(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚሰሙት የመኪና አደጋዎች እጅጉን እየበዙ መጥተዋል:: በየቀኑ የሚደርሰው የመኪና አደጋም በሰውና በንብረት ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ተጽፎ የሚያልቅ አይደለም:: ከአዲስ አበባ ወሬዎች ያገኘነው የፎቶ መረጃ እንደሚያመለክተው ዛሬ የካቲት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ከእኩለ ቀን በኋላ መንገዷን ስታ በካዛንቺስ መናኸርያ መንገድ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካዛንቺስ ቅርንጫፍ ጎራ ያለችው ላዳ ታክሲ በዚህ መልኩ ባንክ ገብታለች::
በንብረት ላይ የደረሰው አደጋ የታወቀ ሲሆን በሰዎች ላይ የደረሰው አደጋ በመጣራት ላይ ይገኛል::
The post (ዜና ፎቶ) ታክሲዋ ባንክ ገባች appeared first on Zehabesha Amharic.