ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚከሰቱ አሳዛኝ የመኪና አደጋዎችን ስትዘግብ ቆይታለች:: ዛሬ ያገኘነው ዜና ደግሞ እሽጅግ አሰቃቂ ነው:: በቡራዩ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋና ተከትሎት በተነሳው የ እሳት ቃጠሎ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተዘገበ:: በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ልዩ ስሙ ቀርሳ በተባለ ስፈራ ትላንት ማምሻውን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰው ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ሲሉ መንግስታዊው ሚዲያዎች ዘግበዋል::
እንደ ዘገባዎቹ ከሆነ አደጋው የደረሰው ትላንት ምሽት 1 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ላይ ሲሆን፥ ወደ አዲስ አበባ ይመጣ የነበረ ሲኖ ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ከሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የደረሰው። በዚህ አደጋ የተነሳም የ11ዱ ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት ሲሆን ሲኖ ትራኩ ላይ የነበሩት ሹፌር እና ረዳት ከአደጋው መትረፍ ቢችሉም በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ ከ11 የሚበልጡ ሰዎች በተነሳው እሳት ተቃጥለው ህይወታቸው ማለፉን ፖሊስ ለመንግስት ሚዲያዎች አስታውቋል::
The post (አሳዛኝ ዜና) ሲኖ ትራክ እና ሚኒባስ በመጋጨታቸው በተፈጠረ እሳት የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ appeared first on Zehabesha Amharic.