Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ኢትዮጵያዉያን አይደሉምን ? ታዲያ ለምን?

$
0
0

አበራ ሽፈራው                                                      

 ከጀርመን                                                                                                  

አበራ ሽፈራው

አበራ ሽፈራው

የኢትዮጵያዉያንን ችግር ያባባሰዉ ጉዳይ ህወሐት / ኢህአዴግ እንድንለያይ ከመታወቂያችን ጀምሮ እየጸፈ የስጠን የብሄርህ ማነዉ ጥያቄ አንዱ ነዉ ለማለት ያስደፍራል።የዚህ ጥያቄ ክፋታዊ እቅድ እውስጣችን ሳናዉቀዉ አድጎና ቅርንጫፍ አዉጥቶ በመቀጥሉና ከዉስጣችን ባለመጥፋቱ ጉዳቱ አሁን አሁን ጐልቶ እየታየ ነው ። በዚህም ምክንያት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እራሱን አጥብቦ እንዲያይና  ከጎሳ አልፎ ወደ ጎጥ እንዲወርድ ተደርጓል። ይህም ኢትዮጵያዊነቱን እየጎዳ እንዳለ ይታያል ። ከዚህ የተነሳ ህወሐት እንደፈለገዉ ህዝቡን እንዲጨቁን እድል እንደፈጠረለት ልንገነዘብ ይገባናል ። እዚህ ላይ ግን ኢትዮጵያዊያን ስለጎሳቸዉ ፣ስለባህላቸውና ስለቋንቋቸው እንዲሁም ሌሎች ማንነታቸዉን በሚገልጹ ጉዳዮች ላይ አያስቡ ወይም አይሳተፉ ማለቴ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ።

 

በየትኛውም ጎሳና ክልል ልወለድ ፣የትኛውንም ቋንቋ ልናገር ፣የትኛዉም ባህል ይኑረኝ አንድ ነገር ይገባኛል፤እርሱም ኢትዮጵያዊ መሆኔ።ኢትዮጵያዊ ነኝ ካልኩኝ ደግሞ የተወለድኩበት ወይም ያደኩበት ማህበረሰብና ቦታ ብቻ ሳይሆን ከሰሜን እስከ ደቡብ ፣ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያለው ሁሉ የኢትዮጵያ የምድር መዳረሻ ሁሉ የእኔም ሃብትና ንብረት መሆኑ፤መኖሪያዬ መሆኑ ፤ህዝቡም ወገኔ መሆኑ፤ የህዝቡም ችግር የእኔም ችግር መሆኑ፤ የህዝቡ ደስታም የእኔም ደስታና ሃዘኑም ሃዘኔ መሆኑም ጭምር ነው ።

 

በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊነቴ ሁሉንም የሚወድ፣የሚቀበል፣ባህላቸዉንና ታሪካቸውን የሚያከብር መሆን ይኖርበታል። ኢትዮጵያዊነቴ የማያዳላና ራሱን ብቻ የማይወድ መሆን ይኖርበታል። ኢትዮጵያዊነቴ አንድነትን በልዩነት ዉስጥ ወይም ልዩነትን በአንድነት ውስጥ ተቀብሎ የሚጓዝ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። ኢትዮጵያዊነቴ ከጎሳና ከዘር ይልቅ ለሰብአዊ መብት መከበር ቅድሚያ መስጠት አለበት። ኢትዮጵያዊነቴ ሁሉንም የአገሪቷን ህዝቦች በእኩልነት የሚመለከት መሆን አለበት። ኢትዮጵያዊነቴ አገራዊ ፣ ሰፋ ወደ አለና ለትውልም ጭምር ማሰብ አለበት ።

አንድ ነገር ሁሌ ያሳዝነኛል ።እርሱም ህወሐት የአገሪቷን ህዝብ ከፋፍሎ ለመግዛት የተጠቀመበት በማር  ውስጥ  የተቀበረ ሬት የሆነዉ ይህ ተግቶ ለመለያየት የሰራበት ክፋታዊ እቅዱ ምን ያህል ዘልቆ በኢትዮጵያዊያን ላይ ተጽዕኖ እንደፈጠረ ነው ። ለማስረጃነት ያህልም በሃገር ውስጥ ከሚታየዉ ልዩነት ይልቅ በውጭዉ ያለን ኢትዮጵያዊያን በዚህ ችግር ተተብ ትበን ለመቀራረብ ትልቅ ማነቆ ሆኖ መቆየቱ ግልጽ ነዉ ።ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ችግሩ እየተሰበረ መምጣቱና መሻሻል እየታየበት መሆኑ ደስ የሚያሰኝ ጅምር ነው ።ይህም በህወሐት መንደር ትልቅ ድንጋጤ እንደሚፈጥር ይታወቃ ል።የአንድ አገር ህዝቦች ሳለን ላለፉት የህወሐት የገዥነት አመታት ሆድናጀርባ ሆነን የቆየንባቸዉን ችግሮች ለመፍታት እንነሳ። በዚህም ለወደፊቱም የሚፈጠሩ ችግሮችን አሁን እየፈታናቸው እንድንሄድ ያስችሉናል።

ይህንን ጉዳይ ለመቅረፍ ከጸሐፊዎች፣ከጋዜጠኞች፣ከፖለቲከኞችና በዚህ ዘረኛ መንግስት የተጠቁ ሁሉ ሊያስቡበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብዬ አምናለሁ ።ትኩረትም ተሰጥቶት መነጋገር ቢቻል ተገቢነዉ እላለሁ ።

ለጽሁፌ መነሻ የሆነኝ ጉዳይ በቅርቡ በአገራችን ኢትዮጵያዊያ ጋምቤላ ክልል በህዝቡና በመሬቱ ላይ እየተፈጸመ ስላለዉ ጉዳይ ወደ ኢንተርኔት ስገባ የተመለከትኳቸው ጽሁፎች ናቸዉ ።የተወሰኑ ኢትዮጵያዉያን በጉዳዩ ላይ ጽፈዋል።በዋናነት ግን የጻፉት የውጭ ሰዎች ወይም ሚዲያዎች ናቸዉ ። የኢትዬጵያ ሳተላይት ቴሌቨዥንና ሬዲዬ /ኢሳት/ ሽፋን ሰጥቶታል።ይህ በጋምቤላ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ህዝብ ባለፉት ዓመታት ከደረሰበት የዘር ማጥፋት ዘመቻ ሳያገግም በተከታታይ የሚደርስበትን የተቀናጀ ጥቃት መስማትና ማየት ሁሉንም ኢትዮጵያዊያንን የሚያም ድርጊት ነዉ ብዬ አምናለሁ ።አሁንም በዚህ ህዝብ ላይ የሚፈፅመዉ ግፍ አላቆመም ቀትሏል።

ሂዪማን ራይት ዎች እንደ ጊርጎርያን አቆጣጠር በማርች 24 /2005 ባወጣዉ ረፓርት ላይ እንደገለጸዉ በዲሴምበር 13/2003 በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት 43ኛ ክፍለ ጦር እና ሌሎች ስቪል ታጣቂዎች በጋምቤላ በአኟኮች ላይ የተፈጸመዉ ግፍ ቀላል እንዳልነበር ገልጻል። ጥቃቱም ዒላማ ያደረገዉም ወንዶችን እንደነበረና ከዚህም በተጨማሪ ሴቶች በወታደሮች ተደፍረዋል።በዚህ ጥቃት 424 ሰዎች መገደላቸዉን ጽፏል።ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ሰዎች ህይወታቸዉን ለማዳን ወደጫካ መሽሻቸዉን፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመጠለል መገደዳቸዉን፣ወደከተማ በመሄድ ቅርብ ዘመዶቻቸዉጋ ለመጠለል እንደሞከሩና ሌሎችም ከሃገር መሰደዳቸዉን ገልጻል።ለበለጠ መረጃ www.hrw.or HYPERLINK “http://www.hrw.org/”g መመልከት ይቻላል።

ከዚህ በጨማሪ የአኟክ የፍትህ ካዉንስል /Anuak Justice Council/ ስለዚሁ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲያብራራ በዚሁ ቀን ማለትም በዲሴምበር 13/2003 424 ሰዎች መደብደባቸዉንና ከዚያም መገደላቸዉን ጽፏል።ድርጊቱ የተፈጸመዉ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደሮችና በሌሎች አናሳ ነዋሪዎች በተቀነባበረ የጅምላ ጭፍጨፋ እቅድ እንደሆነ ገለጿል።ከዚህ ጊዜ በኋላም 2,500 ሰዎችም በተጨማሪ መገደላቸዉን ጽፏል።በዚሁ የግድያ ወቅት በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ተቃጥለዋል፣በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ተደፍረዋል፣የሚመገቡአቸዉ እህሎችና የቤት እንስሳትም ወድመዋል፣አኟክ ፓሊሶች ትጥቅ እንዲፈቱ ተደርጓል፣በመንግስት ስልጣን የነበሩ ተወግደዋል።ከዚህም የተነሳ ከ51,000 በላይ አኟኮች ክልሉን ጥለዉ እንዲሰደዱ ተደርጓል።ለበለጠ መረጃ Anuak Justice Council ዌብ ሳይትን  HYPERLINK “http://www.anuakjustice.org/”www.anuakjustice.org መመልከት ይቻላል።

አሁን ደግሞ በዚሁ በአገራችን ኢትዮጵያዊያ የጋምቤላ ክልል ህዝቡን በግድ በማፈናቀል 42% የሚሆነዉንና በስፋቱ ከኒዘርላንድ አገር ጋር ሊወዳደር የሚችልን መሬት በግፍ ከህዝቡ ነጥቆ በማን አለብኝነት ለውጭ ሰዎችና ለህወሐት ደጋፊዎች በልማት ስም ለመሸጥ የሚደረገዉን እያየን ምነዉ ዝም አልን?። በዚህ ዙሪያ እየሰሩ ያሉና እየታገሉ ያሉትን ሳላመሰግን አላልፍም ።ጉዳዩ የሁላችንም ነዉ፤ ስለሆነም ለምንዝም እንዳልን እራሳችንን በመጠየቅ ዝምታዉ ይሰበር።

 

ትኩረት ያልሰጠነዉ ካለን ቀላል ነገር አይደለምና ትልቅ ትኩረት ልንሰጠዉ ይገባል እላለሁ።ዛሬ ወገኖቼ አንድ ነገር በድፍረት እጠይቃለሁ። ኢትዮጵያዊያዊ ነህ/ሽ ?።አዎ ካልከኝ/ሽኝ ለዚህ ችግር ሌላ ሰዉ የለምና ይህም ችግር አሳሳቢ ነዉና ሌላ ጊዜ ለወገንህ እንደተሰበሰብህ ፣ሰልፍ እንደወጣህ፣እንደተቃወምህ ዛሬም ትልቅ ሊያዉም ተደጋጋሚ ችግር በህዝቡ ላይ እየደረሰ ይገኛል።ይህ የህዝቡ መከራ የሁላንም ችግር ነውና ሁላችንም ኢትዬጵያውያን በችግሩ ላይ እንሰባሰብ፣ሰልፍ ይደረግ ፣እንቃወም ፣መፍትሔም እንፈልግ ፣የፓለቲካ ፓርቲዎችና ስቪክ ማህበራትም ስብሰባቸዉ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተዉ ይነጋገሩበት መፍትሄም ያስቀምጡለት።ጉዳዩ በሰብዓዊ ፍጡር ላይ የሚፈጸም ትልቅ ግፍ ነዉና ዝምታዉ ይሰበር።

ከዚህ በፊት በዚሁ ክልል የተፈጸመዉን ግፍ ኢትዬጵያዉያን  እንዳናውቀዉ ተደርጎ ነበር።ነገር ግን ጉዳዩ በጥቂት ሰዎች ጥረት በዓለምና በኢትዬጵያውያን ዘንድ እየታወቀ ከመጣ በኋላ እጅግ ብዙ ህዝብን ያስደነገጠ ነበር ። የህወሐትን ጭካኔንም ያሳየና በታሪክም ለዘመናት የማይረሳ ድርጊት ሆኖ ተመዝግቧል ። ዛሬ ደግሞ በማን አለብኝነት በጋምቤላ ህዝብ ላይ ትልቅ ፈተና ተጋርጧል ። ፈተናዉ የሁላችንም ፈተና ነዉና በዚህ መጥፎ የታሪክ አጋጣሚ ለህዝባችን አለኝታነታችንን ልናረጋግጥለት ይገባል። በዚህም የህወሐት የመከፋፈል ሴራ በተግባር ይፈነቃቀል ። ይህንን ትልቅ የሃገር ጉዳይ በዝምታ ማየቱ ተገቢ አይደለምና ዝምታዉ  ይሰበር።እንደኔ  ሁሉም እራሱን እንዲጠይቅ እመክራለሁ ፤ካልሆነ ግን በታሪክ አጋጣሚ እኛም ከመጠየቅ አናመልጥም ።

 

እግዚአብሔር  ኢትዮጵያን  ይባርክ

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles