ዛሬ ከላስቬጋስ አልፎ በመላው አለም ተደማጭ የሆነው የህብር ሬዲዮ፤ 5ተኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በመጭው ረቡዕ ፊብርዋሪ 25ቀን2015 በቬጋስ ጎልድ ኮስት ሆቴል ያቀደውን ታላቅ ስብሰባ ሆቴሉ ረቡዕ ማካሄድ አይቻልም ብሎ በመሰረዙ፤ በዚያው በቬጋስ ወደሚገኘውሐምፕተን ኢን ሆቴል በዕለቱ በተመሳሳይ ሰዓት እንደሚያካሂድ የህብር ሬዲዮ ዝግጅት ክፍል ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ ገለፀ።
የአድዋ ድል 119ኛ ዓመት በሚዘከርበት፣ ወቅታዊ የአገር እና የጤና ጉዳይ ዋና መወያያ በሆነበት፣ በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ አቶ ኦባንግሜቶ ከካናዳ፣ የዘ-ሐበሻ ድህረ ገፅና ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሄኖክ አለማየሁ ከሚኒሶታ፣ እውቁ ዩሮሎጂስት ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን ከቬጋስበሚገኙበት፤ አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የዓለም አቀፍ ፍትህ የኢትዮጵያውያን ጉዳይ ዋና ስራ አስኪያጅ የሚሳተፉበትን ይህን ስብሰባ ሐሙስ እንጂረቡዕ ሊካሄድ አይችልም ሲል አስቀድሞ የተገባውን ውለታ አፍርሶ ዝግጅቱን ሰርዟል።በዚህ ከአቅማችን በላይ በሆነ ምክንያት የስብሰባውንቦታ በዕለቱ በሐምተን ኢን ሆቴል ለማድረግ ተገደናል።
ጎልድ ኮስት ሆቴል ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ፌብርዋሪ 12/ 2015 በላከው የስልክ መልእክት የህብርን 5ተኛ ዓመት ዝግጅት የሰረዘ መሆኑንአሳውቀውናል። ከዚያ በኋላ በተደረገው ውይይት ረቡዕ ስብሰባው አለመደረጉ በህብር ላይ ጉዳት ያደርሳል ብለን ገልጸናል። በዚህ ሳቢያዝግጅቱን በመጭው ዕረቡ በቬጋስ ትሮፒካናና ዲን ማርቲን ላይ በሚገኘው ሐምፕተን ኢን ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሄድ የህብርዝግጅት ክፍል ገልጿል።
የህብር ሬዲዮ 5ተኛ ዓመት በዋነኛነት የሚመጡ እንግዶች ባሉበት ስብሰባውን በተሳካ መንገድ ማድረግ ነው የወቅቱ ትኩረታችን የሚለውየህብር ሬዲዮ መግለጫ ባለፈው ዓመት በጎልድ ኮስት ሆቴል 4ተኛ ዓመታችንን ፌብርዋሪ 26/2014 በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን አስታውሷል።
ህብር ሬዲዮ የወቅታዊ መረጃ ምንጭ በመሆን በወቅታዊ አገራዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ፣በኢኮኖሚ፣ በጤና እና በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ላይሰፊ ትኩረት በመስጠት አቅም በቻለው መጠን የአማራጭ የሚዲያ ተግባሩን እያከናወነ መቆየቱን ይሔው መግለጫ ጠቅሶ ህ/ሰቡ በቬጋስናበአካባቢው የሚኖሩ የኢትዮጵያ ወዳጆች በመጭው ረቡዕ ፌብርዋሪ 25 ቀን 2015 በ5 ፒኤም ትሮፒካናና ዲን ማርቲን ላይ በሚገኘውየሀምፕተን ኢን ሆቴል በሚካሄደው በዚህ ታላቅ ስብሰባ ላይ በመገኘት የተሳካ ዝግጅት እንዲደረግ የህብር ሬዲዮ አጋር እንዲሆኑ መግለጫውጥሪውን አስተላልፏል።
The post በቬጋስ የህብር ሬዲዮን 5ተኛ ዓመት ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባጎልድኮስት ሆቴል እንዲካሔድ ባለመፈቀዱ ወደ ሐምተን ኢን ሆቴል እንዲዛዋወር ተደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.