Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ከEBC (የቀድሞ ETV) እና ከሰው ለሰው አዘጋጆች ምስጋናም ሆነ ሽልማት አልጠብቅም

$
0
0

ታሪኩ ደሳለኝ (የተመስገን ደሳለኝ ወንድም)

ትናንት የካቲት 1/2007 ዓ.ም በሸራተን ሆቴል በተደረገው የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ከEBC እና ከሰው ለሰው አዘጋጆች የጥሪ ካርድ ሊደርሰኝ ቀርቶ ዝግጅቱ እንዳለ እንኳን የሰማሁት ትላንት ከዝዋይ እስር ቤት ስመለስ አንድ ሰው ደውሎ የዝግጅቱን መግቢያ ትኬት ካለህ ሲለኝ ነው፡፡
tariku desalegn
እኔና ሰው ለሰው ድራማ

በዚህ ተከታታይ ድራማ ላይ ከክፍል 57 እስከ 87 ድረስ (ምዕራፍ ሦስት ሙሉው) ሲኒማቶግራፊው የተሰራው በእኔ አማካኝነት ነበር፡፡ በስራው ላይ በነበርኩበት ወቅት የካሜራው ቴክኖሎጂ DSLR እንዲሆን፣ አንድ ሰው ሁለት ሦስት ስራ ከሚመደብ ለያንዳንዱ ስራ እራሱን የቻለ አንድ ሰው እንዲቆጣጠረው ጥረት አድርጊያለሁ፡፡ ይሄም በመሆኑ አዘጋጆቹ የሚያስቡትን ሁሉ የሚሰራ ክሩ ተፈጥሮአል፡፡ ከዚህ ባለፈም ከሳምንቱ አንዱን ቀን የሰራነውን ስራ የምንገመግበት ቀን እንዲኖር ሃሳብ አቅርቤ የስራው አካል ሆኖአለ፡፡ በዚህም ሰህተቶቻችንን ወዲያው ማረም ችለናል፡፡ የድራማውን ታሪክ በሲኒማቶግራፊ (ማለትም በብርሃን፣ በካሜራ እንቅስቃሴ እና በፍሬም) መግለፄን ግን ሌላ ባለሞያ ቢናገረው ይሻላል ብዬ አልፈዋለው፡፡

እኔና EBC

ከአንድ ወር ከ 11 ቀናት በፊት የኢትዮጲያ ኢንተርናሽናል 9ኛው የፊልም ፌስቲቫል ሲደረግ በቀሚስ የለበስኩለት ፊልም በሲኒማቶግራፊነት ሳሸንፍ የሽልማቱን መታሰቢያነት በእስር ላይ ለሚገኘው ለወንድሜ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይሁንልኝ ማለቴ ይታወሳል፡፡ EBC ፌስቲቫሉን በሚመለከት ከ 6 ቀን በኋላ በእሁድ መዝናኛ ፕሮግራሙ ላይ በሰራው ዜና ላይ ሰፊ ሀተታ ከመስጠቱም በላይ ተሸላሚዎቹንም ኢንተርቪው አድርጎ አቅርቧል፡፡ ስለኔ ይቅርና ስለ ፊልሙ መሸለም ምንም ሳይል አልፎታል፡፡ ዛሬ ደግሞ ለረጅም ወራት የሰራሁበት ድራማ መጠናቀቂያ ላይ አልጠሩኝም…. በዚህ አጋጣሚ ዛሬ የተሸለማቹሁ ባለሞያዎች እንኳን ደስ ያላቹህ እላለሁ
በመጨረሻም

ከሰው ለሰው ድራማ ሰሪዎች ላይ አንድን ሰው የበለጠ ላመስግን፡፡ “መስፍን ጌታቸው” (ሞገስ) በተናገርከው በመፅናትህና እኔና አንተ ስለምናውቃቸው ነገሮች ሁሉ፡፡

The post ከEBC (የቀድሞ ETV) እና ከሰው ለሰው አዘጋጆች ምስጋናም ሆነ ሽልማት አልጠብቅም appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>