(ምኒልክ ሳልሳዊ) በምእራብ ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ክልል ደቡባዊ አቅጣጫ ቶንጎ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በታጣቂ ሃይሎች እና በወያኔ ወታደሮች መካከል ለሊቱን ከባድ ውጊያ መደረጉን ለታጣቂ ሃይሎቹ ቅርብ ነን ያሉ ምንጮች ከማላካል አስታውቀዋል::
ከደቡብ ሱዳን ማላካል ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ ተነስተው በምእራብ የኢትዮጵያ ድንበር ከሚገኙት የወያኔ ሰራዊት ጋር ውጊያ የገጠሙት ታጣቂ ሃይሎች በስርአቱ በደል ደርሶባቸው የሸፈቱ እንደሆነ ምንጮቹ ሲገልጹ ለሊቱን ከባድ ውጊያ ያካሄዱ ሲሆን ከታጣቂ ሃይሎቹ 26 ሰውች መሰዋቱን ምንጮቹ ተናግረዋል::
በጋምቤላ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በስርአቱ ከባድ በደል እየደረሰባቸው ሲሆን ምንም አይነት የልማት መዋቅር ካለመዘርጋቱም በላይ ከየአከባቢያቸው እየተፈናቀሉ መሬታቸው ለውጪ ባለሃብት እንዲሁም ከትግራይ መጥተው ለሰፈሩ አልሚዎች ለተባሉ የትግራይ ተወላጆች እየተሰጣብቸው ለስደት ለስራ አጥነት እና ለድህነት ተዳርገዋል::እነዚህ የስርአቱ በደል አንገሽግሿቸው ደቡብ ሱዳን ጫካ በመግባት ራሳቸውን ያደራጁ ታጣቂ ሃይሎች የወያኔን ወታደሮች መዋጋታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል::
የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለነጻነቱ እና ለመብቱ በሚያደርገው ትግል በአንድነት መነሳት አለበት አለበት ያሉት ምንጮቹ ራሳችንን ከበደል እና ከብዝበዛ ለማዳን ጠንክረን ልንታገል ይገባል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል::
The post በምእራብ ኢትዮጵያ ቶንጎ አካባቢ ሌሊቱን ውጊያ ሲደረግ ማደሩ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.