Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: ኤች.አይ.ቪ ኤድስን የሚያድኑ መድሃኒቶች ተፈጥረዋል የሚለው ምን ያህል እውነት ነው?

$
0
0

ውድ አዘጋጅ፡- የ21 ዓመት ወጣት ሴት ስሆን በአሁኑ ወቅት በግል ኮሌጅ ውስጥ በመማር ላይ እገኛለሁ፡፡ የምኖረው ጥሩ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦቼ ጋር ነው፡፡ ከወንድ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ የጀመርኩት ከአራት ዓመት በፊት ማለትም ገና የ17 ዓመት ወጣት በነበርኩበት ጊዜ ነው፡፡

በኤች.አይ.ቪ ኤድስ እንዴትና መቼ እንደተያዝኩ አላውቅም። ክብረ ንፅህናዬን ከገፈፈው ከመጀመሪያው የወንድ ጓደኛዬ በተጨማሪ እስካለፈው ዓመት ድረስ ከአራት የተለያዩ ወንዶች ጋር ወሲባዊ ግንኙነትን ፈፅሜያለሁ፡፡ በስሜት የተሞላሁ በመሆኔ በግንኙነት ወቅት ኮንዶም የመጠቀም ጥያቄ አቅርቤ አላውቅም፡፡

HIVከአንድ ዓመት በፊት ሁለተኛው የወንድ ጓደኛዬ በጠና ታሞ መሞቱን በመስማቴና አንድ ጓደኛዬም ልጁ የሞተው በኤች.አይ.ቪ መሆኑን ስትነግረኝ ተጠራጥሬ በምስጢር ባደረኩት ምርመራ ቫይረሱ በደሜ ውስጥ እንደሚገኝ ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡
በአሁኑ ወቅት ሁሉንም ነገር በፀጋ ተቀብዬ ከቫይረሱ ጋር በመኖር ላይ እገኛለሁ፡፡ እንደ ቀድሞው መቅበጤንም ትቻለሁ፡፡

ውጤቴን ከሰማሁ በኋላ ላለፈው አንድ ዓመት ወሲባዊ ግንኙነት አላደረግኩም፡፡ ሲዲ ፎሬ በጣም ያልወረደ በመሆኑ በየጊዜው የምጎበኛት ሐኪም ፀረ ኤች.አይ.ቪ መድሃኒት እንድጀምር አላዘዘችኝም፡፡ ያም ሆኖ በዚህ የወጣትነት ዕድሜዬ በቫይረሱ መጠቃቴ ሁሌም ያሳዝነኛል፡፡ በየጊዜው በኢንተርኔት አማካኝነት ስለ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ የሚወጡ ጥናታዊ ፅሑፎችንም እከታተላለሁ፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት አንድ ፅሑፍ ቫይረሱ የሚጠፋበት እና ሰዎች ከኤድስ ነፃ የሚሆኑበት ጊዜ በጣም ሩቅ እንደማይሆን በመግለፁ ውስጤ በተስፋ ተሞልቷል፡፡ አሁን ልጠይቅህ የፈለኩትም ይህንኑ በሚመለከት ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ ውስጥ ቫይረሱን በከፍተኛ ደረጃ ሊከላከሉ እና ሊያጠፉ የሚችሉ መድሃኒቶች ተፈጥረዋል ይባላል። ይህ ምን ያህል እውነት ነው? እውን ከኤድስ መዳን ወይም መፈወስ የሚቻልበት ጊዜ እየመጣ ይሆን? ቫይረሱን በቅድመ ክትባት ለመከላከል የሚቻልበት ሳይንሳዊ ዘዴ ተገኝቷል የሚባለውስ እውነት ነው? እባክህን በእነኚህ ጥያቄዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ስጠኝ፡፡
ሠላማዊት አስታጥቄ

ውድ እህታችን፡- ጥንቃቄ በጎደለው ወሲባዊ ግንኙነት ምክንያት በዚህ የወጣትነት ዕድሜሽ በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ በመያዝሽ አዝነናል፡፡ ይሁን እንጂ ቫይረሱ በደምሽ ውስጥ ተገኘ ማለት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመኖር ወደ አለመኖር ትሸጋገሪያለሽ፣ ማለት እንዳልሆነ ተገንዝበሽ እንድትፅናኚ እንጠይቅሻለን። ይህንን የምንልሽ ከባዶ ሜዳ ተነስተን ሳይሆን በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በመሰራጨት ላይ የሚገኙት የፀረ.ኤች.አይ.ቪ መድሃኒቶች ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩትን ዕድሜ አስገራሚነትና ባልተጠበቀ መልኩ እያራዘሙት በመሆናቸው ነው፡፡ እናም በአሁኑ ወቅት አንድ ሰው በሚያደርገው ምርመራ ቫይረሱ በደሙ ውስጥ እንደሚገኝ ቢያረጋግጥ እንኳን ስለ ሞት አይጨነቅም፡፡

በእርግጥ እስካሁን ድረስ ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ሙሉ በሙሉ ከደም ውስጥ ማጥራት የሚችል መድሃኒት የለም፡፡ ይህም ማለት ቫይረሱን ከአንድ ሰው አካል ውስጥ ማጥፋት የሚችል እና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ማረጋገጫ የተሰጠው መድሃኒት አልተገኘም፡፡ ይሁን እንጂ በኤች.አይ.ቪ ህክምና ውስጥ በየጊዜው አስገራሚ የሆኑ ዕድገቶችና መሻሻሎች እየተፈጠሩ ሄደዋል፡፡ በዚህም መሰረት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሚደረጉት የህክምና ክትትሎችና መድሃኒቶች ከኤች.አይ.ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎችን ህይወት እየታደጉት ይገኛሉ፡፡ እነኚህ ሁኔታዎች የታማሚዎችን አዕምሯዊ እና አካላዊ ሁኔታዎች በማደስ ላይ ናቸው፡፡

በአውሮፓ ውስጥ አንዳንድ ሰዎች ከቫይረሱ እየተፈወሱ ስለመሆናቸው የሚናፈሰውም ወሬ ቢሆን እውነትነት ያለው ይመስላል፡፡ ከእነኚህ ከኤች.አይ.ቪ መፈወሳቸው ከተነገረላቸው ሰዎች መካከል ‹‹የበርሊኑ ታማሚ›› (The Berlin Patient) በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀው ራሞር ብራውን ይገኝበታል፡፡ በእርግጥ የበርሊኑ ታማሚ ጉዳይ በአውሮፓ ውስጥ በሚገባ የሚታወቅና ጥልቀት ያለው ጥናትም የተካሄደበት ነው፡፡ ታማሚው እንደተባለውም ከበሽታው መፈወሱ ተረጋግጧል፡፡ ይሁን እንጂ ሳይንስ ለዚህ ሰው የመፈወስ ጉዳይ እስካሁን ድረስ እውቅና ሊሰጠው አልፈለገም፡፡

የበርሊኑ ታማሚ ከበሽታው በመፈወሱ ምክንያት በአሁኑ ወቅት የፀረ ኤች.አይ.ቪ መድሃኒቶችን በመውሰድ ላይ አይደለም። በእርግጥም በቲሞቲ ብራውን ውስጥ የሚገኘው የቫይረሱ መጠን በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ መምጣቱ ተረጋግጧል፡፡ ተፈጥሯዊው በሽታን የመከላከል አቅሙም እንደማንኛውም ጤነኛ ሰው የተሟላ ነው፡፡

ከበርሊኑ ታማሚ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ጉዳዮች እዚህም እዚያም በመታየት ላይ ናቸው፡፡ በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ አንዳንድ ሰዎች ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ የፀረ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ፈውስን ማግኘታቸው በስፋት ይወራል፡፡ በውጭ ሀገር ደግሞ ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ ቫይረሱን በተሻለ ሁኔታ ማዳከም እና የሲዲ 4 መጠንን ለማሳደግ መቻሉ እየተነገረ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ሳይንቲስቶች በእነኚህ ሁኔታዎች አልተዘናጉም፡፡ ቫይረሱን ሙሉ በሙሉ ከደም ውስጥ ለማስወገድ የሚችለውንና ሳይንሳዊ ማረጋገጫ የሚሰጠውን መድሃኒት ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙት ሳይንቲስቶች የመፈወሻ መድሃኒቱ በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል፡፡

በቅርቡ የተላላፊ ቫይረሶችና ተለዋጭነት ያላቸው ህመሞች 21ኛው ኮንፈረንስ በቦስቶን ከተማ ተካሂዶ ነበር፡፡ በዚህ ኮንፍረንስ ላይ ሳይንቲስቶች የገለፁት ምንም እንኳን ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ የሚችለው መድሃኒት እስካሁን ባይፈጠርም ህክምናውን በሚመለከት ከፍተኛ መሻሻሎች መታየታቸውን ገልፀዋል። እነኚህ መሻሻሎች የተገኙት ደግሞ ቫይረሱ በደም ውስጥ እንዴት ለረዥም ጊዜ መቆየት እንደሚችል እና እንዴትስ ሊጠፋ እንደሚችል ተጨማሪ ዕውቀቶች በመገኘታቸው ነው፡፡

ከኤች.አይ.ቪ ኤድስ ፈውስ ያገኙ ሰዎችን በሚመለከት ከጀርመኑ ታማሚ በተጨማሪ ሌሎች አጋጣሚዎችም ተስተውለዋል፡፡ ከእነኚህም አጋጣሚዎች መካከል አንዲት በሚሲሲፒ ውስጥ የምትኖር ህፃን ትገኝበታለች፡፡

ዴቦራ ፔርሱር የተባለች በጆንስ ሆፕኪንስ ሆስፒታል ውስጥ የምትገኝ ሐኪም ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ በደሟ ውስጥ ከሚገኝ እናት የተወለደችውን ህፃን በሚመለከት ስትገልፅ ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በሚያደርገው የህክምና ጥበብ ባለመታገዟ በተወለደችበት ወቅት ህፃኗ በቫይረሱ መያዟን ታረጋግጣለች። በመሆኑም ህፃኗ በሚሲሲፒ ከተማ ውስጥ በሚገኝ የህፃናት ሐኪም ቤት ውስጥ እንድትቆይና ከተወለደች ከ30 ሰዓታት በኋላ የአንታየርትሮቫይራል ህክምና እንድትጀምር ተደረገ፡፡
ከህፃኗ ጨቅላነት አንፃር ይህ ህክምና አደገኛነት ሊኖረው ይችል ነበር፡፡ ይሁንና ህይወቷን ለማትረፍ ይህንን ህክምና ከማድረግ ውጭ ሌላ አማራጭ ስላልነበረ ሕፃኗ ለ18 ወራቶች ያህል በሆስፒታሉ ውስጥ ተኝታ የፀረ ኤች.አይ.ቪ ህክምናውን ስትከታተል ቆየች፡፡ በመጨረሻም ማለትም ከ18 ወራት በኋላ ቤተሰቧ በመልካም ጤንነት ላይ የምትገኘውን ህፃን ከሆስፒታሉ አውጥተው ወደ ቤታቸው ይዘው ሄዱ፡፡

የፀረ.ኤች.አይ.ቪ ህክምናውንም አቆመች፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ህፃኗ ወደ ሆስፒታሉ ተመልሳ ምርመራ ስታደርግ በደሟ ውስጥ የነበረው የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ መጥፋቱ ተረጋገጠ፡፡ አሁን ህፃን ዲቦራ የሶስት ዓመት ህፃን ስትሆን ከቫይረሱ ነፃ ሆና ጤናማ ኑሮን በመኖር ላይ ትገኛለች፡፡ ይህም ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመካሄድ ላይ የሚገኙት የፀረ ኤች.አይ.ቪ ህክምናዎች ፈዋሽ መሆናቸውና ህፃናት ጊዜው ከማለፉ በፊት ህክምናውን ካገኙ ከበሽታው ሊፈወሱ እንደሚችሉ ያመለክታሉ፡፡ በዚህ አይነት ሁኔታ ህክምናቸውን የተከታተሉ በርካታ ህፃናት እየተፈወሱ መሆናቸውም ተረጋግጧል፡፡ ከዚህ በታች ያቀረብነው ቃለ መጠይቅ ደግሞ ሰዎች ከኤች.አይ.ቪ የሚፈወሱ ስለመሆናቸው የሚተርክ ነው፡፡

ዶ/ር ማስ አር ዩሱፍ የስሪ ላንግ ብሔራዊ የህክምና አገናኝ ተቋም ምክትል ዳይሬክተር እና የነርቭ ህክምና ስፔሻሊስት ናቸው፡፡ በስሪላንካ ፒታ ኮቴ ሆስፒታል በፍልስፍና እና በነርቭ ህክምና ላይ ጥናት ያደረጉት ዶ/ር ዮሴፍ በናቹራፓዚ እና በማግኔቲያዊ ህክምና ሰፊ ዕውቀት ያላቸው ናቸው፡፡ ዶክተሩ በቅርቡ ኮሎምቦን በጎበኙበት ወቅት ከኤች.አይ.ቪ ኤድስ ጋር እየተካሄደ ያለውን ትንቅንቅ በሚመለከት ከአንድ የህክምና መፅሔት ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር፡፡ እኛም ቃለ መጠይቁን በሚከተለው መልኩ አቅርበነዋል፡፡ ጠያቂያችንም ከቃለ ምልልሱ ግንዛቤ እንደምታገኚ እንገምታለን፡፡

ጥያቄ፡- ኤች.አይ.ቪ ሰዎችን የሚያጠቃው እንዴት ነው?
መልስ፡- ኤች.አይ.ቪ ኤድስ በከፍተኛ ደረጃ የሚያጠቃው ተፈጥሯዊውን የበሽታ መከላከል ሲስተም ነው፡፡ ቫይረሱ የአምዩኒ ሲስተማችንን ካዳከመ በኋላ በተለያዩ በሽታዎች እንድንጠቃ ያደርገናል። አንድ ሰው ሁለት አይነት ቲ ሴሎች አሉት። አንደኛው ቲ ሴል ሲዲ 4 የተባለ ሞሉክዩል በላዩ ላይ የያዘ ሲሆን የዚህ ሞሉክዩል ተግባር ደግሞ ወደ ሰውነታችን የሚገባውን ቫይረስ በመከላከል ማስወገድ ነው፡፡ ሁለተኛው በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው ሞሎክዩል ሲዲ 8 የተባለው ነው፡፡ የዚህኛው ሞሎክዩል ተግባር በበሽታ የተጠቁ ሴሎችን ማስወገድና ፀረ ቫይረስነት ያላቸውን ንጥረ ነገሮች ማምረት ነው። እነኚህ ሁለት የሞሎክዩል አይነቶች ናቸው፡፡ በተቀናጀ መልኩ ሰውነታችን በአንድጀንስ፣ በባክቴሪያ፣ በቫይረስ፣ በፈንገስ እና ከመሳሰሉት ህመም አምጪ ህዋሳት እንዳይጠቃ የሚያደርጉት።

ኤች.አይ.ቪ በሲዲ 4 ሞሉክዩል ጋር በመጣበቅ ቫይረሱ ወደ ውስጥ ገብቶ ሴሎችን እንዲበክል ያደርጋል፡፡ በእርግጥ አንድ በውስጡ የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ያለበት ሰው ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳይሰማው ለተወሰኑ ዓመታት በጤነኛነት ሊቆይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም በቫይረሱ በየቀኑ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የሲዲ 4 ቲ ሴልስ በቫይረሱ ቢደመሰስም የዚያኑ ያህል ቁጥር ያላቸው ሞሉክዩሎችን ሰውነታችን ስለሚያመርትና የተደመሰሱትን ስለሚተካ ነው፡፡

ጥያቄ፡- ኤች.አይ.ቪ ያለ ጥርጥር ኤድስን ያስከትላል ማለት ይቻላል?
መልስ፡- አንድ አዋቂ ሰው ቫይረሱ ወደ ሰውነቱ ከገባ በኋላ ምንም አይነት የህመም ስሜት ሳይሰማው ለ8 ዓመታት ሊቆይ ይችላል፡፡ ለህፃናት ደግሞ አማካይ ጊዜ 2 ዓመታት ነው፡፡ ይህም ሆኖ አንዳንድ አማይዋሎጂስቶች ሞሎኪያሮች፣ ባዮሎጂስቶች፣ ቫይኖሎጂስቶች፣ ባዩኬሜስቶች እና ማይክሮባዮሎጂስቶች ኤች.አይ.ቪ ከመደበኛው በሽታ አስተላላፊ ቫይረስ ምንም የሚለይበት ነገር እንደሌለ ይገልፃሉ፡፡ በእነኚህ ተመራማሪዎች እምነት መሰረት ኤች.አይ.ቪ ኤድስን አያከስትልም። ለዚህ እምነታቸው የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ ኤድስ የባህሪ በሽታ እንጂ በኤች.አይ.ቪ የሚከሰት አይደለም የሚል ነው፡፡ በእነኚህ ጠበብቶች እምነት መሰረት ኤድስ የሚከሰተው በአሙዩኒ ሲስተም ውስጥ በሚከሰት በርካታ የመዛባት ሁኔታዎች ምክንያት ነው፡፡ እነኚህም ሁኔታዎች በወሲባዊ ግንኙነት ምክንያት በሚተላለፉ ህመሞችና በበርካታ የቫይረሱ ጥቃቶች ወዘተ… እንጂ በኤች.አይ.ቪ የሚከሰት እንዳልሆነ ለማሳመንም ይሞክራሉ። በዚህም ሆነ በዚያ አንድ ሰው በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ ሲያዝ ተፈጥሯዊው በሽታን የመከላከል አቅሙ እየመነመነ ይሄዳል፡፡ ይህ ሁኔታም እንደ የሣምባ ምች፣ ካፓሲ ሰርኮም፣ ሰውነትን ለሚያከሳ በሽታ፣ ለተቅማጥ እና ለሌሎችም አደገኛ በሽታዎች ያጋልጠናል፡፡ እነኚህ በሽታዎች ደግሞ ሰውን የመግደል አቅም ያላቸው ናቸው፡፡
ጥያቄ፡- በእርስዎ ቲዩሪ መሰረት በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ምክንያት ተፈጥሯዊው በሽታን የመከላከል አቅሙ የወረደውን ሰው የጤንነት ሁኔታ እንዴት ማሻሻል ይቻላል?

መልስ፡- የወደቀን የኢሚዩኒ ሲስተም ለማነቃቃት በሰው ላይ ችግር ሊያስከትሉ የሚችሉ መድሃኒቶችን በትንሹ እየሰጡ በማከም በሰውነት ውስጥ ያለውን ፊዚዮሎጂካል ሚዛን ማስተካከል የግድ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ በመርፌ ነርቭን እየወጉ የማከም ዘዴ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ አንዴ ተስማሚ የሆነውን መድሃኒት ማግኘት ከተቻለ እና የአሲድ ጂኒክ ሁኔታን በሰውነታችን ውስጥ ወደ አልካሊ ጂኒክ መለወጥ ከተቻለ በሽታን የመከላከል አቅማችን እየተጠናከረ ይሄዳል፡፡ ይህንን ለውጥ መፍጠር የምንችለው ደግሞ በናቹር ፓቲክ ሳይንሳዊ ዘዴ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሰውነታችን ማንኛውንም በሽታ ለመዋጋት የሚችልበትን ተፈጥሯዊ ጥንካሬ እያገኘ ይሄዳል፡፡

በመሰረቱ እኛ ሰዎች የምንኖረው በርካታ ጎጂነት ካላቸው እና ከሌላቸው ህዋሳት ጋር ነው። በሳይንሳዊ ግምት መሰረት አንድ ሰው በአንድ ሰዓት ውስጥ ከ14 ቢሊዮን በላይ ፓቶጂነሶችን ወደ አየር ይለቃል፡፡ ይሁንና በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው የአምዩኒ ሲስተም በየሴኮንዱ ውስጣችንን ከእነኚህ ህዋሳት የማንፃት ተግባር ያከናውናል። ኤች.አይ.ቪ ኤድስን በመዋጋቱ ሂደትም ውስጥ ተመሳሳይ ሁኔታ መፈጠር አለበት።

ጥያቄ፡- እንደ ሆሞፓዚ፣ ፓልም ዲያግኖሲስ ቴክኒኮች፣ ማግኔቶራፒ፣ አዩርቪዳ እና ሌሎችም የህክምና አይነቶች ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ወደ ማዳን ሊያደርሰን ይችሉ ይሆን?

መልስ፡- በእርግጥ የመርፌ ነርቭን እየወጉ የማከሙ ዘዴ ከሌሎች ናውትሮፓቲክ የህክምና ዘዴዎች ጋር በመቀናጀት ቫይረሱ ባለበት እንዲቆምና የአምዩኒ ሲስተማችንንም ሊያሳደግ ይችላል። ሁሉም ችግር የሚመጣው በራሱ በቫይረሱ ሳይሆን ተፈጥሯዊው በሽታን የመከላከል አቅም ሲዛባ ነው፡፡ ፊዚዮሎጂያዊ የህክምና ዘዴ ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከል አቅምን ካጠናከረ ቫይረሱ ራሱን እየወለደ ለመራባት አይችልም። ይህም ሁኔታ የመራባት ባህሪውን ያሳጣዋል፡፡ አንዳንድ ከኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ጤነኛ እና የተረጋጋ ህይወት በመኖር ላይ የሚገኙትም በዚህ ምክንያት ነው፡፡

ጥያቄ፡- በአጭሩ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከኤች.አይ.ቪ ኤድስ የመፈወስ ሁኔታ ይፈጠራል ማለት ነው?

መልስ፡- አንድን በኤች.አይ.ቪ ኤድስ የተያዘ ሰው የሚያድነው ብቸኛው መድሃኒት የገዛ ራሱ ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከል አቅም መጠናከሩ ነው፡፡ ሌሎች የህክምና ዘዴዎች አምዩኒ ሲስተምን ለመንከባከብና ቫይረሱ እንዳይራባ ለማድረግ ብቻ የሚከናወኑ ናቸው፡፡ ይህ ህክምና የህመምተኛው አምዩኒ ሲስተም ከቫይረሱ ጋር ብቻ ሳይሆን ከመድሃኒቶቹም ጋር ተስማምቶ ያለ ችግር እንዲያድግ ያደርገዋል፡፡ ይህ እውነት ያለው ነገር ነው። በመሆኑም ሐኪሞች በቅድሚያ ማድረግ ያለባቸው ነገር የህመምተኛው ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከል አቅም እንዲያድግ ጥረት ማድረግ ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ህመምተኛው ወይም ህመምተኛዋ ወደ ሙሉ ፈውስ በሚያደርሳቸው ጎዳና ላይ እንዲጓዙ ያደርጋቸዋል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን አሚዩኒ ሲስተምን ሳያሳድግ የሚካሄድ ማንኛውም የህክምና ዘዴ ህመምተኛውን ከሞት ሊያድነው አይችልም፡፡

ጥያቄ፡- ነርቭን በመርፌ በመውጋት ከሚካሄደው ህክምና በተጨማሪ ሌላ ኤች.አይ.ቪ ኤድስን በተሻለ ሁኔታ ሊከላከል የሚችል መድሃኒት አግኝተዋል?

መልስ፡- በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ኪንግደም የሆምፓዝ ሐኪም የሆኑት ዶክተር ፒተር ቻፕል የፈጠሩትን መድሃኒት በጥቅም ላይ ለማዋል በሙከራ ላይ እገኛለሁ፡፡

ጥያቄ፡- ይህ መድሃኒት ከአሁን በፊት በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ህመምተኞች ላይ ተሞክሯል? ውጤቱስ ምንድነው?
መልስ፡- አዎን! ግን ሙከራውን ያደረኩት እኔ ሳልሆን ዶ/ር ቻፕል ናቸው። ዶ/ር ቻፕል በኢትዮጵያ ውስጥ ከኤች.አይ.ቪ ኤድስ ጋር በሚኖሩ 200 ሰዎች ላይ ባደረጉት ሙከራ አስደናቂ ውጤት ተገኝቶበታል፡፡ በእርግጥ እስካሁን ያለውን ሁኔታ ከክሊኒካል ሙከራ የዘለለ አይደለም። ግን አዲሱ መድሃኒት እጅግ በጣም በሚያስገርም ሁኔታ የሰውነትን የሲዲ 4 መጠን ከማንኛውም ጤነኛ ሰው ጋር ለማስተካከል የተቻለ ሲሆን የህመም ስሜቶችም መቀነሳቸው ተረጋግጧል፡፡

ጥያቄ፡- ይህ ከሆነ ታዲያ መድሃኒቱ ከሙከራ አልፎ በመላው ዓለም በስፋት ጥቅም ላይ ለምን አልዋለም?

መልስ፡- መድሃኒቱ እስካሁን ድረስ ጥቅም ላይ ያልዋለው ገንዘብና አስፈላጊው ትብብር ስለተነፈገው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ዶ/ር ቻፕል መድሃኒቱን የበለጠ ለማሻሻል ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ እኔም በዶክተሩ የተፈጠረውን መድሃኒት በማሻሻል ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ሙሉ በሙሉ የሚፈውስ መድሃኒት የመፍጠር ሙከራዬን ገፍቼበታለሁ፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>