በርካታ የኤርትራና አፍቃሪ ህወሀት/ኢህአዴግ ብሎጎች፣ የህወሀት/ኢህአዴግ ደጋፊ ካድሬዎች እንዲሁም የተቃዋሚ ደጋፊ መስለው የሚንቀሳቀሱ ድረ-ገጾች በአንድላይ “መንግስቱ Mengistu_Haile_Mariam ሀይለማርያም አረፈ” የሚል ዜና በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ ጉዳዩን አንድም ነብስ ያለው የዜና አውታር አልዘገበውም።
ይህን አስመልክቶ ታዋቂው የኢሳት ራድዮ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን የሚከተለውን በፌስቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል፣
ኮነሬል መንግስቱ ኃይለማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ፌስቡኩን ድረ-ገጹን የወረረ ምንጭና ፍንጭ የሌለው ወሬ በግሌ ወረርሽኙ ሲዛመት ለማጣራት ያሉኝን መንገዶች በሙሉ ተጠቀምኩ ደወልኩ ነዘነዝኩ ምንም የለም ሊንክ ተደርገው የተለጠፉና ምንጭ ተብለው የተጠቀሱትን በሙሉ አየሁ በረበርኩ ዋንኛ ምንጭ የተባለው ድረ ገጽ ከሶስት ሳምንት በፊት የለቀቀውና ውሸት መሆኑ ወዲያውኑ ኢሳት ያረጋገጠው ነበር ሌላው የዙምባቡዌ ቴሌቪዥን ተናገረ የተባለው ነው ሲከፈት ግን ምንም የለም እና ወሬው ከየት መጣ የበዓሉ ግርማ በህይወት አለ ወረርሽኝ ለማንኛውም እስከዚህ ሰዓት ድረስ ባለኝ መረጃ ኮነሬል መንግስቱ ኃይለማያም በህይወት አሉ።
ሀና መታሰቢያ በመባል የምትታወቅ የፌስቡክ ተተቃሚ ደግሞ እንዲህ ብላለች፣
ፌስቡክን ሙሉ ለሙሉ መዝጋት ፖለቲካል ኪሳራው ከባድ መሆኑን የተረዱ የሚመስሉት ወያኔዎች ከዚህ ይልቅ ለየት ያለ መንገድ እየተከተሉ ነው።ፌስቡክ ውስጥ እየተፈጠሩ ያሉት አባዛኛዎቹ አሉባልታዎች ምንጭ ወያኔዎች ይመስሉኛል። በአጠቃላይ ፌስቡክን በተመለከተ የወያኔ ፕሮፐጋንዲስቶች እየተከተሉ ያሉት መንገድ፦
1. ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የሚካሄድባቸውን ግሩፖችና ገፆችን ነጥሎ መዝጋት(ምንም እንኳን በhttps://መከፈት ቢችሉም)
2. ፌስቡክ ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ ግለሰቦችን አካውንት መዝጋት
3. መንግስትን የሚያወግዙ ፖስተሮችና ፅሑፎች ስር ከርዕሱ ባፈነገጠ መልኩ ፖስት ያደረገውን ግለሰብ በመዝለፍ የውይይቱን አቅጣጫ ማሳት
4. ፌስቡክ ላይ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉ ግለሰቦችን ሜሴጅ እየላኩ ማስፈራራት፣ በስድብና በዛቻ ማሸማቀቅ
5. ምንም እንኳን ማንኛውንም ነገር ያለ ፕሮግራም መጠቀም ጊዜን ማባከኑ እሙን ቢሆንም ወያኔዎች ስለፌስቡክ ጊዜ አጥፊነት የሚሰብኩት ለኛ በማዘን አይደለም ስለሚጠፋ ጊዜ ከምር ቢጨነቁ ሀገሪቷን የወረሯትን ጫት ቤቶች በዘጉ ነበር እስካሁን የፌስቡክን ጉዳት እና ጊዜ አጥፊነት በተመለከተ በወያኔ ሚዲያዎች ከ3 ጊዜ በላይ ፀረ ፌስቡክ ዝግጅቶች ቀርበዋል
6. አዲሱ የወያኔ ፕሮፐጋንዲስቶች ታክቲክ መያዣ መጨበጫ የሌላቸውን አሉባልታዎች በፌስቡክ በመንዛትና በማሰራጨት የፌስቡክን ተአማኒነት በመቀነስ ፌስቡክ የቦዘኔዎች ብቻ መሰብሰቢያ የሚመስል ገፅታ እንዲላበስ ማድረግ በዚህ መንገድ ከተነዙ አሉባልታዎች ውስጥ የልመንህ ሞት፥ የበአሉ ግርማ በህይወት ተገኘ መባል እና የዛሬው የመንጌ ሞት ይጠቀሳል።
እኛ ጭቁን ኢትዮጵያውያን ጉዟችን እሩቅ ነውና በጅላጅል አሉባልታዎች ሳንዘናጋ ፌስቡክን እንደ መወያያ እና መገናኛ መድረክ እንጅ እንደዋነኛ የትግል አውድ ሳንወስድ ትግላችንን እናበርታ።