት እንደ ማንቸስተር ዓይነት ባሉት ታላላቅ የጎዳና ላይ ውድድሮች ተሳትፎ አያውቅም።በዚህ የተነሳም ክብረወሰኑን በእርግጠኛነት እንደሚያሻሽለው ለመናገር አልደፈረም። ነገር ግን በዩኒቨርሲቲ ደረጃ እያለ በአስር ኪሎ ሜትር አገር አቋራጭ ውድድር ተሳትፎ ጥሩ የሚባል ሰዓት እንደነበረው አስረድቷል።

ባለፈው ህዳር 40ኛ ዓመቱን ያከበረው የዓለማችን ምርጡ የረጅምና የመካከለኛ ርቀት ሯጭ ላጋት ባለፈው ዓመት በ300 ሜትር የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ላይ ተካፍሎ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኗል። በአምስት የኦሊምፒክ መድረኮች ላይ በመካፈልም ጥሩ ልምድ በማካበቱ በሚቀጥለው ዓመት በሪዮ ዲጄኔሮ በሚካሄደውና በመጪው ክረምት በቤጂንግ የዓለም ሻምፒዮና በ5000ሜትር ተካፋይ እንደሚሆንም ይጠበቃል።
ላጋት የሦስት ሺ ሜትር የቤት ውስጥ ክብረወሰንን ለሦስተኛ ጊዜ ያሻሻለው ባለፈው ሳምንት በፈረንሳይ ሜዝ ከተማ በተካሄደው ውድድር ላይ ነው።በውድድሩ ያስመዘገበው አዲስ ሰዓትም 7፡37፡71 ነው። ላጋት በኒውዮርክ ሚልሮዝ ጨዋታዎች ላይ ተካፍሎ በኢሞን ኮግላን ተይዞ የነበረውን ከአርባ ዓመት በላይ የማይል ክብረወሰን በ3፡54፡91 ማሻሻል ችሏል።
HAMBURG MARATHON 2014..DUEL OF GIANTS…HAILE GEBRESILASSIE vs MARTIN LEL

ላጋት ባለፉት አስራ ስምንት ቀናት ውስጥ ስድስት ያህል የዕድሜ ክብረወሰኖችን በማሻሻል አስደናቂ ብቃቱን ማሳየት ችሏል። « ማኔጀሬ ስለ ማንቸስተር አስር ኪሎ ሜትር ውድድር ኃይሌገብረስላሴና ቀነኒሳ በቀለን የመሳሰሉ አትሌቶች እንዳሸነፉበት አጫውቶኛል» ያለው ላጋት የእነዚህን ታላላቅ አትሌቶች ፋና መከተል እንዳለበት እምነቱን ገልጿል።

ላጋት ኃይሌ ገብረስላሴን ክብረወሰን ለማሻሻል ጠንካራ ዝግጅት ማድረግ እንዳለበትም አምኗል። « ግማሽ ማራቶንን በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኜ ሮጫለሁ፤ አሁንም ጥሩ ዝግጅት ካደረኩኝ የተሻለ እሰራለሁ ብዬ አምናለሁ» በማለት ላጋት አስተያየቱን ሰጥቷል።

The post Sport: በርናንድ ላጋት የኃይሌን ክብረወሰን ለማሻሻል ብዙ መስራት እንደሚጠበቅበት ተናግሯል appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>