ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው በፌስቡክ ገጹ እንዳስታወቀው በርካታ ንፁሃን ወንድሞቻችን ከመዲናችን አዲስ አበባ እየታደኑ ነው።
“ህወሃት መራሹ ወያኔ አሁንም ንፁሃን ሙስሊሞችን ከየአካባቢው ማደነኑን ቀጥሏል።” ሲል ዘገባውን የጀመረው ጋዜጠኛው በዛሬው እለት በብርጭቆ አካባቢ ኮንዶሚኒየም ይኖር የነበረው ወንድማችን የሆነው እና የቢላል ሬዲዬ ጋዜጠኛ የነበረው ፣ ከአመት በፊት በረመዳን ወር መግቢያ ላይ በ3ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው ጋዜጠኛ ካሊድ ሙሃመድ በዛሬው እለት የፈጅር ሰላቱን ሰግዶ ወደ ቤቱ በሚመለስበት ወቅት በደህንነት ሀይሎች ታፍኖ እየተደበደበ ወዳልታወቀ ቦታ ተወስዷል ብሏል::
እንደ ጋዜጠኛው ዘገባ ካሊድ መሃመድ ከቤቱ ውስጥም ላፕቶፖችን ጨምሮ በርካታ የሚገለገልባቸውን ንብረቶች ተወስዶበታል:: ካሊድ በአሁኑ ወቅት የ2 ወር ልጅ ያለው ሲሆን በዛሬው እለት የደህነነት ሃይሎች በአራስ ባለቤቱ ላይም ከፍተኛ ድብደባ እንደፈፀሙ ለማወቅ ተችሏል።
The post የሕወሓት አስተዳደር ሙስሊሞችን ከየአካባቢው እያደነ ማሰሩን ቀጥሏል appeared first on Zehabesha Amharic.