ለርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት፤ እንዲሁም በUK እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች በሙሉ።
በመጀመሪያ በቸሩ ፈጣሪአችን ሥም የከበረ ሰላምታችን ይድረሳችሁ።
በስደት ሀገር ከተመሠረተች 40 ዓመታትን ያስቆጠረቸው ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለአያሌ ዓመታት የምእመኗ ሰላምና አንድነት ተጠብቆ በመቆየት ለከፍተኛ የዕድገት ደረጃ ከደረሰች በኋላ እነሆ ባለፉት ሁለት ዓመታት ግን ሰላሟ ተናግቶ የቤተ ክርስቲያኗ በጎ ገጽታና መልካም ምሳሌነቷ ይልቅ በስሟ የሚፈጸመው ክፉውና አሳዛኙ ተግባር ጎልቶ እየተስተጋባ ብዙ ክርስቲያኖችን ሲያሳዝንና ግራ ሲያጋባ ቆይቷል።
The post በርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ አዳዲስ መረጃዎች appeared first on Zehabesha Amharic.