የኢትዮጵያ ሀገራችንና ህዝባችን ሰቆቃና በደል ከጊዜ ወደጊዜ እይባሰ በመሄድ ላይ ይገኛል። የዜጎች የኑሮ ዋስትና ከዕለት ዕለት ጥያቄ ውስጥ እየገባ ነው። ምንም እንኳን የበደሉን ጥልቀት መዘርዘር ለቀባሪው አረዱት ቢሆንም ባጭር ሀርጎች ብንጠቅስ፤ የጨቋኙና የከፋፋዩ የህውሀት ወያኔ አገዛዝ የህዝቦቿን መከባበርና አንድነት በጥላቻና በመከፋፈል ለመተካት የሚጥርበት፤ ዜጎች አላግባብ የሚታሰሩባት፣ የሚገደሉባት፤ የሚሰደዱባት፤ ነፃ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ የማይካሄድባት፤ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ከቀዬአቸው የሚፈናቀሉባት፤ ለሕግ ተገዢ ያልሆነ ፍጹም አምባገነናዊ ሥርዓት ያለባት፤ ዜጎች የገዢው ፓርቲ አባል ካልሆኑ በነፃነት ሠርተው መኖር የማይችሉባት፤ በተግባር ያልዋለ ህገ-መንግሥት ያላት፤ ከገዢው ፓርቲ ቁጥጥርና ነፃ የሆኑ የመገናኛ ብዙሀንና የማህበረሰብ ድርጅቶችና የሌሉባት፤ የኃይማኖት ነጻነት በፖለቲካ የበላይነት የሚመራባት፤ በሀገሪቱ የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት-የምርጫ ቦርድ፤ ፍርድ ቤቶች፤ ፖሊሶች፤ የደህንነት መስሪያ ቤቶች፤ መከላከያና ሌሎች የገዢው ፓርቲ ፖለቲካ መጠቀሚያ የሆኑባት፤ ዜጎች እንደ ሰው በሃገራቸው የመኖር መብቶች በሌለበት፤ የእድገት ምልክቶች ናቸው ተብለው የተሰሩ ህንፃዎችና ቤቶች በቁመታቸው ባዶ ሆነው መገኘታቸው እንደ ብሄራዊ ልማት የሚቆጠርባት፤ ወጣቶች ተምረው በሃገራቸው ሰርተው ለመኖር ስለማይችሉ የሚሰደዱባት ወዘተ ሀገር ሆናለች።
—-[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—
The post ከኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል (ሸንጎ)ና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC) ሁሉን አቀፍ የሆነ አማራጭ ኃይል ተወያይቶና ተስማምቶ ስለማቋቋም አስፈላጊነት የተሰጠ የጋራ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.