ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ፣የደሴ፣ የሀዋሳ፣የአርባምንጪ፣ የሀረር፣ የሚዛን ተፈሪ፣የሰበታ፣ የባህርዳር፣ የወልቂጤና የሌሎችም ከተሞች ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት፣በካድሬዎች አማካይነት ህዝቡ የምርጫ ካርድ በግዳጅ እንዲወስድ እና ድምጹን ለኢህአዴግ እንዲሰጥ እየተደረገበት ያለው ግፊት ከመቼውም ጊዜ በላይ እየከፋ መጥቷል።
ከካድሬዎቹ ማስፈራሪያዎች መካከል፦<>የሚሉት ይገኙበታል። <>ተብሏልም።።
በግድ የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑና ኢህአዴግን እንዲመርጡ እየተገደዱ መሆናቸውንም የገለጹ በርካቶች ናቸው። ከዚህም በላይ አንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች ኢህአዴግ አንዳንድ ሰዎችን ያለፍላጎታቸው በተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎቻቸው ጫና በመፍጠር ለሱ እንዲሰሩለት በማስጠንቀቅ በየምርጫ ጣቢያው በገለልተኛ ስም ማስቀመጡ የተጋለጠ ሲሆን፤ ሰዎቹ-ከተቃዋሚዎች ጥያቄ ቢቀርብላቸው <>የሚል ምላሽ ይሰጡ ዘንድ መመሪያ እንደተነገራቸው ተሰምቷል።
በተመሳሳይ ምርጫውን ተከትሎ በተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ላይ እየተፈጸመ ያለው እስርና ድብደባ ተባብሶ ቀጥሏል። ታህሳስ 27/2007 ዓ,ም በባህርዳር ከተማ የኢትዮጰያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መድረክ አባላት – በስርዓቱ አገልጋዮች ታፍነው ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል።
ታፍነው ከተወሰዱት የመድረክ አባላት መካከል፤ አቶ ቴዎድሮስ መለስ፤ ወ/ሮ ሪዒማ ከድር፤ በባህር ዳር ዩንቨርስቲ መምህር የነበረው አቶ ተፈራ ማሙና ሌሎችም የሚገኙበት ሲሆን፤ የታፈኑበት ምክንያትም ሆነ ፤ያሉበት ስፍራ እስካሁን ድረስ አልታወቀም።
እንዲሁም ” ኢቲቪ ውሸታም ነው ፣ ኢህአዴግ ሌበ ነው”ብለሀል ተብሎ ክስ የተመሰረተበትና የሶስት ዓመት እስራት የተፈረደበት የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት አባል የሆነው አዲሱ ሁሴን፤ በእስር ቤት ከፍተኛ ድብደባና ግርፋት እየተፈጸመበት እንደሆነ ድርጅቱ ገልጿል። የደቡብ ወሎ የመኢአድ አባል የሆነው አዲሱ ሁሴን ፍርደኛ እስረኛ ሆኖ ከድብደባና ግርፋት ማረፍ አለመቻሉ፤ በኢትዮጰያ እስር ቤቶች ለሚፈጸሙ የከፉ ሰብ ዓዊ መብት ጥሰቶች አንድ ማሳያ ነው ብለዋል-መረጃውን ያደረሱን የመኢአድ አባል።
ከሰሞኑ ብቻ ብቻ ሁለት የአንድነት ፓርቲ አባላት የፐጻርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ ተሳትፈው ወደቤታቸው ሲያቀኑ መደብደባቸው እና በወላይታ የሰማያዊ ፓርቲ አስተረባባሪዎች መታሰራቸው ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ፓርቲና የኢትዮጰያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ በጋራ ባወጡት መግለጫ ገዥው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ በተቃዋሚዎች ላይ በተለይም በሰማያዊ፣ በአንድነትና በ መ ኢአድ ፓርቲዎች ላይ የሚፈጽሙትን ዛቻና በደል እንዲያቆሙ መጠየቃቸውን ነገረ-ኢትዮጵያ ዘግቧል
ፓርቲዎቹ ህዳር 7/2007 ዓ.ም ‹‹በምርጫ ዋዜማ በፓርቲዎች ላይ የሚደርሰው ደባና ዛቻ በአስቸኳይ ይቁም›› በሚል በጋራ ባወጡት መግለጫ ፤ ሰማያዊ ፓርቲ አገራዊ ግዴታውን እየተወጣ በመሆኑ፣ እንዲሁም መኢአድና አንድነት ብቃት ያላቸው ልሂቃንን ማፍራት በመቻላቸው ስጋት የተፈጠረበት ገዥው ፓርቲ – ፓርቲዎቹን ለማጥፋት እየጣረ መሆኑን በመጥቀስ፤<> ሲሉ ወቅሰዋል፡፡
ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው-ገዥው ፓርቲ -በፓርቲዎቹ ላይ እየፈጸመ ካለው ድርጊት እንዲቆጠብ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድመረ ከገዥው ፓርቲ መሳሪያነት ወጥቶ የተጣለበትን ኃላፊነት እንዲወጣ፤ አሣስበዋል፡፡
Source:: Ethsat